UMMA TOKEN INVESTOR

About me

Writ good or remain silent

Translation is not possible.

ሙዓዊያ እና ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁማ በተጋጩ ግዜ ሁለት

ኢስላማዊ ስረወ መንግስት ተመሰረተ የሮሙ ንጉስ ይህን ሰምቶ

እንዲህ ሲል ደብዳቤ ፃፈ።

<<ከሮም ንጉሰ ነገስት ለ ሙስሊሞች መሪ ሙዐዊያ አቡ ሱፍያን!!

ባንተ እና በዐሊይ መካከል የተከሰተውን ግጭት

ሰምተናል።ስለዚህም ለሙስሊሞች መሪ አንተ መሆን

እንዳለብህም ስለምናምን አንተ ፍቃድህ ከሆነ የዐሊይን ጭንቅላት

ቀንጥሶ የሚያመጣልህን ወታደር ልላክልህ>>

ይህ ደብዳቤ ሙዐዊያ ጋር እንደደረሰም ሙዓዊያም

<<ከሙዓዊያ ለሮም መሪ!!! ሁለት ወንድማማቾች ስለተጣሉ

አንተ ምን አገባህ? አፍህን የማትዘጋ ከሆነ ጅማሬው እኔ ጋ የሆነ

እና ፍፃሜው አንተ ጋ የሆነ ሰራዊት ልኬ አንገትህን በማስቀንጠስ

ለዐሊይ በስጦታ መልኩ አበረክትለታለሁ>>

#ይህ_ትክክለኛ_ሙስሊሞች_ሳለን_ነው

_____

___

ካሊድ ኢብን ወሊድ ለፐርሺያው ንጉሰ ነገስት እንዲህ ሲል

ደብዳቤ ፃፈለት

<<ስለም ትድናለህ። እንቢ ያልክ እንደሆን ግን፤ እናንተ ህይወትን

የምትወዱትን ያህል ሞትን የሚወዱ ሰራዊቶችን ይዤልህ

እመጣለሁ።>>

ንጉሱ ይህን ደብዳቤ ካነበበ በኋላ የቻይናውን ንጉስ የጦር እርዳታ

ሊለምነው ደብዳቤ ፃፈለት።

የቻይናውም ንጉስ እንዲህ ሲል ደብዳቤ መልሶ ላከለት።

<<ንጉስ ሆይ! ተራራን እንኳን ለመናድ ካሰቡ ምንም

ከማያግዳቸው ወታደሮች ጋር ለመጋፈጥ አቅሙ ስለሌለኝ

ጥያቄህን መፈፀም አልችልም።>>

# ምን_ያህል_ሀያላን_እንደነበርን_ተመልከቱ

_____

____

በደውለቱል ዑስማኒያ የአገዛዝ ዘመን የሙስሊም ወታደሮች የጦር

መርከቦቻቸውን ይዘው በአውሮፓ ደሴቶች ሲያልፉ በአከባቢው ያሉ

አብያተ ክርስትያናት በሙሉ ሙስሊሞች መጥተው ፈትህ

እንዳያደርጉ በመፍራት ከበሮ ከመምታት እና ምንም አይነት ድምፅ

ከማሰማት ይቆጠቡ ነበር።

#ያኔ_ጀግና_ሳለን

_____

____

በደውለቱል ኡስማኒያ የአገዛዝ ዘመን በያንዳንዴ ቤት ደጅ ላይ

ሁለት የበር ማንኳኩያዎች ይኖራሉ። አንዱ ትልቅ ሲሆን አንዱ ትንሽ

ነው። በትልቀኛው ከተንኳኳ አንኳኪው ወንድ ነው'ና በሩን ሊከፍት

ሚመጣው ወንድ ይሆናል። ነገር ግን በትንሸኛዋ ከተንኳኳ

አንኳኪዋ ሴት መሆኗ ስለሚታወቅ ሴት ትከፍትላታለች።

በዚያ ምርጥ ዘመን አንድ ቤት ውስጥ ሰው ከታመመ ደጅ ላይ

ቀይ አበባ ይንጠለጠል ነበር። ያን አበባ የተመለከቱ ሰዎች ሁሉ

እዝያ ቤት በሽተኛ መኖሩን ስለሚያውቁ በበሩ ሲያልፉ ድምፃቸውን

ዝቅ ያደርጉ ነበር።

#ሹፍ_ምን_እንመስል_እንደነበር !!!

_____

_

ግዜው ሰላሁዱን አል አዩቢ በይተል መቅዲስን ባስመለሰበት ግዜ

ነበር። እና ጦርነቱ ነገውን ሊጀመር ማታ ላይ የጦር መሪው

ሰላሁዲን የወታደሮቹን ድንኳን እየዞረ ሲያዳምጥ፤ ግማሹ ለይል

ይሰግዳል፣ ሌላው ቁርአን ይቀራል፣ የተቀሩት ደግሞ ይዘክራሉ።

ግን ድንገት በሆነ ድንኳን አጠገብ ሲያልፍ በድንኳኑ ውስጥ ያሉት

ሁሉም ተኝተው ነበር። ይህን ግዜ፦"በዚህች ድንኳን አዳሪዎች

ምክንያት ልንሸነፍ እንችላለን" ብሎ አለፈ።

#ማንተኛበት_ዘመን

_____

___

ቀደምት ዑለማኦች በሶስት ነገራት አደራ ይባባሉ ነበር።

1፦ሰውዬው በሱ እና በአላህ መካከል ያለውን ግንኙነት ካሳመረ፤

በሱ እና በሌሎች መካከል ያለው ግንኙነት ያምርለታል።

2፦ሰውዬው ሚስጥራዊ ተግባሩን ካሳመረ አላህ ይፋዊ ተግባሩን

ያሳምርለታል።

3፦ሰውዬው የአኪራው ጉዳይ ካስጨነቀው አላህ የዱንያውንም

የአኪራውንም ጉዳይ ያግራራለታል።

_____

_

#ትልቁ_ኪሳራ_ማለት_ይህ_ነው

ጀነት ስፋቷ የምድርን እና የሰማያትን ያህል ሁና ላንተ በሷ ቦታ

ሳይኖርህ ሲቀር...ትልቅ ኪሳራ ነው።

በእለታዊ ፕሮግራምህ ውስጥ ቁርአንን መቅራት ካልተካተተ ትልቅ

ኪሳራ ነው።

ይህን ፅሁፍ በማሰራጨት ጓደኛህን እንድታነቃው ይከጀላል!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Follow & Share → Umma ሚዲያ

↓↓↓↓↓

Umma ሚዲያ

ከነቢ ሰዐወ ህልፈት በኋላ ሰሃባዎች ወደ ተለያዩ የአለማችን

ክፍሎች ተበትነው ዘመቻ ላይ ናቸው።

ሳዕድ ኢብኑ አቢ ወቃስ ረዐ በታዘዘው መሰረት ሰራዊቱን ይዞ

ከፐርሺያ ምድር ተከስቷል። ያ በዐረብያ ምድር ያለ ስልጣኔ የኖረ

ማህበረሰብ ትልቁን የስልጣኔ መገለጫ የሆነውን ፐርሺያን በጦር

ሊገጥም አኮብኩቧል።

የፐርሺያው ስረወ መንግስት እልፍ አዕላፍ የሆነ የሰራዊት ማዐት

አሰልፎ ቁጥራቸው እና ትጥቃቸው እዚህ ግባ ከማይባሉ

ሰሓባዎች ጋር ሊፋለም ድንኳናቸውን ተክለው ማዶ ለማዶ

ይተያያሉ።

በዚህ መሃል የሰሓባዎቹ የጦር አዛዥ የሆነው ሳዕድ ከሰራዊቱ 7

ወጣቶችን መልምሎ የፐርሺያ ሰራዊቶችን ሁኔታ እንዲያጣሩ እና

ከቻሉም አንድ የፐርሺያ ወታደር ጠልፈው እንዲመጡ ላካቸው።

7 ሁነው ጉዞ ጀመሩ። ትንሽ እንደተጓዙም በርከት ያለ ቁጥር

ያላቸው የፐርሺያ ወታደሮችን ከርቀት ሲመጡ ተመለከቱ'ና

መቋቋም ስለማይችሉ ለመመለስ ወሰኑ።

ግና ከመካከላቸው በሀሳባቸው ሳይስማማ ቀርቶ አንደኛው

«የታዘዝኩትን ሳልፈፅም አልመለስም» በማለት ተልዕኮውን

ለማሳካት ጎዞውን ቀጠለ። 6ቱ ትተው ተመለሱ።

ጉዞውን በእርጋታ እና በመጠንቀቅ ቀጠለ። ሰራዊቱን በውሃ

ድልድዮች ተደብቆ ከተሻገረ በኋላ ማንም በማያውቀው ሁኔታ

ከ40,000 ሰራዊት እንብርት ላይ ተከሰተ።

ከሰራዊቱ መሀል ላይ ቁሞ ሩቅ እያማተረ ሲመለከት ከርቀት ነጭ

ድንኳን እና ከደጁ የቆመ የንጉሳን ፈረሰ ከአይኑ ገባ።

«ይህ የጦር አዛዣቸው የሩስቱም ድንኳን መሆን አለበት» ብሎ ወደ

ድንኳኑ ተጠግቶ ሌሊቱ ፅልመቱን ለምድር እስኪያልብስ እዝያው

ቁጭ አለ።

ፀሀይ ጠልቃ ምድር በፅልመት ስትወረር፣ ሰራዊቱ ከብርዱ

ጭጋግ ሽሽት ከየድንኳኖቻቸው ሲወሸቁ፤ ወጣቱ ሰይፉን

ከማንገቻው መዝዞ ወደ አዛዡ ድንኳን አመራ።

ከድንኳኑ ደጅ ሲደርስም የድንኳኑን ማዋቀርያ ገመዶች በሰይፉ

ቆራርጦ ሙሉ ድንኳኑ በአዳሪያኑ ላይ ሲወድቅ እሱ ደጅ ላይ

የታሰረውን ፈረስ ፈትቶ ጎዞውን ቀጠለ።

ፈጣን ፈረሰኞች ኮቴውን ተከትለው ያሯርጡት ጀመር፤ ከፈረስ

ጀርባ ያደገው የዐረብያ ብላቴናውም አሸዋውን እያቦነነ ከፊታቸው

ይከንፋል።

በመጨረሻም ከሁሉም ርቆ ሶስት ፈረሰኞች ብቻ ሲያሯርጡ

ደረሱበት። ከሶስቱ ፈረሰኞች የግድ አንዱን ይዞ ወደ አሚሩ መሄድ

ስለሚጠበቅበት ሊያጃጅላቸው ፈልጎ ሲደርሱበት እያመለጣቸው፤

በጣም ሲራራቁ እየጠበቃቸው ከክልላቸው አስወጣቸው።

ከዝያም ዞሮ ሰይፍ ተማዘዛቸው፤ ብዙም ሳይቆይ ሁለቱን ገድሎ

አንዱን አስሮ ይዞት ከፊት ከፊት እየነዳው ጉዞ ወደ አሚሩ ጀመረ።

ልክ የሙስሊሞችን ሰራዊት ደርሶ ምርኮኛውን ከአሚሩ ፊት

ሲያቆመው ምርኮኛው ለአሚሩ፦ «ከለላህን ስጠኝ እኔም

ዕውነታውን ላውራ» አለው።

«እኛ የዕውነት ህዝቦች ነን፤ ከላላችንን የምንሰጥህ እማትዋሸን

እንደሆን ነው» አለው አሚሩ።

ንግግሩን ቀጠለ፦ «እስቲ ስለ ፐርሺያ ሰራዊቶች ንገረኝ»

ምርኮኛው፦ «ስለ ፐርሺያ ሰራዊት ስብጥር ከመናገሬ በፊት ስለ

ጀግናው ጓድህ ላውጋህ።

ከልጅነቴ አንስቶ የጦርነት ሜዳ ላይ ነው ያደግኩት እንዲህ አይነት

ሰው አይቼም አላውቅም። ሁለት ጠንካራ የሰራዊት ቡድኖችን

አልፎ በመግባት የአዛዣችንን ድንኳን ቆራርጦ ጣለ'ና ፈረሱን ይዞ

ጋለበ።

ለ3 ሁነን እስከ መጨረሻ ተከታተልነው። ከፈረሱ ወርዶ

ተፋለመን'ና የ1000 ፈረሰኛ ግምት የምንሰጠውን ጀግናችንን

ገደለው።

ሁለተኛውንም የጦር መኳንንት በ1000 የምንገምተው ሲሆን

እሱንም እያየሁ ገደለው። ሁለቱም ያጎቶቼ ልጆች ነበሩ።

ይህ ድርጊቱ እልህ በልቤ ቋጥሬ ልገድለው ባለ በሌለ ጉልበቴ

እንዳሯሩጠው አስገደደኝ። የኔ አይነት ጉልበታም ከወታደሩ ይኖራል

ብዬ ባልገምትም ባላሰብኩት መልኩ የዚህ ልጅ ምርኮኛ ሆኜ

መጣሁ።

የዚህ አይነት ጀግና አንድ ካላችሁ መቼም አትሸነፉም» አላቸው።

በመጨረሻም እስልምናን ተቀበለ።

የሙስሊሞቹ ወታደሮችም ምድር አንቀጥቃጭ የሆነ ጦርነት

አድርገው ፐርሺያን ሙሉ በሙሉ ደምስሰው ድልን ተቀዳጁ።

ያ ጀግናው ሰሓቢይም ስሙ ጡለይሃ ቢን ኩወይሊድ ዱንያ

እስካለች ድረስ ሲወሳ ይኖራል።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

boycot abbysinia bank

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Follow & Share → Umma ሚዲያ

↓↓↓↓↓

Umma ሚዲያ

አዲስ ቤት ገዛህ? ዝም በል አታውራ

አዲስ መኪና ገዛ? አትናገር

ትዳር መሰረትክ? ብዙ አታውራለት

ለመዝናናት ከከተማ/ሀገር ወጣ ብለህ ነበር? ዝም በል

ንግድ ልትጀምር ነው? ድምፅህን አጥፋ

ኑሮ እየሰመረልህ ነው? ብዙ አታውራ

አብዛኛውን ጊዜ

ያሰብናቸው ህልሞች እና የወጠንናቸው ራእዮች የማይሳኩበት

ዋነኛው ምክንያት ከመከናወናቸው በፊት ብዙ ስለምናወራ ነው -

ገና እንቁላሉን ስንታቀፍ ማውራት እንጀምርና ብዙ

ሸለምጥማጦችን እንጠራለን::

ወዳጅ እና የቅርብ ሰዎች የምንላቸው ሰዎች "ሰዋዊ ቅናት" እና

"የጥሎ ማለፍ ውስጣዊ ትንቅንቅ" በጣም የሚጠበቅ ተፈጥሯዊ

ሁነት ነው:: ስለዚህ ህልሞችህ መስመር ይዘው ፍሬ እስኪያፈራ

ድረስ ዝም ብለህ መስራትን ምረጥ::

አብዛኛው ሰው

ቢያልፍልህ እና ህልምህ ቢሰምርልህ ደስ ይለዋል ሆኖም ግን

ጥለኸው እንድትሄድ እና አንጋጦ ሊያይህ ይተናነቀዋል::

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Follow & Share → Umma ሚዲያ

↓↓↓↓↓

Umma ሚዲያ

ከነቢ ሰዐወ ህልፈት በኋላ ሰሃባዎች ወደ ተለያዩ የአለማችን

ክፍሎች ተበትነው ዘመቻ ላይ ናቸው።

ሳዕድ ኢብኑ አቢ ወቃስ ረዐ በታዘዘው መሰረት ሰራዊቱን ይዞ

ከፐርሺያ ምድር ተከስቷል። ያ በዐረብያ ምድር ያለ ስልጣኔ የኖረ

ማህበረሰብ ትልቁን የስልጣኔ መገለጫ የሆነውን ፐርሺያን በጦር

ሊገጥም አኮብኩቧል።

የፐርሺያው ስረወ መንግስት እልፍ አዕላፍ የሆነ የሰራዊት ማዐት

አሰልፎ ቁጥራቸው እና ትጥቃቸው እዚህ ግባ ከማይባሉ

ሰሓባዎች ጋር ሊፋለም ድንኳናቸውን ተክለው ማዶ ለማዶ

ይተያያሉ።

በዚህ መሃል የሰሓባዎቹ የጦር አዛዥ የሆነው ሳዕድ ከሰራዊቱ 7

ወጣቶችን መልምሎ የፐርሺያ ሰራዊቶችን ሁኔታ እንዲያጣሩ እና

ከቻሉም አንድ የፐርሺያ ወታደር ጠልፈው እንዲመጡ ላካቸው።

7 ሁነው ጉዞ ጀመሩ። ትንሽ እንደተጓዙም በርከት ያለ ቁጥር

ያላቸው የፐርሺያ ወታደሮችን ከርቀት ሲመጡ ተመለከቱ'ና

መቋቋም ስለማይችሉ ለመመለስ ወሰኑ።

ግና ከመካከላቸው በሀሳባቸው ሳይስማማ ቀርቶ አንደኛው

«የታዘዝኩትን ሳልፈፅም አልመለስም» በማለት ተልዕኮውን

ለማሳካት ጎዞውን ቀጠለ። 6ቱ ትተው ተመለሱ።

ጉዞውን በእርጋታ እና በመጠንቀቅ ቀጠለ። ሰራዊቱን በውሃ

ድልድዮች ተደብቆ ከተሻገረ በኋላ ማንም በማያውቀው ሁኔታ

ከ40,000 ሰራዊት እንብርት ላይ ተከሰተ።

ከሰራዊቱ መሀል ላይ ቁሞ ሩቅ እያማተረ ሲመለከት ከርቀት ነጭ

ድንኳን እና ከደጁ የቆመ የንጉሳን ፈረሰ ከአይኑ ገባ።

«ይህ የጦር አዛዣቸው የሩስቱም ድንኳን መሆን አለበት» ብሎ ወደ

ድንኳኑ ተጠግቶ ሌሊቱ ፅልመቱን ለምድር እስኪያልብስ እዝያው

ቁጭ አለ።

ፀሀይ ጠልቃ ምድር በፅልመት ስትወረር፣ ሰራዊቱ ከብርዱ

ጭጋግ ሽሽት ከየድንኳኖቻቸው ሲወሸቁ፤ ወጣቱ ሰይፉን

ከማንገቻው መዝዞ ወደ አዛዡ ድንኳን አመራ።

ከድንኳኑ ደጅ ሲደርስም የድንኳኑን ማዋቀርያ ገመዶች በሰይፉ

ቆራርጦ ሙሉ ድንኳኑ በአዳሪያኑ ላይ ሲወድቅ እሱ ደጅ ላይ

የታሰረውን ፈረስ ፈትቶ ጎዞውን ቀጠለ።

ፈጣን ፈረሰኞች ኮቴውን ተከትለው ያሯርጡት ጀመር፤ ከፈረስ

ጀርባ ያደገው የዐረብያ ብላቴናውም አሸዋውን እያቦነነ ከፊታቸው

ይከንፋል።

በመጨረሻም ከሁሉም ርቆ ሶስት ፈረሰኞች ብቻ ሲያሯርጡ

ደረሱበት። ከሶስቱ ፈረሰኞች የግድ አንዱን ይዞ ወደ አሚሩ መሄድ

ስለሚጠበቅበት ሊያጃጅላቸው ፈልጎ ሲደርሱበት እያመለጣቸው፤

በጣም ሲራራቁ እየጠበቃቸው ከክልላቸው አስወጣቸው።

ከዝያም ዞሮ ሰይፍ ተማዘዛቸው፤ ብዙም ሳይቆይ ሁለቱን ገድሎ

አንዱን አስሮ ይዞት ከፊት ከፊት እየነዳው ጉዞ ወደ አሚሩ ጀመረ።

ልክ የሙስሊሞችን ሰራዊት ደርሶ ምርኮኛውን ከአሚሩ ፊት

ሲያቆመው ምርኮኛው ለአሚሩ፦ «ከለላህን ስጠኝ እኔም

ዕውነታውን ላውራ» አለው።

«እኛ የዕውነት ህዝቦች ነን፤ ከላላችንን የምንሰጥህ እማትዋሸን

እንደሆን ነው» አለው አሚሩ።

ንግግሩን ቀጠለ፦ «እስቲ ስለ ፐርሺያ ሰራዊቶች ንገረኝ»

ምርኮኛው፦ «ስለ ፐርሺያ ሰራዊት ስብጥር ከመናገሬ በፊት ስለ

ጀግናው ጓድህ ላውጋህ።

ከልጅነቴ አንስቶ የጦርነት ሜዳ ላይ ነው ያደግኩት እንዲህ አይነት

ሰው አይቼም አላውቅም። ሁለት ጠንካራ የሰራዊት ቡድኖችን

አልፎ በመግባት የአዛዣችንን ድንኳን ቆራርጦ ጣለ'ና ፈረሱን ይዞ

ጋለበ።

ለ3 ሁነን እስከ መጨረሻ ተከታተልነው። ከፈረሱ ወርዶ

ተፋለመን'ና የ1000 ፈረሰኛ ግምት የምንሰጠውን ጀግናችንን

ገደለው።

ሁለተኛውንም የጦር መኳንንት በ1000 የምንገምተው ሲሆን

እሱንም እያየሁ ገደለው። ሁለቱም ያጎቶቼ ልጆች ነበሩ።

ይህ ድርጊቱ እልህ በልቤ ቋጥሬ ልገድለው ባለ በሌለ ጉልበቴ

እንዳሯሩጠው አስገደደኝ። የኔ አይነት ጉልበታም ከወታደሩ ይኖራል

ብዬ ባልገምትም ባላሰብኩት መልኩ የዚህ ልጅ ምርኮኛ ሆኜ

መጣሁ።

የዚህ አይነት ጀግና አንድ ካላችሁ መቼም አትሸነፉም» አላቸው።

በመጨረሻም እስልምናን ተቀበለ።

የሙስሊሞቹ ወታደሮችም ምድር አንቀጥቃጭ የሆነ ጦርነት

አድርገው ፐርሺያን ሙሉ በሙሉ ደምስሰው ድልን ተቀዳጁ።

ያ ጀግናው ሰሓቢይም ስሙ ጡለይሃ ቢን ኩወይሊድ ዱንያ

እስካለች ድረስ ሲወሳ ይኖራል።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group