Reshad akmel shared a
Translation is not possible.

«እማ»

--------------------------

አውጥቼ አውርጄ እርእስ አልመርጥም፡

ፍቅሬን በምን ቋንቋ እያልኩኝ አልቀብጥም፡

ብቻ ግን ፃፍኩላት ያው ስራዬም አይደል?

ብራናዬ አጥሮብኝ ካላነሰኝ ፊደል፡

ስለ እሷ የማውቀውን ታምርና ገድል፡

ከልኳ ጫፍ ሳላልፍ ከክብሯ ሳላጎድል፡

እጽፋለሁ እኔ ያየሁትን እውነት፡

ልጇ ሆኘ ለርሷ እማ በሚል እምነት፡

------------------------------

የሴቶች የበላይ የፍቅር አሻራ፡

ገፀ-በረከቴ የተስፋ ቢሻራ፡

እናት በሚል ስምሽ አለምን የቃኘሽ፡

የፍቅር ውብ ቅኔ ሁሉም የተመኘሽ፡

እናት እና ፍቅር አንድ አይነቶች ናቸው፡

በሶስት ፊደላት ሁሉም ያወቃቸው፡

ለሁሉም ፍጥረታት አዛኝ ነው ልባቸው፡

-----------እማማዬ------------

በገረጣው ፊቷ ተፅፏል ታሪኳ፡

ያደፈ ቢመስልም ተውቦ አለ መልኳ፡

ረቂቅ ነው ቅኔው የናትነት ልኳ፡

ሳቄ ደስታዋ ነው ሀዘኔም ሀዘኗ፡

የኔ ልጂነት ነው የእማዬ ሚዛኗ፡

ጧትም ማታም ቢሆን «ልጄ»ነው ልሳኗ፡

ጤናዬ ጤናዋ ህመሜ ህመሟ፡

ለልጇ መኖር ነው የህይወት ቅመሟ፡

--------------------------------

          «እማ»

         --------

ተቆጥታኝ እንኳን አይታኝ ትራራለች፡

ውስጧን ቢከፋውም ለእኔ ትስቃለች፡

ብዙ ውጣውረድ ብዙ ፈተና አልፋ፡

ወዝና ቀለሟን ከፊቴ ላይ ፅፋ፡

እኔ እንድቃናላት እርሷ ጎንበስ ያለች፡

በልጅነት ዕድሜ ገና ለጋ ሳለች፡

ምኑንም ሳታውቀው ወልዳ ያሳደገች፡

የእርሷን ህይወት ትታ ለኔ ነፍስ የኖረች፡

--------------------------------

እድሜዋን በሙሉ ለደስታዬ ኖራ፡

ሀሴት የምትሰጠኝ ስሜን ስትጠራ፡

ለትንሽ ጊዜ እንኳን ከፊቷ ስሰወር፡

ፈጥኖ የሚመታ የልቧ መዘወር፡

ዘመን የማይፈታት እንኳን ትንሽ ቀናት፡

የደግነት አርማ ልዩ ነች የኔ እናት፡

-----------------------------

ምናብ መስላ፤

ግን እንደ ሰው በእውን ያለች፡

በእዝነቷ ጥልቀት፤

በጥበቧ ድምቀት ህልም መስላ የተሳለች፡

እማ ብዬ.....፤

በፍቅር ቃል በልቤ ላይ የደረስኳት፡

በቃሌ ላይ ሳልታጠፍ፤

የዘወትር ትዝታዬ በምናቤ የቀረፅኳት፡

እጂግ በጣም የምወዳት፤

የፍቅር መምህሬ ከራስ በላይ የማፈቅራት፡

እናቴ ነች በጥበቡ ፤

አምላካችን ንግሥት አርጎ የፈጠራት፡

በእውን አይኔ ስዬ፤

እያስታወስኩ እስከማያት የታመነች፡

እስከዛው ግን፤

በልቤ ያለች የልቦለድ ድርሰቴ ነች፡

----------እማማማዬ----------          

ላረግሽልኝ ሁሉ አልችልም ልክስሽ፡

ግና ቃል አለብኝ ሁሌም ላስታውስሽ፡

እንደ ልጅነቴ ልጦርሽ ባልችልም፡

ልቤ ላይ ነው ቀብርሽ ለምን አይባልም፡ በጀነት ሀገር ላይ ለማገኘት ያብቃኝ፡

በደማቅ ፈገግታች በሀሴት እንድቃኝ፡

     ----------እማማዬ------------

በጀነት እንዳይሽ አላህ እኔን ይርዳኝ፡

ፊት ለፊትሽ ሆኘ በፈገግታሽ ልዳኝ፡

አሏህ ይዘንልሽ ውብ አዳራሽ ሰቶ፡

ጀነት ያገናኘን ፊትሽን ልየው ፈክቶ፡

--------------------------------

የእድገቴ መሰረት የነገ አላማዬ፡

አሁን ላለኝ እውነት አንች ነሽ ማማዬ፡

ሰላም ላንች ይሁን ውበቴ እማማዬ፡

--------------------------

       በኑረዲን አል አረቢ

-----------------------------

t.me/nuredinal_arebi

t.me/nuredinal_arebi           

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Reshad akmel shared a
1 year Translate
Translation is not possible.

🌸ምክር ለእህቴ 🌸

🔸የንጉሱ ሚስት ነብዩላህ ዩሱፍ (ዐ.ሰ)

ዘንድ ለመድረስ የተጠቀመችው

ማማለል ሽንገላና ማስፈራሪያ

ዩሱፍን ለማግኘት አላስቻላትም

ነገር ግን

👉የነብዩላህ ሹዐይብ (ዐ,ሰ) ልጅ ግን

በነበራት ሀያእ ነብዩላህ ሙሳን (ዐ,ሰ)

ማግባት ችላለች።🌷🌷🌷🌷

👌 እናማ እህቴ አደራ ሀያእሽን ጠብቂ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Reshad akmel shared a
Translation is not possible.

━┈የጥበብ ጫፍ ┅━

አንድ የሁዳዊ ወደ ሩቅ ሀገር እይተጓዘ ሳለ በመሀል የሙስሊሞች ሀገር ይደርሳል።

ያው እንደምታውቁት ይሁዳ ሁሌም ሸር እንዳሰበ ነው።

እናም፦"እዚህ ከተማ ገብቼ ዑለማኦችን ማደናገር አለብኝ" ብሎ ያስባል።

ከዚያም ከተማዋን ሊገባ ሲል አንድ እረኛ ያጋጥመውና በሱ ሊጀምር ወሰነ እና እንዲህ በማለት ጨወታ ጀመረ፦"እኛ ሙስሊሞች እኮ ቁርአን ለመሀፈዝ በጣም እየተቸገርን ነው።

አንደኛ፦30 ጁዝ ነው በዝቷል።

ሁለተኛ፦አንቀፆችም በጣም ብዙ ናቸው።

ሶስተኛው እና አስቸጋሪው ፦ ቁርአን ውስጥ ድግምግሞሽ አለ።

ስለዚህ ለምን የተደጋገሙ አንቀፆችን አንሰርዝም? ምክንያቱም የቃላት መደጋገም ነው እንጂ ምንም አይደለም።

ድግምግሞሹን ከሰረዝን መሀፈዙም ይቀለናል።"

የሁዳው ይሄን ሁሉ ሲያወራ እረኛው በፅሞና ያዳምጠው ነበር።

ከዚያም እረኛው ቀና አለና፦"ንግግርህ በጣም ደስ ይላል አሪፍ ሀሳብ ነው።" አለው።

የሁዳው ደስታው ወደር አጣ ነገር ግን ድብቅ ሴራው እንዳይታወቅበት ደስታውን ደበቀው።

እረኛውም እንዲህ በማለት ንግግሩን ቀጠለ፦

"አንድ ጥያቄ አለኝ።

ባንተ የሰውነት አካል ውስጥ ድግምግሞሽ የለም?

ለምሳሌ፦ ሁለት እጅ

☞ሁለት አይን

☞ሁለት እግር

☞ሁለት ጆሮ.....

ታዲያ ሰውነትህ ቀለል እንዲልልህ አንድ አንዱን ለምን አትቆርጥም? ያው ድግምግሞሽ ነው እንጂ እኮ ምንም አይደለም"

ይሄን ሲለው የሁዳው ደነገጠ።ፊቱን አጨፍግጎ፦ "የእረኛዎቻቸው መልስ እንዲህ ከሆነ የዑለማኦቻቸው መልስ እንዴት ሊሆን ነው?" እያለ ከተማዋን ትቶ አለ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Reshad akmel shared a
Translation is not possible.

እኚህ በምስሉ ላይ ያሉት የወራሪዋ ወታደሮች በሙጃሂዶቹ የጀግንነት ተጋድሎ እዚህም እዚያም የወደቁ በሄሊኮፕተር ከጦር ሜዳው የተነሱ ጀናዛዎች ናቸው።

ጂእቱኩም ነበር ያለው ኻሊድ "እናንተ መኖርን የምትጓጉትን ያህል መሞትን የሚፈልጉ ተዋጊዎችን ይዤባችሁ መጥቻለሁ" ታሪክ ራሱን እየደገመ ነው።

ፍርሀት በራስ አለመተማመን በጠላት ጦር መሐል ሰፍኗል። ቀሳም ሆይ ሰንዝር የሚሉ መፈክሮች ከፍልስጤማዊያን በኩል ይደመጥ ከጀመረ ሀያ ቀናት አልፈዋል።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Reshad akmel shared a
Translation is not possible.

የኢትዮጲያ ሙስሊም ሲነካ ብቻ ሊያመን አይገባም አላህ በኢስላም አድ አድርጎናል

ኢስላም ዘር ቢሆር ጎሳ አይልም ሙስሊም ለሙስሊም ወድማማች ነዉ المسلم اخو المسلم

الحمد الله

አድ ሙስሊም ሲታመም ሌላዉም መታመም አለበት

ሙስሊም ማለት ልክ እደ አንደ ጀሰድ ነዉ እጅ ከታመመ ሁሉም ሰዉነት እደሚታመመዉ

المسلم اخو المسلم

#ሼር አደራ

#ፎሎው

Send as a message
Share on my page
Share in the group