UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

«በሕይወታችን ከምንም በላይ ሊያሳስበን የሚገባው ትልቁ ጉዳይ የዓለማቱ ጌታ፣ ረሕማኑ ዘንድ ያለን 'ቦታ' ነው። ሰው የማይመዘን ገ 'ለ' ባ በሆነበት ዘመን በፍፁም ሰዎች ዘንድ ስላለን ቦታ ልንጨነቅም ሆነ፣ ለሰዎች ልንኖር አይገባም። ረሕማኑን ከያዝን፣ እርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ካሳመርን ወደፊት ሁሉም ወደኋላ ቀሪ፣ ሐቅ ደግሞ ውሸትን ገፍታሪ ነው። ውሸትን ለመደበቅ እንጅ እውነትን ግልፅ ለማድረግ መሮጥ አያስፈልግም፤ እውነትም ሆነ ውሸት ግዜን ይፈልጋሉ ግዜያቸውን እየጠብቁ ይፋ ይሆናሉ።»

ጊዜ + ዝምታና + ሶብር = ሐቅን ይወልዳሉ!

✍አቡ ሒባ (ሕዳር 1, 2016 E.C)

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Follow & Share → Umma ሚዲያ

↓↓↓↓↓

Umma ሚዲያ

ንጉስ ፈይሰል አሸዋ ላይ በተዘረጋው ምንጣፍ ላይ ተቀምጦ የአሜሪካ ቴፕላይን ካምፓኒ ሃላፊን አስጠራ

"አንዲት የነዳጅ ጠብታ ወደ እስራኤል እንዳይላክ" ሲልም አዘዘ።

አሜሪካ ትዕዛዙን ጥሳ ለእስራኤል እርዳታ እንደላከች ሲሰማ ከአሜሪካ ጋር የነበረውን የነዳጅ ሽያጭ ውሉን አቋረጠ።

በሀገረ አሜሪካ ሰላማዊ ሰልፍ ነገሰ

ሰዎች በነዳጅ ማደያዎች ፊት ተሰልፈው

ነዳጅ እንጂ እስራኤልን አንፈልግም የሚለውን መፈክር አስተጋቡ።

በዚህ ጊዜ ንጉስ ፋይሰል ታዋቂ ንግግሩን አደረገ

"ነዳጅ ከቁድስ ክብር አይበልጥብንም። አያቶቻችን በተምርና በወተት ኖረዋል እኛም ወደዛው ህይወት እንመለሳለን"

አላህ ይዘንልህ

ምንጭ፡-

مذكرات الدكتور معروف الدواليبي

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

INSA

ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተሰጠ ማስጠንቀቂያ👇

ሁሉም ሰው የኢንተርኔት ዓለም እውነታዎችን መረዳት እና ማወቅ አለበት፡፡

በኦንላይ የሚደረጉ ግብይቶች፣ የመረጃ ልውውጦች እና የምናጋራቸው መረጃዎች እንዴት በእውነተኛ ህይወት ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ማወቅ እና መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

በተለይም በቴሌግራም እና በፌስቡክ አካውንቶች ሰሞኑን በብዛት ሲዘዋወሩ የተስተዋሉት ሊንኮች እውነት የሚመስሉ ነገር ግን ከጀርባቸው ተንኮል አዘል ተልእኮ  የያዙ ሊንኮች ወይም መልዕክቶች ናቸው፡፡

የእነዚህ ሊንክ ፈጣሪዎች ግላዊ መረጃ ለመውሰድ በማሰብ እጅግ አሳማኝ እና ትክክል የሚመስሉ መረጃዎችን በማጋራት ሊንኩ ሲከፈት ሙሉ ስም፣ የቤት አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በመጠየቅ ስለግለሰቡ መረጃ ካገኙ በኃላ ለቀጣይ ጥቃት የሚዘጋጁበት መንገዶች ናቸው፡፡

ብዙ የግል መረጃዎቻችንን በመስመር ላይ (online) እናጋራለን፣ አጭበርባሪዎች ከፈጠሩልን አጀንዳ አሳሳችነት አንጻር አንዳንድ ጊዜ ከመጠን በላይ ግላዊ መረጃዎቻችንን አሳልፈን በመስጠት አደጋ ውስጥ መሆናችንን እንኳን አናስተውልም።

ግላዊ መረጃዎች በጥቁር ገበያ ጭምር ስለሚሸጡ የሳይበር ወንጀለኞች የመረጃ ግላዊነትን ጥሰው በመግባት መረጃችንን በብዙ ዋጋ ይሸጡታል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሰረቀ መረጃ በጥቁር ገበያ በተለያዩ አገሮች ይቸበቸባል። በሀገራችንም የሳይበር ወንጀለኞች በመስመር ላይ (online) የሚሸጡአቸው የመረጃ አይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡

✔ የሞባይል ስልክ ቁጥሮች

✔ የኢሜይል አድራሻዎች

✔የክሬዲት/ATM ካርድ/ባንክ አካውንት ቁጥሮች

✔ የIP አድራሻዎች

✔ PIN Code/የይለፍ ቃል

✔ሌላ የግል መረጃ

በመስመር ላይ (online) የሚደረጉ ግብይቶች፣ የመረጃ ልውውጦች እና ሳናውቅ/ በቸልተኝነት የምንከፍታቸው ሊንኮች በእውነተኛ ህይወታችን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ማወቅ እና መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡ በኢሜል፣ በቴሌግራም፣ በፌስቡክ፣ በሌሎች ድረ-ገጾች የሚላኩ ሀሰተኛ ግን ተመሳስለው የተሰሩ ሊንኮች ናቸው፡፡ ሊንኩ ሰዎች በሚወዱት፣ በሚፈልጉት (ስኮላርሺፕ)፣ በሚያስደነግጣቸው ወይም ሌላ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ ከሚያደርግ አጭር የጽሁፍ መግለጫ ጋር ሊላክ ይችላል፡፡

ኅብረተሰቡ የጥንቃቄ እርምጃ በመውሰድ ከሚደርስበት የሳይበር ጥቃት እራሱን፣ ቤተሰብዎን፣ ተቋሙን እና ሀገሩን መጠበቅ አለበትል፡፡ 

መወሰድ ያለበት የጥንቃቄ እርምጃ

• በመስመር ላይ (online) መረጃ ከመስጠታችን አስቀድሞ የተቀባዩን ማንነት እና ትክክለኛነት ማረጋገጥ፤

• የተላኩትን ሊንኮች ከመክፈታችን በፊት የላከውን አካል ማንነት ማጣራት

• የተላከው ሊንክ ከምናውቃቸው ሊንኮች ጋር አንድ መሆን አለመሆኑን ማረጋገጥ

• ከተጠራጠርን ፈጽሞ ሊንኮቹን አለመክፈት::

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

#ሰበር

የፍልስጤም ጦር በየሰዓቱ 3 የጦር ተሸከርካሪዎች ከ6 ሰአት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ደግሞ 17 የእስራኤል ታንኮችን አውድሟል ሲል ቁድስ የዜና ወኪል ገለፀ

በፍልስጤም ጦር የወደሙ የወራሪዋ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች፣ ታንኮች፣ የታጠቁ ተሽከርካሪዎች እና ቡልዶዘሮች በሁለት ቀን ውስጥወደ 27 ጨምሯል።

@Quds news network

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

‘አራት (4)’

በዱንያም በአኼራም ስኬታማ ሰው መሆን ትፈልጋለህ – እንግዲያውስ አራት (4) ነገሮችን እድሜ ልክህን ፈፅሞ እንዳትተዋቸው 👇

🌀1⃣ ሹክር : ፈጣሪህን ሁሌ ማመስገን እንዳትተው መጨመርን (በረካን) ትነፈጋለህና

{لَئِن شَكَرْتُمْ لَأَزِيدَنَّكُمْ}

🌀2⃣ ዚክር : አብዝተህ አሏህን ማስታወስን እንዳትተው የሱን ትውስታ (እሱ አንተን ማስታወሱን) ትከለከላለህና

{فَاذْكُرُونِي أَذْكُرْكُمْ}

🌀3⃣ ዱዐእ : አሏህን መለመንን እንዳትተው ኢስቲጃባን (ተቀባይነትን) ትነፈጋለህና

{ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ}

🌀4⃣ ኢስቲግ’ፋር : ለወንጀሎችህ ምህረትን መጠየቅ እንዳትተው ነጃ መሆንን (ከእሳት መዳንን) ትነፈጋለህ

{وَمَا كَانَ اللَّهُ مُعَذِّبَهُمْ وَهُمْ يَسْتَغْفِرُونَ}

✅ አጂብ!... ምንኛ ያማሩና የተዋቡ ታላቅ የአሏህ ቃልኪዳኖች ናቸው!! እንጠቀምባቸው አህባቢ!!

Send as a message
Share on my page
Share in the group