UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.
7 days Translate

ከቁርኣን ልዩ ባህሪያት

ጥንቅር ኢብን አሚን

ለተከበረው ቁርአን ቀድመውት ከወረዱት ሰማያዊ መጻሕፍት የሚለይበት ልዩ ባህሪያት አሉት፡-

1. ከዚህ በፊት የወረዱት መጻሕፍት ይዘውት የነበረውን መለኮታዊ የመልእክት ጭብጥ አጠቃሎ ያካተተ መሆኑ፣ በእነዚህ የተላያዩ መጻሕፍት ተበታትነው የሚገኙ መልካምና የላቁ አስተምህሮቶች ሰብስቦ መያዙ፣ ሁሉንም ያካበበና በነርሱ ላይ ተጠባባቂ መሆኑ፣ በሌሎች መጻሕፍት ውስጥ ያሉ እውነታዎችን የሚያረጋግጥና በነርሱም ውስጥ የተደረጉ ብረዛዎችንና ቅየራዎችን የሚያጋልጥ መሆኑ። አላህ እንዲህ ብሏል፡-

‘’ ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲሆን በውነት አወረድን…’’ አልማዒዳ፡48

2. አላህ (ሱ.ወ.) ለሁሉም የሰው ልጆች፣ ለሁሉም ዘመንና ቦታ እንደሚስማማ አድረጎ ያወረደው መሆኑና ለአንድ ለተለየ ሕዝብ ብቻ ያልወረደ መሆኑ። አላህ አንዲህ ብሏል፡-

‘’ ያ በባሪያው ላይ ፉርቃንን (ቁርአንን) ለዓለማት አስፈራሪ ይኾን ዘንድ ያወረደ(አምላክ) ክብርና ጥራት ተገባው።’’

3. ቁርአን አላህ እንደሚጠብቀው ቃል የገባለት ብቸኛ መለኮታዊ መጽሐፍ መሆኑ። የተናጋሪዎች ሁሉ አሸናፊ (አላህ) እንዲህ ብሏል፡-

‘’ቁርአንን እኛው አወረድነው፣ እኛም ለርሱ ጠባቂዎቹ ነን’’ (አል-ሂጅር 9)

ይህም የሆነበት ምክንያት የሰው ልጆች ይመሩበት ዘንድ የወረደውና የአላህ የመጨረሻ ቃል የሆነው የቁርአን አስተምህሮ ዘመን ሳይሽረው ለሁልጊዜም እንዲቆይ አላህ (ሱ.ወ.) በመፈለጉ ይህንን መልእክት የመበረዝ፣ የመቀየርም ሆነ የመለወጥ አደጋ እንዳይደርስበት አላህ እራሱ ስለጠበቀው ነው።

“እርሱ (ቁርአን) አሸናፊ የሆነ መጽሀፍ ነው፤ ከበስተፊቱም ከበስተኋላውም ስህተት የማይመጣበት ከጥበበኛውና ከምስጉኑ (አላህ) የተወረደ ነው) [ፉሲለት 14፣24]

4. አላህ (ሱ.ወ.) ንግግሩ ወደ ሰው ልጅ አእምሮና ጆሮ ውስጥ እንዲሰርፅና መልእክቱ እንዲደርስ ከዚያም ወደ ተጨባጭ ተግባር እንዲቀየር ይፈልጋል። ይህ ደግሞ ቁርአን በራሱ ገር ካልሆነ በስተቀር በቀላሉ ለማስታወስና ለመረዳት ስለማይቻል አላህ ገር አድርጎታል፡-

‘’ቁርአንን ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፣ ተገንዛቢም አለን?’’ አልቀመር፡17

#gaza #palestine #freepalestine

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
7 days Translate
Translation is not possible.

የአላህ መልእክተኛ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ስለ ክህደት እንዲህ ይላሉ፡፡

ቢጾምም ቢሰግድም ሙስሊም ነኝ ቢልም ሦስት ነገሮች ያሉበት ሰው ሙናፊቅ ነው፡፡

1.ሲያወራ ይዋሻል፡፡

2.ቀጠሮ ሰጥቶ ያፈርሳል፡፡

3.ሲያምኑት ይከዳል፡፡

ታላላቅ ሰዎች ስለክህደት እንዲህ ብለዋል፡፡

• ከዳተኛ ሰዎች ለግዜው ደስተኛ ይምሰሉ እንጂ የክዳታቸው ማእበል ያሰምጣቸዋል፡፡

• ክህደት ካልፈጸምክ በሰላም ተኛ፡፡

#gaza #palestine #freepalestine

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አንድ አባት ሴት ልጁን ውድ በሆነ ሆቴል ራት ጋበዛት....

ከሆቴሉ ባልተቤት ጋር በመነጋገር  ከፊት ለፊታቸው የተለያዩ  ያማሩና ጣፍጭ ምግቦች እንዲያስቀምጥ ነገረው ።

ከትንሽ ደይቃ ብኋላ የሆቴሉ ባልተቤት የተለያዩ ጣፍጭ ምግቦችንና

የተሸፈነ ምግብ ይዞ መጣ..

ልጂቱም ከፊት ለፊቶ የተቀመጡትን ምግቦች

መመልከት ጀመረች  በእቃ የተሸፈነው  ምግብ

ይበልጥ ሳባትና ልትከፍተው ስትል አባቷ ከለከላት ....!

አባቷም ከፊት ለፊትሽ በርካታ ጣፍጭና የሚያማምሩ ምግቦች እያሉ የተሸፈነውን ለምን መክፈት ፈለግሽ ሲል ጠየቃት...?

ልጂቱም የተሸፈነ ስለሆነ በውስጥ ያለው ያማረና የተሻለ ጥፍጥና ይኖረዋል  ብየ ስላሰብኩ ነው ስትል መለሰች ...

አባቷም ፈገግ አለና እንዲህ አላት

በሒጃብ ለምን እንደምሸፍንሽ አወቅሽ!

ልጂቱም ወደ መሬት እየተመለከተች አባቷ ያላት ገባት !

ከዛ ብኋላ ምርጥ የተሸፈነ ምግብ ሆነች!

ሒጃብ ነገራቶች ለማክበድ ሳይሆን በአጭሩ

መደበቅ ያለበት ተደብቆ ማየት ያለበት እንዲያይ ነው ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ፈጅር ከግማሽ ሰዓት በፊት ንቃ፣ ዊትርን ስገድ ዱዓ አብዛ

ለፈጅር አዛን ሲል መስጊድ ሄደህ ሁለት ረከዓህ ስገድ ሴት ከሆነች እቤት ውስጥ ትሰግዳለች።

ከዚያም ሁለት መዳፎችህን ወደ ላይ ዘርጋና  ለሶላቱ ኢቃም እስኪደረግ ድረስ ዱዓውን አስረዝም፣ ከዚያም ከሶላት በኋላ  የጠዋት ዚክርዎችን አንብብ።

በአላህ እምላለሁ! የአላህ ውዴታ፣ ስኬት፣ ሲሳይ እና  ደስታ በሁሉም የሕይወትህ ዘርፍ ውስጥ ታያለህ።

ዶ/ር ያሲር አል ዒነዘይ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🔶ከኢብኑል ቀይም ድንቅ ምክሮች🔶

''ረሱል(ﷺ)ማርን በውሃ ደባልቀው በባዶ ሆዳቸው ይጠጡ ነበር። ይህ ጤንነትን በመጥቀም ዙርያ ብልጥ ሰዎች እንጂ የማያውቁት ጥልቅ ሚስጥር አለው።''

📖ዛዱል መዓድ 4:35

Send as a message
Share on my page
Share in the group