Translation is not possible.
አንድ የመኪና አምራች ካምፓኒ የተለያዩ የመኪና ሞዴሎቹ ላይ እንደየምርት አመታቸው የተለያዩ ፊቸሮችን ይገጥማል ።የተለያዩ ማንዋሎችንም ያዘጋጃል።ማንም ሰው ተነስቶ ለምን ተለያዩ? ሁሉም ሞዴል እኩል ናቸው!  ወይም ሁሉንም በአንድ መመሪያ አሽከረክራለሁ ወዘተ ብሎ  የሚቃወም ሰው የለም።
ለምን? ከተባለ መብት ስለሌለው። በመኪናዎቹ ላይ ብቸኛ መብት ያለው አምራቻቸው ነው።የራሱ ምክንያትና ጥበብ አለው። ለአእምሮ ቀረብ ለማድረግ እንጅ ለአላህ የላቀ ምሳሌ አለው! 
አላህ የፍጡራኑ ሁሉ ፈጣሪና መራጭ ነው። ከየፍጡራኑ ሁለት አይነት ፆታ ሲፈጥር የሚገባውን መብትና ግዴታም አስቀምጧል። ስለ አፈጣጠራችን ጥበብ ብቸኛ እውቀት ያለው እርሱ ስለሆነ ወንድ ምን መብት ምን ግዴታ ሴት ምን መብት ምን ግዴታ እንዳላቸው ደንግጓል። ከዚያ በኋላ  ማንም ተነስቶ የፆታ እኩልነት ብሎ መስበክ አይችልም።አላህ ፆታዎችን እኩል አላደረገምና። በኢስላም ወደ ፆታ እኩልነት መጣራትም ክህ  ደት ነው።
ለምሳሌ ሴትን ልጅ የቤት አስተዳዳሪነትን ግዴታ አልጫነባትም። ወንዱ ላይ ደግሞ ሰርቶ ለፍቶ ቤቱን እንዲያስተዳድር ዋጂብ አድርጎበታል።ሴቷን ደግሞ ቤቷ ቁጭ ብላ እንድትኻደም ወሰነላት። ቀበሮዎቹ ታዲያ ቤቷ ቁጭ ብላ በባሏ መኻደሟን ተመቀኙና ነይ ውጪ ከወንድ ጋር እኩል ነሽ ብለው ጠሯት። ስለ ፌሚኒዝም እያወጋን ነው ...
የቴሌግራም ቻናል 👉https://t.me/IbnuibrahimOfficial
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group