UMMA TOKEN INVESTOR

About me

ሁሌም አመስጋኝ አድርገኝ

ummaabdurezak shared a
Translation is not possible.
🔴ከጎረቤታችን የኬንያ ሙስሊሞች ምን እንማራለን…?
🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰
♣️ እንደ ኬንያ ማእከላዊ ስታትስቲክስ መረጃ የኬንያ ሙስሊሞች ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ህዝብ 11 % ያክል ይሸፍናሉ። ያ ማለት 5 ሚሊዮን አካባቢ ይሆናሉ ማለት ነው። ያ ማለት የሶማሌ ሙስሊሞች ከኬንያ አጠቃላይ የሙስሊሞች ብዛት ይበልጣል ማለት ነው ። INSAMER የተሰኘ ተቋም ይፋ ባደረገው አሃዝ ደግሞ የኬንያ ሙስሊሞች ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ህዝብ ከ 25-30% ይሸፍናሉ። ያ ማለት ከ 12 - 14ሚሊዮን ህዝብ ማለት ነው።
በከፍተኛው አሃዝ ወስደን ብናሰላው እንኳ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ብዛት ከኬንያ ሙስሊሞች በ 5 እጥፍ ገደማ ይልቃል!
ነገር ግን
♣️ የኬንያ ሙስሊሞች ሁለት ታላላቅ አለምአቀፍ ኢስላማዊ ዩኒቨርስቲዎች አሏቸው ። RAF international universty እና Umma University የሚባሉ ሁለት ግዙፍ ዩኒቨርስቲዎች እና የምርምር ማእከሎች! ነገር ግን ከ 50 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ምንም አይነት ዩኒቨርስቲም ሆነ ዪኒቨርስቲ ኮሌጆች የላቸውም!
♣️ የኬንያ ሙስሊሞች በርካታ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንድሁም ኮሌጆች ሲኖሯቸው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ግን ያሏቸው በጣት የሚቆጠሩ የኢለመንታሪ ትምህርት ቤቶች ብቻ ነው ።
♣️ የኬንያ ሙስሊሞች በፖለቲካ ተሳትፏቸውም ከኢትዮጵያዊያን በጣም የተሻለ ነው ። ከየትኛውም ማህበረሰቦች በላይ የኬንያ ሙስሊሞች በጣም ጠንካራ በጣምም ተፅእኖ ፈጣሪዎች ናቸው ። 222 መቀመጫ ካለው የኬንያ ፓርላማ 32 ቱ ሙስሊሞች ናቸው። ሚስሊሞች በኬንያ በጣም ስትራቴጂካዊ አካባቢዎችን የያዙ ሲሆን እነ ሞንባሳ ፣ ላሙ ወዘተ በመሳሰሉ የወደብ ከተሞች ላይ የሚኖሩት በአብዛኛው ሙስሊሞች እንደመሆናቸው በሀገሪቱ ፖለቲኮ-ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ያላቸው ተፅእኖ ከፍተኛ ነው።
♣️ የኬንያ ሙስሊሞች ራሳቸውን በከፍተኛ ልእልና ነው የሚያዩት ። በኬኒያዊያን ዘንድ ሙስሊምነት ማለት ስልጡንነት አዋቂነት እና በማህበራዊ አስተሳሰብ ላቅ ማለት ነው ። ራሳቸውንም የኬንያ ባለቤት አድርገው ነው የሚያዩት ። በርካታ የታሪክ አሻራዎችና ረጅም ዘመን የመሪነት ታሪክም አላቸው ። ኬንያዊያን ሙስሊሞች አለምአቀፋዊ ንቃተ ህሊናቸውም በጣም ከፍ ያለ ነው።
♣️ ኬኒያዊያን ሙስሊሞች ከራሳቸው አልፈው ስለመላው ሙስሊሞች ሁኔታ የሚያጠና የሚከታተል ታላቅ የሚዲያ ተቋም አላቸው ። የሚዲያ ግሩፑም ISLAM AND MEDIA WORKING GROUP ( #iamcr ) ይሰኛል። ይህ ድርጅት በአለም አቀፍ ደረጃ በመላው ሙስሊሞች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን ይከታተላል ፣ ጥልቅ ምርምሮችን ያደርጋል የመፍትሔ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል። ይህ ተቋም በተለያዩ የሙስሊሙ አለም ክፍሎች የሚገኙ ምሁራንን ስለ ኢስላማዊ አለም የሚዲያ እና ግንኙነት እንቅስቃሴ በአንድ በመሰባሰብ እንዲያጠኑና የመፍትሔ አቅጣጫ እንዲያስቀምጡ በከፍተኛ ሁኔታ ያበረታታል። በአንፃሩ የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች አንድም ጠንካራ ሚዲያ (Mainstream media ) የላቸውም ። ይህ አሳፋሪ ነው።
♣️ ኬንያዊያን በአንድ ጥላ ስር የሚያሰባስባቸው ፤ ፊርቃና መዝሃብ ሳይለይ እንደ ጃንጥላ ከለላ የሚሆናቸው የእስልምና ተቋም አላቸው ። ለኬንያዊያኑ ስድብ አይሁንብኝና እኛ መጅሊስ እንደምንለው ማለት ነው ። ያ የሀይማኖታቸው ከፍተኛ ተቋም Supreme council pf Kenya Muslims ( #supkem ) ይሰኛል። ይህ የሃይማኖት ተቋም በኬንያ ሙስሊሞች ከፍተኛው የስልጣን ባለቤት ነው ። ከፈትዋ ጀምሮ የተለያዩ ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴዎችን ከፖለቲካዊ እስከ ኢኮኖሚያዊ ከዚያም እስከ ማህበራዊ ዘርፎች የሙስሊሞችን እጣፈንታ ይወስናል። የራሱ ፍርድ ቤት አለው ። አንድ ሰው ሙስሊም እስከሆነ ድረስ ጉዳዩ የሚታየው በሼሪአ ፍርድ ቤት በኩል ነው ።
ዋና ቃዲና የኢስላማዊው ካውንስል ፕሬዝዳንት ስልጣናቸው ከሙስሊሞችም ይሻገራል ። የሙስሊሞች ካውንስል ፕሬዝዳንቱ የኬንያን ፕሬዝዳንት የማማከር ስልጣንም አላቸው ወይም የኬንያ ፕሬዝዳንት አማካሪ ናቸው ።
♣️ በዚህም የኬንያ መንግስት ከሙስሊሞች ጋር ሊኖረው የሚገባውን ግንኙነት ያማክራሉ ፤ የሙስሊሞችን ጥያቄ ፍላጎት ለመሪው በቀጥታ ይነግራሉ በአጠቃላይ እጅግ ከፍተኛ ስልጣን አላቸው።
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
ummaabdurezak shared a
Translation is not possible.
If You Want To Be Beautified By Allāh Then Study And Teach Ḥadeeth
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : نضر الله امرأ سمع مقالتي فوعاها وحفظها وبلغها.
The Messenger of Allāh ﷺ said: “May Allāh beautify a man who hears my speech then understands it and memorises it and conveys it (to others).”
● [رواه الترمذي ٢٦٥٨ وصححه الألباني]
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
ረመዳን ቀን 2️⃣1️⃣
ከእናታችን አዒሻ (رضي ﷲ عنها) ተይዞ፡ እንዲህ ትላለች፦
﴿كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَجْتَهِدُ فِي الْعَشْرِ الْأَوَاخِرِ مَا لَا يَجْتَهِدُ فِي غَيْرِهِ.﴾
ነቢዩ (ﷺ) ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት ከሌላ ጊዜ በተለየ መልኩ (በዒባዳ) ላይ ይተጉ ነበር።
📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 1175
Send as a message
Share on my page
Share in the group
ummaabdurezak shared a
Translation is not possible.
⚡የኢስማኤል ሀኒየህ መገደል አንድምታ:-
እሱ የሐማስ የፍልስጤማዊያን የተቃውሞው ኃይሎች መሪ ብቻ አልነበረም፣ እሱ በቅርብ ዘመናት ፖለቲካ እና ኢስላማዊ ስርዓትን ከኢስላማዊ ጂሀድ ጋር አጣምሮ መሄድ እንደ ሰማይ ከራቃቸው ድንዙዝ አረቦች ዘር የተመረጠ የጀግንነት ምልክት ነበር፡፡
እሱ ዙሪያውን በከዱት ሱኒ አረቦች መካል ለሶስተኛው ቂብላ መከበር ሰበብ ለመሆን ድጋፍ ለማግኘት ሲባክን የነበረ መሪ ብቻ አይደለም፣ እሱ ዓለም ላይ ካሉት ሁሉም መሪዎች የተሻለ ኢስላምን ያወቀ ቁርዓንን ሀፍዞ ቁርዓንን የሀፈዙ ህዝቦችን የመራ የዘመናችን ሙዕሚን መሪ ነበር፡፡
እሱ ከፍልስጤም እና የመን የሱኒዮቹ ተቃውሞ እስከ ኢራቅ ሊባኖስ እና ኢራን የሺዓ ተቃውሞ ኃይሎች እኩል መግባባትን ፈጥሮ ቁድስን ያስከበረ የዲፕሎማሲ ሰው ብቻ አይደለም፣ እሱ እስራኤል በተቃውሞ ከበባ የማያባራ የስጋት ህይወት ውስጥ እንድትኖር ያደረገ የእስራኤልን መጥፋት በእጅጉ ያቃረበ ከገዢዎቹ ውጪ በሁሉም ሙስሊም ዓለም የሚወደድ ውድ ሰው ነበር፡፡
ለምን ተገደለ?
ኔታንያሁ እና መላው ምዕራባዊያን እንዲሁም ለዙፋናቸው የሚጨነቁ ሙስሊም መሪዎችም ጭምር የእሱን መሞት እንደሚፈልጉ እገምታለሁ እንዲሞት የሚፈልጉበት የሁሉም ምክንያት ግን ይለያያል፡፡
እስራኤል አሁን ጦርነቱን እንደት አድርጋ እንደምታቆመው መንገድ እየፈለገች ነው፡፡
አሳካዋለሁ ያለችው ድል ሩቅ እንደሆነ ግልፅ ነው ግን ለህዝቡ አሸነፍን ለማለት ይሄው ሳላህ አል አሩሪ እና ኢስማኤል ሀኒዬህን ከሐማስ ኮማንደር ፉአድ ሾክሪን ከሂዝቦላህ ገደልን (ፉኣድ ሾክሪ ገና ሂዝቦላህ ማረጋገጫ አልሰጠበትም አላህ ካተረፈው አስተካክላለሁ) እነዚህ ቡድች ከእንግዲህ አቅም የላቸውም ብለው ለማስረዳት ይሞክራሉ ከዚያም የተኩስ አቁም ስምምነቱ እስራኤል እንዳሸነፈች ተደርጎ እንዲታዎቸጅ ይፈልጋሉ፡፡
በምርጡ ሰው ግድያ ሁሉንም ሀገር እጠረጥራለሁ ሁሉንም ሀገር፣ ኔታንያሁ አሜሪካ በሄደ ሰአት ጦርነቱን አቁም ተብሎ መምጣቱን አውቀናል እሱም እሺ ቢያንስ ለፖለቲካ የሆኑ ሰዎችን ልግደል እኛ ምንም የሚወራ ድል ሳይኖረን ውጊያውን ካቆምን ለሁሉም የምዕራቡ ዓለም ሽንፈት እና ለተቃውሞው ብርታት ይሆናል ስለዚህ አግዙኝ ብሎ እንደለመናቸው አስባለሁ እነሱም ተስማምተዋል፡፡
ሁለተኛ ተጠርጣሪዬ ኢራን ነች፣ ዝርዝር መጻፍ አልችልም ግን እንዴት በዚህ ልክ ለሀኒዬህ ደህንነት ዋስትና መስጠት ሳይችሉ ጠሩት ሲቀጥል ሀገሪቱ ራሱ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔት የእስራኤል ሚሳኤል ዋና ከተማዋ ቴህራን ድረስ ገብቶ ሀኒዬህ ያለበትን ቤት እስኪመታ ደህንነቷ ያልተረጋገጠ ሆነች?
ሶስተኛ ተጠርጣሪዬ የአረብ ሀገራት መሪዎች ናቸው፣ እዚህ ላይ የኢራን ጦር የጥቃቱን ሁኔታ መረጃ እስኪያወጣ ብዙ ነገር አልልም ግን በፍቅር ተወዳጅተው መኖር ከሚፈልጓት እስራኤል ጋር ፍልስጤምንም ሰጥተው ቢሆን የተረጋጋ የወዳጅነት ጊዜ እንዳያሳልፉ እንቅፋት ሆኖብናል ብለው የሚያስቡት ይሄን ጠንካራ ሰው ስለሆነ እንደው በተወገደልን ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡
በሀኒዬህ መገደል መካከለኛው ምስራቅ ላይ ትልቅ ለውጥ እጠብቃለሁ ወይ ጦርነቱ በቶሎ ይቆማል ወይም የለየለት ግጭት ይነሳል፡፡
ሀኒዬህ እንደ አንድ ሙስሊም ሙጃሂድ በወባ ሳይሆን ቤተሰቡን ሁሉ አጥቶ ሶብር አድርጎ እየታገለ ሳለ ሸሂድ ሆኗል፡፡ ሐማስ እና ተቃውሞው የተገነቡት በእሱ አይደልም በማይቀለበስ አላማ መሪ በማይጠፋበት ልክ ነው፡፡ የህያ ሲንዋር እና መሀመድ ዴይፍ ጋዛ ውስጥ ምንም ሳይሆኑ ባሉበት ሁኔታ ሀኒዬህ የተገደለበት ክስተት ጥያቄ የሚያጭር ነው፡፡
የሙሐመድ ትውልድ
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
ummaabdurezak shared a
Translation is not possible.
♻🔻⚡🇵🇸🇮🇷🇸🇦 ከኢራን እስከ ኢራቅ ከዚያም እስከ ሳዑዲ ዑለሞች ለሚደርሰው ውዝግብ:-
በመጀመሪያ የፍልስጤም ነፃ መውጣትን የሚቃወም ሙስሊም የለም በሚለው እንስማማ በመቀጠል ሺዓዎች ያሉበትን የዲን ሁኔታ የማይታወቅ አድርጎ ማሰብ አያስፈልግም፡፡
🔸ፖለቲካውን ብቻ ልንገራችሁ...
ኢራቅ በምዕራባዊያን እየታገዘች ኢራንን ታጠቃ ነበር በዚህ ኢራቅ እና ሳዳም ልክ ናቸው የሚል ካለ ሳዳም አረብ ሀገራትን ሊቆጣጠር ጉዞ ሲጀምር ካዕባ ላይ አደጋ ሲደቅንም በተመሳሳይ መርህ የኩዌትን መወረር እና የሳዳምን ሳዑዲንም ጭምር የመቆጣጠር ፍላጎት መደገፍ ነው ግን ሳዳም በአረቦች እና ምዕራባዊያን ሲወገድ ኢራቅ ላይ የኢራን የበላይነት ነግሷል፡፡
በፍልስጤም ጉዳይ በከፍተኛ ሁኔታ ኃላፊነታቸውን የተወጡት እስራኤል ወገኖቻችንን ጨረሰቻቸው ብለው አንድ ጥይት ወደ እስራኤል የተኮሱት ናቸው እነዚህም ሊባኖስ፣ የመን፣ ኢራቅ እና ኢራን ናቸው፡፡ ከዚህ በመቀጠል ኃላፊነታቸውን የተወጡት የዲፕሎማሲ ጥረት እደረጉ ያሉት ናቸው አነዚህም ኢራን ቱርክ ሳዑዲ ኳታር አልጄሪያ ቻይና ሩሲያ እንዲሁም ብዙ የደቡብ አሜሪካ ሀገራት ናቸው፡፡
ኢራቅ ኩዌትን ስታጠቃ ኩዌት ነፃ የወጣችው እና አረብ ሀገራት ከመወረር የዳኑት በአሜሪካ መራሹ የጦር ጥምረት ታግዘው ብቻ ሳይሆን ብቻውን የኢራቅን ጦር አስወጥቶላቸው ኢራቅንም አፍርሶላቸው ነው ስለዚህ ሙስሊም ባልሆነ አካልም መታገዝ ይቻላል፡፡ ኢራን በሶሪያ እና ኢራቅ በርካታ ሱኒዎችን በሀገሯም ጭምር ጨፍጭፋለች የሚል ብዙ መረጃ አለ ይህ ከምዕራባዊያን የሚወጣ ስለሆነ በጥንቃቄ ማየት ይፈልጋል ምክንያም በርካታ ንፁሀንን በመካከለኛው ምስራቅ የገደሉት ISIS እና ሌሎች አሸባሪ ደርጅቶች ናቸው እነዚህ ደግሞ በዋናነት በአሜሪካ የሚደገፉ ናቸው፡፡
ኢራን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ መሰረቷ እስራኤል የምትባል ሀገር የለችም የሚል እና ፍልስጤምን በማፅናት ላይ መሰረቱን ያደረገ ነው፡፡ ፍልስጤማዊያን በሙሉ ሱኒ ሆነው በዚህ ልክ ብሔራዊ ደህንነቷ አደጋ ውስጥ ገብቶ ከሩሲያ ቀጥሎ በዓለም ከፍተኛው ማዕቀብ የተጣለባት ሀገር እስክትሆን ድረስ ፍልስጤማዊያንን እየደገፈች የመቀጠሏ እና እስራኤልን የመጥላቷ ምክንያት የፍልስጤማዊያንን ነፃነት መፈለጓ እና እስራኤል ለብሔራዊ ደህንነቴ ስጋት ናት ብላ ማሰቧ ነው፡፡
ሳዑዲ አረቢያ ካላት የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ተፅእኖ አንፃር ብዙ አላደረገችም በሚል እንጂ ያን ያህል በዘመቻ ልትሰደብ የሚገባት ሀገር አይደለችም፡፡ ከእስራኤል ጋር የጀመረችው የእርቅ ሂደት እንዳለ ሆኖ ቢያንስ እስካሁን ይፋዊ ወዳጅነት ያልመሰረተች ሀገር ነች ለዚህ የቀደሙ ንጉሶቿን እና ዑለማዎቿን ማክበር ግድ ነው አሁንም መንግስታዊ አስተዳደሩ በተለይም በየመን የውስጥ ጉዳይ ገብቶ የፈጠረው የንፁሀን ስቃይ ከባድ ቢሆንም ከአረቡ ዓለም በተሸለ በኢስላማዊ መርህ የቆመች የተረጋጋች እና ጠንካራ ሀገር ነች ፍልስጤማያንንም በተለይም በኢኮኖሚ እና ሲቪል አስተዳደሩን በመደገፍ ትልቅ ሚና አላት፡፡
ባለንበት ዘመን የእስራኤል ፍልስጤም ጉዳይ በመካከለኛው ምስራቅ እና በቀጣዩ አዲሱ የዓለም ስርዓት ላይ እጅግ ወሳኝ የሆነ ሀይማታዊ ስርዓትን በመጠበቅ እና ኃይማኖት አልባ ዓለም በመፍጠር መካከል የሚደረገው ዘላለማዊ ትግል መነሻ ጉዳይ ነው፡፡ እስራኤል ፈጣሪ የለም ብሎ በሚያምነው ቴዎዶር ሄርዝል የተፀነሰች የኢ-አማንያን መነሻ ስትሆን ፍልስጤም ደግሞ በምድር ላይ ካሉት ኃይማኖታዊ ቅሪቶች ውስጥ እጅግ ጥንታዊውን ትልቅ ተአምር የያዘውን አለ አቅሳ የያዘች ቀደምት የኃይማኖት ፋና ነች፡፡
ሳዑዲ ግብፅ ኩዌት እና ሌሎችም ከኢራን ጋር የተሸለ ግንኙነት ጀምረው መካከለኛው ምስራቅ ላይ በትብብር ለመስራት ጥረት እያደረጉ ባለበት በዚህ ጊዜ ፍልስጤማዊያን በኢስላምም በሞራልም የመዋጋት ፍፁም መብትን በተሰጣቸው የጽዮናዊያን ህዝብ ጋር በሚያደርጉት ትግል በኢራንም ሆነ በማንኛውም የእነሱን ዓላማ በሚደግፍ ወይም ለራሱ ጥቅም ሲል እነሱን በሚደግፍ ሀገር ቢታገዙ ምክንያታዊ ፖለቲካ ነው፡፡ አሜሪካ ፍልስጤምን ብትደግፍ ማንም ሙስሊም ሊቃወም አይችልም አሜሪካ ከያዘችው ዘግናኝ ፈሳድ ጋር፣ ኢራንም ፍልስጤማዊያንን ሺዓ ሁኑ ሳትል መደገፍ ከፈለገች ፍልስጤማዊያን በኢራን ቢታገዙ የሚከለክል ነገር የለም፡፡
አሁን ባለው ዓለም የፖለቲካ አሰላለፍ አረቦች በዲፕሎማሲም ሆነ ተዋግተው ፍልስጤምን ነጻ አያወጡም፡፡ ስለዚህ ፍልስጤማዊያንን ከማለቃቸው በፊት ኢስላማዊ ኃይማኖታቸውን አክብሮ ለራሱ ስትራቴጂክ ጥቅምም ሆን ለእነሱ ብቻ ብሎ ከሚያግዛቸው አካል ጋር መተባበር አለባቸው፡፡
የመጀመሪያ እውነት በአይናችሁ ያያችሁት ነው፡፡ ፍልስጤማዊያን ሀገራቸውን ላለማጣት እየታገሉ ነው ኢራን ይሄን እየደገፈቻቸው ነው፡፡ ሳዑዲ ብዙ እንድታደርግ ይጠበቃል ግን ሀገሪቱን መሪዎቿን ይባስ ብሎ ዑለማዎቿን መሳደብም ሆነ ክብር መንካት በፍፁም በፍፁም አደገኛ አካሄድ ነው፡፡
ቴሌግራም https://t.me/Alif_Online_Official ላይ ጆይን በማድረግ ወቅታዊ መረጃን ተከታተሉ
Telegram: Contact @Alif_Online_Official
t.me

Telegram: Contact @Alif_Online_Official

✍️Daily Updates, detailed analysis and informed openions focusing on Ethiopia, Middle East and beyond✈️?
Send as a message
Share on my page
Share in the group