Translation is not possible.

INSA

ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተሰጠ ማስጠንቀቂያ👇

ሁሉም ሰው የኢንተርኔት ዓለም እውነታዎችን መረዳት እና ማወቅ አለበት፡፡

በኦንላይ የሚደረጉ ግብይቶች፣ የመረጃ ልውውጦች እና የምናጋራቸው መረጃዎች እንዴት በእውነተኛ ህይወት ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ማወቅ እና መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

በተለይም በቴሌግራም እና በፌስቡክ አካውንቶች ሰሞኑን በብዛት ሲዘዋወሩ የተስተዋሉት ሊንኮች እውነት የሚመስሉ ነገር ግን ከጀርባቸው ተንኮል አዘል ተልእኮ  የያዙ ሊንኮች ወይም መልዕክቶች ናቸው፡፡

የእነዚህ ሊንክ ፈጣሪዎች ግላዊ መረጃ ለመውሰድ በማሰብ እጅግ አሳማኝ እና ትክክል የሚመስሉ መረጃዎችን በማጋራት ሊንኩ ሲከፈት ሙሉ ስም፣ የቤት አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በመጠየቅ ስለግለሰቡ መረጃ ካገኙ በኃላ ለቀጣይ ጥቃት የሚዘጋጁበት መንገዶች ናቸው፡፡

ብዙ የግል መረጃዎቻችንን በመስመር ላይ (online) እናጋራለን፣ አጭበርባሪዎች ከፈጠሩልን አጀንዳ አሳሳችነት አንጻር አንዳንድ ጊዜ ከመጠን በላይ ግላዊ መረጃዎቻችንን አሳልፈን በመስጠት አደጋ ውስጥ መሆናችንን እንኳን አናስተውልም።

ግላዊ መረጃዎች በጥቁር ገበያ ጭምር ስለሚሸጡ የሳይበር ወንጀለኞች የመረጃ ግላዊነትን ጥሰው በመግባት መረጃችንን በብዙ ዋጋ ይሸጡታል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሰረቀ መረጃ በጥቁር ገበያ በተለያዩ አገሮች ይቸበቸባል። በሀገራችንም የሳይበር ወንጀለኞች በመስመር ላይ (online) የሚሸጡአቸው የመረጃ አይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡

✔ የሞባይል ስልክ ቁጥሮች

✔ የኢሜይል አድራሻዎች

✔የክሬዲት/ATM ካርድ/ባንክ አካውንት ቁጥሮች

✔ የIP አድራሻዎች

✔ PIN Code/የይለፍ ቃል

✔ሌላ የግል መረጃ

በመስመር ላይ (online) የሚደረጉ ግብይቶች፣ የመረጃ ልውውጦች እና ሳናውቅ/ በቸልተኝነት የምንከፍታቸው ሊንኮች በእውነተኛ ህይወታችን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ማወቅ እና መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡ በኢሜል፣ በቴሌግራም፣ በፌስቡክ፣ በሌሎች ድረ-ገጾች የሚላኩ ሀሰተኛ ግን ተመሳስለው የተሰሩ ሊንኮች ናቸው፡፡ ሊንኩ ሰዎች በሚወዱት፣ በሚፈልጉት (ስኮላርሺፕ)፣ በሚያስደነግጣቸው ወይም ሌላ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡ ከሚያደርግ አጭር የጽሁፍ መግለጫ ጋር ሊላክ ይችላል፡፡

ኅብረተሰቡ የጥንቃቄ እርምጃ በመውሰድ ከሚደርስበት የሳይበር ጥቃት እራሱን፣ ቤተሰብዎን፣ ተቋሙን እና ሀገሩን መጠበቅ አለበትል፡፡ 

መወሰድ ያለበት የጥንቃቄ እርምጃ

• በመስመር ላይ (online) መረጃ ከመስጠታችን አስቀድሞ የተቀባዩን ማንነት እና ትክክለኛነት ማረጋገጥ፤

• የተላኩትን ሊንኮች ከመክፈታችን በፊት የላከውን አካል ማንነት ማጣራት

• የተላከው ሊንክ ከምናውቃቸው ሊንኮች ጋር አንድ መሆን አለመሆኑን ማረጋገጥ

• ከተጠራጠርን ፈጽሞ ሊንኮቹን አለመክፈት::

Send as a message
Share on my page
Share in the group