UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

#ታላቁ_ቀን_ጁምዓ!

ረሱል ‏(ﷺ) እንዲህ ይላሉ፦

﴿خَيْرُ يَومٍ طَلَعَتْ عليه الشَّمْسُ يَوْمُ الجُمُعَةِ، فيه خُلِقَ آدَمُ، وفيهِ أُدْخِلَ الجَنَّةَ، وفيهِ أُخْرِجَ مِنْها، ولا تَقُومُ السّاعَةُ إلّا في يَومِ الجُمُعَةِ﴾

“ፀሀይ ከወጣችባቸው ጥሩ ‘የጁምዓ ቀን’ ነው።

➜ አደም የተፈጠረበት ነው።

➜ ወደ ጀነት የገባበት ነው።

➜ ከሷም ከጀነት የወጣበት ነው።

የትንሳዔ ቀንም በጁምዓ ቀን ቢሆን እንጂ አትቆምም።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: ‍854

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🚨የአል-ቃሳም ብርጌድ ወታደራዊ ቃል አቀባይ አቡ ዑበይዳ ሳምንታዊ መግለጫ፡-

🔹ባለፈው ሳምንት የአልቃሳም ተዋጊዎች 68 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ማውደም ችለዋል።

🔹የእኛ ተዋጊዎች በተለያዩ ዘመቻዎች 53 የጽዮናውያን ወታደሮችን ከቅርብ ርቀት መግደል ሲችሉ ተጨማሪ 9 ወታደሮችን በጥይት በመምታት ገድለዋል፣ ሌሎች በደርዘን የሚቆጠሩ ወታደሮች ሙት እና ቁስለኛ መካከል እንዲሆኑ አድርገዋል።

🔹በአንድ ሳምንት 57 የተለያዩ ወታደራዊ ተልዕኮዎች ፈፅመናል እነዚህ ተልእኮዎች ጥይቶችን ፀረ-ምሽግ እና ፀረ-ሰው ፈንጂዎችን እንዲሁም መትረየስ በመጠቀም ሰርጎ ገብ የሆኑትን የጽዮናውያን ሃይሎችን ኢላማ አድርገዋል።

🔹በተጨማሪም 4 ቤቶችን በጠላት ጦር ላይ ማፍረስ፣ የሁለት ዋሻዎች መግቢያ እና ፈንጂ የተጠመደበትን ቦታ በጠላት ወታደሮች ላይ ማፈንዳት፣ ሁለት "ስካይ ላርክ" የስለላ ሰው አልባ አውሮፕላኖች መምታት፣ 8 ድሮኖች 2 አጥፍቶ ጠፊ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ጨምሮ መቆጣጠር ይዘዋል፡፡

🔹የጠላት ወታደራዊ ስብስቦችን በሞርታር መሳሪያ እና በአጭር ርቀት ሚሳኤሎች በሁሉም የውጊያ ግንባሮች ደብድበናል እንዲሁም የተለያዩ የሮኬት ጥቃቶችን ወደ ጽዮናዊው አካል ሰንዝረናል፡፡

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

በቁርኣን አንዱ በሌላው ላይ ድምፅን ከፍ ማድረግ

~

ሶላት ስንሰግድ አጠገባችን ሌላ ሰጋጅ ካለ እንዳንወሰውስ ድምፃችንን ዝቅ ልናደርግ ይገባል። ልክ እንዲሁ መስጂድ ውስጥ - ለምሳሌ ጁሙዐ ቀን ሊሆን ይችላል - ቁርኣን ስንቀራ ሌሎችን በሚረብሽ መጠን ድምፃችን ከፍ ያለ መሆን የለበትም። ነብያችን ﷺ በአንድ ወቅት ኢዕቲካፍ ላይ ነበሩ። ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚቀሩ ሰዎችን ሰሙ። መጋረጃቸውን ገለጥ አድርገው እንዲህ አሉ፦

أَلَا إِنَّ كُلَّكُمْ مُنَاجٍ رَبَّهُ، فَلَا يُؤْذِيَنَّ بَعْضُكُمْ بَعْضًا، وَلَا يَرْفَعْ بَعْضُكُمْ عَلَى بَعْضٍ فِي الْقِرَاءَةِ ، أَوْ قَالَ: فِي الصَّلَاةِ

"ንቁ! እያንዳንዳችሁ ከጌታው ጋር ነው እየተንሾካሾከ ያለው። ስለዚህ አንዳችሁ ሌላውን አያስቸግር። ከፊላችሁ በከፊሉ ላይ ቁርኣንን በመቅራት - ወይም በሶላት - አይጩህ።" [አቡ ዳውድ፡ 1332]

በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ እንዲህ ብለዋል፦

أما إن أحدكم إذا قام في الصلاة، فإنه يناجي ربه، فليعلم أحدكم ما يناجي ربه، ولا يجهر بعضكم على بعض بالقراءة في الصلاة

"አንዳችሁ ለሶላት ሲቆም ከጌታው ጋር ነው የሚንሾካሾከው። ስለሆነም ከጌታው ጋር የሚንሾካሾክበትን ይወቅ። ከፊላችሁ በከፊሉ ላይ በሶላት ውስጥ በቁርኣን አይጩህ።" [ሙስነድ አሕመድ፡ 11896]

ስለዚህ ሌሎች ሰጋጆች ባሉበት ጀማዐ ሶላት ላይ ያለፈንን ስንመልስ፣ ወይም ካጠገባችን ሌሎች ቁርኣን የሚቀሩ ሲኖሩ ድምፃችንን ዝቅ በማድረግ ልንቀራ ይገባል። ጁሙዐን እየጠበቁ በድምፅ ማጉያ ቁርኣንን ከመስጂድ መክፈትም እንዲሁ ተገቢ አይደለም።

ልክ እንዲሁ በየቤታችን ሆነን ሶላት የሚሰግድ ባለበት እየተንጫጩ ማውራትም የተለመደ ነው። ይህም መታረም ያለበት ነው። በቁርኣን አንዱ በሌላው ላይ እንዲጮህ ካልተፈቀደ በሌላ ወሬ፣ ያውም ሶላት ላይ ያለን አካል መወስወስ ግልፅ የሆነ ጥፋት ነው። ለሶላት ክብር ሊኖረን ይገባል። ልጆቻችንንም እንዲሁ አደብ ማስተማር አለብን።

Ibnu Munewor

=

* የቴሌግራም ቻናል

https://t.me/IbnuMunewor

* የዋትሳፕ ቻናል፦

https://whatsapp.com/channel/0....029VaA3X1e5kg7BlsJbo

* ፌስቡክ

https://www.facebook.com/Ibnu.....Munewor?mibextid=ZbW

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

    የሰው ልጅ

              ያለ ምንም ነገር ይመጣል:

ከዝያም

      ሁሉም ነገር ለማግኘት ሲል ይሮጣል:

ከዝያም

       ያለ ምንም ነገር ይሄዳል:

ከዝያም

      ስለ ሁሉም ነገር ይጠየቃል።

እቺ ናት ዱንያ!!

منقول

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

እግሮችን ወደ ቂብላ አቅጣጫ መዘርጋት

~

ከዑለማእ ውስጥ እግሮችን ወደ ቂብላ አቅጣጫ መዘርጋትን የተጠላ ነው ያሉ አሉ። ነገር ግን ይህንን የሚከለክል አንድም ማስረጃ የለም። ሸይኽ ኢብኑ ሑመይድ - ረሒመሁላህ - "ከዚህ የሚከለክል የለም" ይላሉ። [ፈታወ ሸይኽ ኢብኒ ሑመይድ: 144]

ሸይኽ ኢብኑ ባዝም እንዲሁ ምንም ችግር የለበትም ብለዋል።

ኢብኑ ዑሠይሚንም እግሮችን በእንቅልፍ ጊዜ ወደ ቂብላ አቅጣጫ ስለማድረግ ሲጠየቁ እንዲህ ብለዋል፦

ليس على الإنسان حرج إذا نام ورجلاه في اتجاه القبلة .

"በአንድ ሰው ላይ እግሮቹ ወደ ቂብላ አቅጣጫ ሆነው ቢተኛ ችግር የለበትም።" [ፈታወ ሸይኽ ኢብኒ ዑሠይሚን፡ 2/976]

Ibnu Munewor

=

የቴሌግራም ቻናል፡-

https://t.me/IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

كناشة ابن منور
Send as a message
Share on my page
Share in the group