🔴ከጎረቤታችን የኬንያ ሙስሊሞች ምን እንማራለን…?
🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰
♣️ እንደ ኬንያ ማእከላዊ ስታትስቲክስ መረጃ የኬንያ ሙስሊሞች ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ህዝብ 11 % ያክል ይሸፍናሉ። ያ ማለት 5 ሚሊዮን አካባቢ ይሆናሉ ማለት ነው። ያ ማለት የሶማሌ ሙስሊሞች ከኬንያ አጠቃላይ የሙስሊሞች ብዛት ይበልጣል ማለት ነው ። INSAMER የተሰኘ ተቋም ይፋ ባደረገው አሃዝ ደግሞ የኬንያ ሙስሊሞች ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ህዝብ ከ 25-30% ይሸፍናሉ። ያ ማለት ከ 12 - 14ሚሊዮን ህዝብ ማለት ነው።
በከፍተኛው አሃዝ ወስደን ብናሰላው እንኳ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ብዛት ከኬንያ ሙስሊሞች በ 5 እጥፍ ገደማ ይልቃል!
ነገር ግን
♣️ የኬንያ ሙስሊሞች ሁለት ታላላቅ አለምአቀፍ ኢስላማዊ ዩኒቨርስቲዎች አሏቸው ። RAF international universty እና Umma University የሚባሉ ሁለት ግዙፍ ዩኒቨርስቲዎች እና የምርምር ማእከሎች! ነገር ግን ከ 50 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ምንም አይነት ዩኒቨርስቲም ሆነ ዪኒቨርስቲ ኮሌጆች የላቸውም!
♣️ የኬንያ ሙስሊሞች በርካታ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንድሁም ኮሌጆች ሲኖሯቸው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ግን ያሏቸው በጣት የሚቆጠሩ የኢለመንታሪ ትምህርት ቤቶች ብቻ ነው ።
♣️ የኬንያ ሙስሊሞች በፖለቲካ ተሳትፏቸውም ከኢትዮጵያዊያን በጣም የተሻለ ነው ። ከየትኛውም ማህበረሰቦች በላይ የኬንያ ሙስሊሞች በጣም ጠንካራ በጣምም ተፅእኖ ፈጣሪዎች ናቸው ። 222 መቀመጫ ካለው የኬንያ ፓርላማ 32 ቱ ሙስሊሞች ናቸው። ሚስሊሞች በኬንያ በጣም ስትራቴጂካዊ አካባቢዎችን የያዙ ሲሆን እነ ሞንባሳ ፣ ላሙ ወዘተ በመሳሰሉ የወደብ ከተሞች ላይ የሚኖሩት በአብዛኛው ሙስሊሞች እንደመሆናቸው በሀገሪቱ ፖለቲኮ-ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ያላቸው ተፅእኖ ከፍተኛ ነው።
♣️ የኬንያ ሙስሊሞች ራሳቸውን በከፍተኛ ልእልና ነው የሚያዩት ። በኬኒያዊያን ዘንድ ሙስሊምነት ማለት ስልጡንነት አዋቂነት እና በማህበራዊ አስተሳሰብ ላቅ ማለት ነው ። ራሳቸውንም የኬንያ ባለቤት አድርገው ነው የሚያዩት ። በርካታ የታሪክ አሻራዎችና ረጅም ዘመን የመሪነት ታሪክም አላቸው ። ኬንያዊያን ሙስሊሞች አለምአቀፋዊ ንቃተ ህሊናቸውም በጣም ከፍ ያለ ነው።
♣️ ኬኒያዊያን ሙስሊሞች ከራሳቸው አልፈው ስለመላው ሙስሊሞች ሁኔታ የሚያጠና የሚከታተል ታላቅ የሚዲያ ተቋም አላቸው ። የሚዲያ ግሩፑም ISLAM AND MEDIA WORKING GROUP ( #iamcr ) ይሰኛል። ይህ ድርጅት በአለም አቀፍ ደረጃ በመላው ሙስሊሞች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን ይከታተላል ፣ ጥልቅ ምርምሮችን ያደርጋል የመፍትሔ አቅጣጫዎችንም ያስቀምጣል። ይህ ተቋም በተለያዩ የሙስሊሙ አለም ክፍሎች የሚገኙ ምሁራንን ስለ ኢስላማዊ አለም የሚዲያ እና ግንኙነት እንቅስቃሴ በአንድ በመሰባሰብ እንዲያጠኑና የመፍትሔ አቅጣጫ እንዲያስቀምጡ በከፍተኛ ሁኔታ ያበረታታል። በአንፃሩ የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች አንድም ጠንካራ ሚዲያ (Mainstream media ) የላቸውም ። ይህ አሳፋሪ ነው።
♣️ ኬንያዊያን በአንድ ጥላ ስር የሚያሰባስባቸው ፤ ፊርቃና መዝሃብ ሳይለይ እንደ ጃንጥላ ከለላ የሚሆናቸው የእስልምና ተቋም አላቸው ። ለኬንያዊያኑ ስድብ አይሁንብኝና እኛ መጅሊስ እንደምንለው ማለት ነው ። ያ የሀይማኖታቸው ከፍተኛ ተቋም Supreme council pf Kenya Muslims ( #supkem ) ይሰኛል። ይህ የሃይማኖት ተቋም በኬንያ ሙስሊሞች ከፍተኛው የስልጣን ባለቤት ነው ። ከፈትዋ ጀምሮ የተለያዩ ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴዎችን ከፖለቲካዊ እስከ ኢኮኖሚያዊ ከዚያም እስከ ማህበራዊ ዘርፎች የሙስሊሞችን እጣፈንታ ይወስናል። የራሱ ፍርድ ቤት አለው ። አንድ ሰው ሙስሊም እስከሆነ ድረስ ጉዳዩ የሚታየው በሼሪአ ፍርድ ቤት በኩል ነው ።
ዋና ቃዲና የኢስላማዊው ካውንስል ፕሬዝዳንት ስልጣናቸው ከሙስሊሞችም ይሻገራል ። የሙስሊሞች ካውንስል ፕሬዝዳንቱ የኬንያን ፕሬዝዳንት የማማከር ስልጣንም አላቸው ወይም የኬንያ ፕሬዝዳንት አማካሪ ናቸው ።
♣️ በዚህም የኬንያ መንግስት ከሙስሊሞች ጋር ሊኖረው የሚገባውን ግንኙነት ያማክራሉ ፤ የሙስሊሞችን ጥያቄ ፍላጎት ለመሪው በቀጥታ ይነግራሉ በአጠቃላይ እጅግ ከፍተኛ ስልጣን አላቸው።