Ashreka kemal Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Ashreka kemal shared a
Translation is not possible.

የታሉ እነዛ ሙስሊሞች

━━━━━━✦✿✦━━━━━━

#አስራ_አምስት_ሺ_ከፈን_የለበሱ_ሰራዊቶች

━━━━━━✦✿✦━━━━━━

ዘመኑ እንደ ሂጅራ አቆጣጠር በ463 ዓመት የተከሰተ ነው። የምስራቅ ሮማ ባይዛንታይን ኢምፓየር የሙስሊም ግዛቶችን ለመቆጣጠር በተደጋጋሚ የፈፀመው ወረራ በሰልጁቅ ቱርኮች እየተደመሰሰ ግዛቱን መነጠቅ ጀመረ። ሮማኖስ ዳዮጌኔስ ወደ ስልጣን መጣ። ሮማኖስ ከሙስሊሞች ጋር የገባውን የሰላም ስምምነትን ለማደስ ለሙሐመድ አልብ አርስላን ልዑካንን ላከ። ሮማኖስ ይህን ያደረገው የሙስሊሞቹን የሰልጁቅ ቱርክ ጦር ለማዘናጋት ነበር።

ይህንን የሰላም ስምምነት በማድረጉ አልብ አርሰላን ፊቱን ወደ ግብፅ አዞረ። የሺዓ ኸላፋ የነበረውን የግብፁን ፋጢሚድ ዳይናስቲ ለመደምሰስ ጦሩን ይዞ ጉዞውን ወደ ሶሪያ አቅጣጫ አመራ። በሺዓው ፋጢሚድ ስር የነበረችውን ሐለብን ነፃ አወጥቶ በሐለብ ጦሩን አሳረፈ።

ሮማኖስ ባይዛንታይን 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ጦሩን አስከትሎ የሙስሊሞችን ሀገር ኢራቅን፣ ኢራንንና ሶሪያን ጨምሮ አብዛኛውን የሙስሊም ግዛት ለመቆጣጠር ወደ ምስራቅ ተመመ። የባይዛንታይ የዘመቻ እንቅስቃሴ ለአልብ አርሰላን ደረሰው። ከፋጢሚዮች ጋር ሊያደርግ የነበረውን ጦርነት ትቶ ወደ ምስራቅ ኢፍራጠስ ወንዝ ጦሩን አዞረ።

ታላቁ የሙጃሒዶች መሪ አልብ አርስላን ጥቂት ቁጥር ያለውን ጦሩን ከ300,000 የባይዛንታይን ሮም ሰራዊት ጋር ይዋጋ ዘንድ ለጂሃድ አዘጋጀ።

ቀኑ ጁሙዐ ነበር። ታላቁ ኢማም አቡነስር ሙሀመድ ኢብን አብዱልመሊክ አልቡኻሪ ከሚንበር ላይ ወጡ ስለ ጂሃድ ኹጥባ አደረጉ። ሙጃሒድ አላህ ዘንድ ያለውን ደረጃ፣ ሸሂዶች ከአላህ ዘንድ ያላቸውን ምንዳ አወሱ። ስለኢስላም ተጋደሉ አላህም ሊረዳችሁ ቃል ገብቷል አሏቸው። አላህ የድል ባለቤት እንዲያደርጋቸውም ዱዓ አደረጉላቸው። ሁኔታው ሁሉ የሰሐቦች ዘመን ይመስላል። እነዚያ 15,000 የአላህ ሙጃሂዶች በእርሱ መንገድ ሸሂድ ሊሆኑ ጓጉተዋል።

ሱልጣን ሙሐመድ አልብ አርስላን ከፈኑን ለብሶ ወጣ። ወደ እነዚያ የአላህ ሙጃሂዶች ፊቱን አዙሮ "ዋ ኢስላማ! ዛሬ እስልምና አደጋ ላይ ወድቋል! ላኢላሀኢለሏህ ከምድር ገፅ ላይ እንዳትጠፋ እፈራለሁ እኔን የሚመስል ይከተለኝ" አላቸውና ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ሁሉም በእንባ ተራጩ

"በአላህ መንገድ ሸሂድ መሆን የፈለገ ብቻ ይከተለኝ" አላቸው እኔ ዛሬ የእናንተ አዛዥ አይደለሁም። ስለአላህ ዲን መዋጋት ግዴታ የተደረገው በኔ ላይ ብቻ አይደለም በሁላችንም እንጂ ስለአላህ ዲን በማገልገል ላይ ሁላችንም እኩል ነን። ለህይወቱ ቅንጣት ታክል የሚፈራ ካለ አይከተለኝ። ነፃነቱን ሰጥቼዋለሁና መመለስ ይችላል። እኔ ሸሂድነትን ናፍቄያለሁ ከሞትኩ በዚህ በያዝኩት ከፈን ቅበሩኝና በአላህ መንገድ መዋጋታችሁን ቀጥሉ። እኔ በጦርነቱ ስሰዋ ልጄ መሊክሻህ የጦር አመራርነቱን ይረከብ" አላቸው። ሁሉም በእንባ ተራጩ በተክቢራ ድምፅ ምድር ተናወጠች።

አስራ አምስር ሺህ ሰራዊት ከፈኑን ለበሰ። ከ300,000 መስቀላዊያንን ሊገጥም ወደ ማንዚከርት (መላዝከርድ) መ ዳ ተጓዘ።

300,000 የሚሆነው የሮም ሰራዊት የተውጣጣው ከሩሲያ፣ ከኡጉዝ፣ ከካውካሰስ፣ ከኻዛርስ፣ ፈረንሳይና ከአርሜኒያ ሲሆን የአልብ አርስላን ጦር ግን 4,000 ልዩ ጦር እና 11,000 ተራ ጦር ሲሆን ሁሉም ቱርካዊያን ናቸው ።

#የጦርነቱ_ፍልሚያ

የሱልጣኑ ሰላዮች የሮማኖስ ጦር ያለበትን ቦታ ብዛቱን አጠቃላይ እንቅስቃሴውን በሚገባ አውቀዋል። ሮማኖስ ጦሩን በአህላድ እና ማንዚክርት መካከል በሚገኝ አል-ራህዋ በሚባል ቦታ አሰፈረ። የሱልጣኑ ጦር ወደ እርሱ እያመራ መሆኑን አላወቀም።

ሮማኖስ በ ጄኔራሉ የሚመራ 60,000 ጦር ቀድሞ ያጠቃ ዘንድ አዘዘ። ሱልጣን አልብ አርስላን ይህንን ያውቅ ነበርና ለጄነራሉ ወጥመድ አዘጋጅቶ ጠበቀው። ከዚያ በኋላ ስልሳ ሺህ ጦር በተዘጋለት ወጥመድ ገብቶ ሁሉም አለቁ። ጄኔራሉም ተማረከ። ይህ ሁሉ ሲሆን ንጉስ ሮማኖስ ምንም የደረሰው መረጃ አልነበረም።

ቀሪ 240,000 ሰራዊቱን ይዞ በማንዚክሪት 15,000 ከያዘው የአልብ አርስላን ጦር ጋር ተጋጠመ። አልብ አርስላንም ጦሩን ከፊት እየመራ በጀግንነት ተጋደለ። ሰልጁቆች እጅግ የሚታወቁበትን የቱርክ የጦር ስልት መጠቀም ጀመሩ።

የተወሰኑ የቱርክ ተዋጊዎች ወደ ጦርነቱ ይዘልቁና ከዚያ ወደኋላ ያፈገፍጋሉ በዚህ ጊዜ ባይዛንታይኖች ቱርኮቹ አፈገፈጉ ብለው ስለሚያስቡ ይከተሏቸዋል። ነገር ግን ቱርኮቹ አብዛኛውን ጦራቸውን ከጦር ሜዳው ቅርብ ላይ ነው ደብቀው የሚያስቀምጡት። የሮም ባይዛንታይን ጦር ግዙፍና በመሳሪያም የተደራጀ ስለሆነ በፍጥነት ደርሶ የሚያፈገፍጉትን ሙስሊሞች ሊወጋቸው ይቸገራል። በዚህ መሀል የተደበቀው የሙስሊም ጦር ይወጣና በቀስትና በጦር ግዙፉን የሮም ጦር ደመሰሰው።

እንደዚህ እያደረጉ 15,000 ሰራዊቶች 300,000 የሚሆነው የሮም ክርስቲያን ሰራዊት ደመሰሱት ። ሙስሊሞችን ከምድር ገፅ ሊያጠፋ የዛተው ሮማኖስም ተማረከ።

ላኢላሀ ኢለላህን ለመታደግ ከፈኑን ለብሶ የወጣው እጅግ አነስተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት ከእርሱ በ20 እጥፍ የሚበልጠውን የጠላት ሰራዊት ደመሰሰ።

ከድሉ በኋላ የሙስሊሞች ታላቁ ኸላፋ ለአልብ አርስላን "የዐረቡም የአጀሙም ታላቁ ሱልጣን" ሲል አድናቆቱንና ለኢስላምም ለሰራው ገድል ምስጋናውን ላከለት።

ኢምፔሬር ሮማኖስ ተማርኮ ከሱልጣኑ ፊት ቀረበ። ሱልጣን አልብ አርስላን ለሮማኖስ "የተማረኩት እኔ የማረከኝ ደግሞ አንተ ሆነህ ቢሆን ምን ታደርገኝ ነበር?" ሲል ጠየቀው።

ሮማኖስም "ወይ እገድልሀለሁ ያ ካልሆነ እየጎተትኩህ በኮንስታንትኖፕል ጎዳናዎች ላይ እያስዞርኩ መሳቂያ መሳለቂያ አደርግሃለሁ" አለው። በዚህ ጊዜ ሱልጣኑ ለሮማኖስ "አሁን እኔን ምን ያደርገኛል ብለህ ታስባለህ?" ሲል ዳግም ጠየቀው። ሮማኖስም "ሶስት አማራጮች አሉህ አንደኛው ትገድለኛለህ ሁለተኛው ደግሞ በሀገርህ እያዞርክ የድልህ ማንፀባረቂያ ታደርገኛለህ። ሶስተኛውን ይቅር ብለከኝ ካሳዬንም ትቀበለኛለህ" አለው።

ሱልጧን አልብ አርስላን ሶስተኛውን ይቅር ብዬሀለሁ አለው።

1.5 ሚሊዮን ዲናር ካሳ ሊከፍል ተስማምተው ሮማኖስ ወደ ኮንስታንትኖፕል ተመለሰ። እዚያ ሲደርስ የባይዛንታይን መሪዎች ከስልጣኑ አውርደው ዓይኑን አጠፉት። ሮማኖስ የእስልምናን መሀሪነት አዛኝነት እና ይቅር ባይነት ይዞ ለሮሞችም ሊነግራቸው ቢቋምጥም አልፈቀዱለትም።

ሮማኖስ ያን የተስማማውን የካሳ ክፍያ ማግኘትም አልቻለም። ለአልብ አርስላንም ደብዳቤ ላከለት "ኢምፔሬር በነበርኩበት ጊዜ የ 1.5 ሚሊዮን ዲናር ካሳ ተስማምቼ ነበር። ግና ከስልጣኔ ተባረርኩ። የሌሎች ጥገኛም ሆንኩ። ለምስጋና ያክል ብቻ እንደምንም ያሰባሰብኳትን ልኬልሃለሁ" በማለት።

ሮማኖስ በጊዜው ለካሳ የላከው 300,000 ዲናር ብቻ ነበር።

━━━━━✦✿✦━━━━━

💎💎አላማችን 💎💎

#የላኢላሃ_ኢለሏህ_ባንዲራን_ከፍ_ማድረግ_ነው።

#ሼር_በማድረግ_ለወዳጅ_ዘመድዎ_ያዳርሱ።

ከማይቋረጠው አጅር ተካፋይ ይሁኑ

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

#ኢኽላስ - #ታማኝነት - #ትጋት - #ስኬት

#zubeyr379

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Ashreka kemal shared a
Translation is not possible.

ፍላጎታቹ እንዲሳካ ከፈለጋቹ...

{ قَدْ أَفْلَحَ الْمُؤْمِنُونَ (١)الَّذِينَ هُمْ فِي صَلاتِهِمْ خَاشِعُونَ (٢)}

“ምዕመናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)፡፡ እነዚያም እነሱ በስግደታቸው ውስጥ (አላህን) ፈሪዎች፡፡” [አል-ሙዕሚን፡ 1-2]

በሰላታቹ ላይ አላህን ፍሩ! ወቅቱን ጠብቃቹ ስገድ፣ መስፈርቶችን አሟሉ፣ ዘውታሪ ሁን!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Ashreka kemal shared a
Translation is not possible.

ይህ ልጅ ከጠፋ 10 ወር አለፈው

ለአሏህ ብላችሁ ሼር አድርጉት አፋልጓቸው !

መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!

የ umma life ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇

https://ummalife.com/post/164424

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Ashreka kemal shared a
Translation is not possible.

4 views
1 view
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Ashreka kemal shared a
Translation is not possible.

አል-ካቡስ"

ይህ በእንቅልፍህ ጊዜ የሚያጠቃህ "አል-ካቡስ" የተባለ ልዩ ጂን ነው።

የጥቃቱ ምልክቶች አንድ ሰው በእንቅልፍ ላይ እያለ ደረቱ ላይ ከባድ ነገር

መጫን ፣እግርን ቆላልፎ አካሉን ጨምቆ በመያዝ እና ትንፋሹን በመገደብ

መናገር መጮኽ እና መንቀሳቀስ እንዳይቺል ያደርጋል

ይህ ጂን ከላይህ ላይ ከሄደ በኋላ ወዲያውኑ በድንጋጤ ትነቃለህ።

የምዕራባውያን ሳይንቲስቶች ይህንን ክስተት "የእንቅልፍ ሽባነት" ብለው

ይጠሩታል።

ነገር ግን እስልምና ሰዎችን በእንቅልፍ ወቅት የሚያጠቃ ጂን እንደሆነ

ይነግረናል .....

አንድ ሰው ሰይጣን ይተኛል ወይ በማለት ስለ ሰይጣን መተኛት በየትኛው

ኢስላማዊ ወጎች ውስጥ ተጠቅሷል ብሎ አንድ አሊምን ጠየቀ ? .......

አሊሙም ፈገግ አሉና “ያ የተረገመ ፍጡር ተኝቶ ቢሆን ኖሮ ትንሽ ፋታ አግኝቼ

ነበር!” በማለት መልስ ሰጡ።

ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-ወደ መኝታ ስትሄድ ሰይጣን

ጭልጥ ያለ እንቅልፍ እንድትተኛ ከራስህ ጀርባ ሶስት ቋጠሮዎችን ይቋጥራል

።በእያንዳንዱ ቋጠሮ ላይ የተለያዩ ቃላትን እያነበነበ ይተነፍሳል...

⇨1.ኛው ቋጠሮ ከእንቅልፍህ ስትነቃ ይበጠሳል

⇨2.ኛው ቋጠሮ ወዱእ ስታደርግ ይበጠሳል

⇨3.ኛው ቋጠሮ ስትሰግድ ይበጠሳል

በተለይ ለሱብሂ ሰላት ንቁ እንዳትሆን ወደተሻለ የእንቅልፍ ደረጃ ያሸጋግራል

፣ይህ ከሰይጣን መሆኑን እወቅ።

በእንቅልፍ ወቅት ሰይጣን በጆሮዎችህ ውስሕ ሽንቱን ይሸናል።

ሰይጣን በአፍንጫህ ያድራል ፣በእንቅልፍ ውስጥ ጥቁር ውሻ ካየህ ሰይጣን

መሆኑን እወቅ።

በቤትህ ወይም በክፍልህ ውስጥ መኖሩን አታውቀውም በተለይ በእንቅልፍ

ውስጥ የግብረ ሥጋ ግንኙነት እንትፈጽም ያደርግሀል!! ከዛ የሱብሂ ሰላትን

ይከለክልሀል

ሰይጣን አይተኛም አንተ በምትተኛበት ጊዜ የተረገመው ሰይጣን ሙሉ በሙሉ

ንቁ ሆኖ ይጠብቅሀል። በጭራሽ አይተኛም።እርሱ ሁል ጊዜ ሰዎችን ይጠብቃል

እነሱን ለመጉዳት እድሎችን ይፈልጋል።

ታዲያ እራሳችንን ከዚህ ጂን እንዴት እንከላከል? በሱና ተኛ

ከመኝታ በፊት ዉዱእ አድርግ ከዛም የወዱእ ሱና ስገድ፡-

ወደ አልጋህ ከመውጣትህ በፊት የምትተኛበትን ቦታ በጨርቅ ፣ወይም

በምትለብሰው ልብስ አልያም በእጅህ ሶስት ጊዜ ወደ ግራ አራግፍ ....

ይህ ጂኑ በምትተኛበት ቦታ ላይ ቀድሞህ ስለሚቀመጥ ከክፍልህ ወይም

ከቤትህ እንዲወጣ ያደርገዋል ።ከዚያም ወደምትተኛበት ቦታ በፍጥነት

ተቀመጥ። ከመተኛትህ በፊት......

✯ ሱራ ኢኽላስን

✯ ሱራ አል-ፈለቅ እና

✯ ሱራ አን-ናስን ማለትም

⇨ቁልያ አዩኽል ካፊሩን 3 × ጊዜ

⇨ቁልሁ ወላሁ አሀድ 3 ×ጊዜ

⇨ቁል አኡዙ ቢረቢናስ 3 × ጊዜ ቅራ

✪ከቻልክ አያተል ኩርሲይን አስከትል

ከቀራህ በኋላ በመዳፎችህ ላይ ሶስት፣ሶስት ጊዜ ትፍ፣ትፍ አድርገህ፣ ከአናትህ

በስተኋላ ጀምረህ እጅህ መድረስ እስከሚችለው ቦታ መላ ሰውነትህን ዳብስ

በመቀጠል.... ➽ ሱብሃነላህ 33 ጊዜ

➽ አልሀምዱሊላህ 33 ጊዜ

➽ አላሁ አክበርን 34 ጊዜ ዚክር አድርግ ።

ከዛ ለሌሎች እንዲደርስ ሼር አድርገው

አላህ ሁላችንንም ከጂን ይጠብቀን። አሚን

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group