UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

⭕️ ሷሊህ ልጅና የማይቋረጥ ውለታው‼️

የወለዱት ልጅ የተስተካከለ ጊዜ ለወላጆቹ የአይን ማረፊያ ይሆናል ውለታውም ከምድራዊ ህይወት እስከ ዘላለማዊ አኺራ ይደርሳል

ለዚህም እያንዳንዱ ሙስሊም ሷሊህ ልጅ እንዲኖረው ይመኛል

ምክንያቱም ሷሊህ ልጅ ወላጆቹ በህይወት ቢኖሩም ቢሞቱ መልካምነቱና ጥቅሙ አይቋረጥባቸውም

ልጅ ሲበላሽ ለወላጆቹ  የህይወት መራራ እንዲቀምሱ ከማድረጉ ባሻገር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የመሞታቸው ሰበብ ሊሆንም ይችላል

ሷሊህ ልጅ ግን  የወላጆቹ  የደከመ ተስፋ እንዲለመልም ያደርጋል ሷሊህ ልጅ የተቸሩ ወላጆች "ትናንት ያሳደግኩት ልጄ ዛሬ እያሳደገኝ ነው" የሚል የደስታና የተስፋ እስትንፋስ ከአንደበታቸው ትሰማለህ

ሷሊህ ልጅ ለወላጆቹ  ምንም ያህል ቢለፋ ሰለቸኝ ደከመኝ ብሎ የሚያማርር ሳይሆን ሁል ጊዜ ጉድለቱንና ድክመቱን እያሰበ ራሱን የሚወቅስ እንደዚሁ የወላጆቹን ልፋት  ከፊት ለፊቱ በማየት

{ رَّبِّ ٱرْحَمْهُمَا كَمَا رَبَّيَانِى صَغِيرًا ﴾

"ጌታዬ ሆዬ ልጅ ሆኜ ተንከባክበው እንዳሳደጉኝ ወላጆቼ እዘንላቸው"

እያለ አዘኔታው የሚያንፀባርቅና ዱዐ የሚያደርግ ነው

የወለዱት ልጅ የተስተካከለ ጊዜ ወላጆች ቀድመው ቢሞቱ ወላጆቹን ቀብሮ የሚረሳ አይደለም

ይልቁንስ  ሰደቃ በማድረግና  ዱዐ በማብዛት ለወላጆቹ ከፍታን ይጨምራል

አንድ ሰው ሲሞት ከመልካም ስራ ሁሉ ይቋረጣል ሶስት ነገራቶች ሲቀር ከነዚህም አንዱ ሷሊህ ልጅ ኖሮ ዱዐ ሲያደርግላቸው ወላጆች ቢሞቱም ከመልካም ስራ ግን አይቋረጡም 

ነብያችን ﷺ እንዲህ ይላሉ

" إِذَا مَاتَ الْإِنْسَانُ انْقَطَعَ عَنْهُ عَمَلُهُ إِلَّا مِنْ ثَلَاثَةٍ ؛ إِلَّا مِنْ صَدَقَةٍ جَارِيَةٍ، أَوْ عِلْمٍ يُنْتَفَعُ بِهِ، أَوْ وَلَدٍ صَالِحٍ يَدْعُو لَهُ "

"አንድ ሰው ሲሞት ስራው ሁሉ ይቋረጣል ሶስት ነገር ሲቀር.... ዱዐ የሚያደርግለት ሷሊህ ልጅ"

ስለዚህ የሷሊህ ልጅ ጥቅሙ ምድራዊ ህይወት ላይ ብቻ ያጠረ ሳይሆን ለዘላለማዊ ሀገር ይተርፋል

ለዚህም ነው ከአባታችን አደም ጀምሮ ነብያቶችና ሙእሚኖች ትኩረት ሰጥተው ሷሊህ ልጅ እንዲረዝቃቸው ጌታቸውን የሚማፀኑት

አባታችን አደምና እናታችን ሀዋ ተገናኝተው ልጅ የተረገዘላቸው ጊዜ ሷሊህ እንዲያደርግላቸው ጌታቸውን ተማፀኑ

ጉዳዩ ትኩረት የሚፈልግ በመሆኑ ጌታችን በቁርአን ሲያስተላልፍልን እንዲህ ይላል

فَلَمَّآ أَثْقَلَت دَّعَوَا ٱللَّهَ رَبَّهُمَا لَئِنْ ءَاتَيْتَنَا صَٰلِحًا لَّنَكُونَنَّ مِنَ ٱلشَّٰكِرِينَ ﴾

እናታችን ሀዋ  ያረገዘችውን  "ግልፅ በሆነ ጊዜ ጌታቸው اللهን ሷሊህ ልጅ ከሰጠህን አመስጋኝ እንሆናለን በማለት  ተማፀኑ"  ይላል

ነብዩ الله ዘከሪያ አርጅተው እንዲሁ ባለቤታቸውም ያረጀች ከመሆኗ ጋር  ሷሊህ ልጅ እንዲኖራቸው ጉጉታቸው በጣም ድካ ሲደርስ  ጌታቸውን ሷሊህ ልጅ እንዲረዝቃቸው ተማፀኑ

ይህንንም ጌታችን በቁርአኑ ሲገልፀው እንዲህ ይላል

قَالَ رَبِّ هَبْ لِى مِن لَّدُنكَ ذُرِّيَّةً طَيِّبَةً ۖ إِنَّكَ سَمِيعُ ٱلدُّعَآءِ ﴾

"ጌታዬ ሆይ! ካንተ ዘንድ ሷሊህ  ልጅ ስጠኝ "

ይህ "ذُرِّيَّةً طَيِّبَةً"  ኢብኑ ከሲር: ሷሊህ ልጅ በሚል ፈስረውታል

ጌታችን ልጅ እንዲሰጠን ብቻ ሳይሆን ሷሊህ ልጅ እንዲሰጠን ነው መጠየቅ ያለብን

አንተ ጌታህን ታዘዝ ሷሊህ ልጆች እንዲለግስህ ዘወትር ጠይቀው እንጂ ጌታህ ይሰጥሀል

ከራስህ ልጆች ባታገኘው ከልጅ ልጆችህ አታጣውም አንተ ብቻ ሷሊህ ባሪያ ሆነህ የሚጠበቅብህን ሰበብ አድርስ ዱዐንም አትርሳ

ነብያችን ሙሀመድﷺ  ስለራሳቸው ሲናገሩ

ነ   "دَعْوَةُ أَبِي إِبْرَاهِيمَ"

"የአባቴ የኢብራሂም ዱዐ ነኝ" አሉ

ነብዩ الله ኢብራሂም ያደረጉት ዱዐ የልጅ ልጅ እየተባለ ከ20 ጊዜ በላይ  የሆኑት ነብያችን ሙሀመድﷺ ላይ አገኙት

ጌታቻን በተከበረው ቁርአኑ የሙእሚኖችን ዱዐ ሲገልፅ ከዱዐቸው ውስጥ ይህንን እንደሚገኝ ይገልፃል:-

{رَبَّنَا هَبْ لَنَا مِنْ أَزْوَٰجِنَا وَذُرِّيَّٰتِنَا قُرَّةَ أَعْيُنٍ وَٱجْعَلْنَا لِلْمُتَّقِينَ إِمَامًا ﴾

"ጌታችን ሆይ! የአይናችን ማረፊያ የሚሆኑ ጓደኞች, ባለቤቶችና ልጆች ስጠን "

በማለት የሚማፀኑ ናቸው ይለናል ሙእሚኖች

አ "أَزْوَٰجِنَا" የሚለው ጓደኛ እና ባለቤት በሚል ተፈስሯል

ስለዚህ አንተ ሳትቸኩልና ሳትሰላች ጌታህን ተማፀን እንጂ በልጆችህ ወይም በልጅ ልጆችህ አታጣውም

👌ሰበቦችንም አትርሳ

ከሰበቦቹ አንዱ ሷሊህ የትዳር አጋር መፈለግ ነው

ሳይዘወጅ ሷሊህ ልጅ እንዲሰጠኝ ዱዐ አድርጉልኝ እንዳለው ሰውዬ መሆን ሳይሆን

አንድ ሰው  ሷሊህ ልጅ ለማግኘት የግድ መዘወጅ ይኖርበታል

👌 ሷሊህ ልጅ ለማግኘት በጣም ብዙ ሰበቦች አሉት إن شاء الله  በሌላ ጊዜ የምንመለስበት ይሆናል

.                      وبالله التوفيق

https://t.me/+SZr_FCsW3uUgu6G7

https://t.me/+SZr_FCsW3uUgu6G7

Telegram: Join Group Chat

Telegram: Join Group Chat

#እስልምናን በእዉቀት ተመራበት እንጂ አላዋቂዎች በሚዘላብዱትና በሚያታልሉት እየተታለልክ ዲንህን በእዉቀት ካለመመራት ታቀብ# ኹጥባዎች ሙሐደራዎች ነሲሐዎች ደርሶች እና አስገራሚ እና አስተማሪ የሆኑ ታሪኮች የነብያቶች፣የሰሐቦች፣የታበችዮች ታሪክ ያገኛሉ
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
kamil yemer shared a
Translation is not possible.

🛑 በነቢዩ ሙሀመድ [ﷺ] ላይ ሰለዋት ሲያደርጉ ሀጥያት እንደሚራገፍልዎ ያውቃሉ?

የአላህ መልዕክተኛ(ሰዓወ) እንዲህ ብለዋል:–

🛑 "በኔ ላይ አንዴ ሰለዋትን ላወረደ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድበታል። አስር ኃጥያቶችንም ያራግፍለታል።"

"Namni anarrattii salawaata tokko buuse Rabbiin isarratti salawaata kudhan buusa. Badii kudhan isaaf dhiisa."

Nabi Muhammad(saw)

Send as a message
Share on my page
Share in the group
kamil yemer shared a
Translation is not possible.

ኡስታዛችን ሸይኻችን በክብር ጀናዛቸው

ተሸኘ። አላህ ይማራቸው ጀነተል ፊርደውስን ይወፍቃቸው ያረብ!🤲🤲😥😥😥

መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉት

6 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
kamil yemer shared a
Translation is not possible.

እስራኤል እና ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለሁለት ቀናት ለማራዘም መስማማታቸውን ኳታር አስታወቀች

ለአራተኛ ተከታታይ ምሽት የተወሰኑ የእስራኤል ታጋቾች በሃማስ እና በእስራኤል መካከል በተደረገው ጊዜያዊ የእርቅ ስምምነት መሰረት ከፍልስጤማውያን እስረኞች ጋር ተለዋውጠዋል። 33 ፍልስጤማውያን ከእስራኤል እስር ቤት የተፈቱት በሃገር ውስጥ አቆጣጠር ከእኩለ ሌሊት በኋላ ነው። ቀደም ሲል ሃማስ 11 እስራኤላውያንን እስረኞችን የለቀቀ ሲሆን የፈረንሳይ፣ የጀርመን ወይም የአርጀንቲና ጥምር ዜግነት ያላቸው እስራኤላውያን መሆናቸው ታውቋል።

ትላንት የኳታር አሸምጋዮች እንዳሉት የእርቅ ስምምነቱ ለሁለት ቀናት መራዘሙን አስታውቀዋል። ኋይት ሀውስ መራዘሙን አረጋግጧል። ነገርግን እስራኤል በዚህ ዙሪያ ማረጋገጫ ከመስጠት ዘግይታለች።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለጋዛ ዜጎች የሚደርሰውን አስቸኳይ የእርዳታ አቅርቦት ለመጨመር የተኩስ አቁሙን ተጠቅሞበታል።

ነገር ግን የሚመጣው የረድኤት ድጋፎች እየቀነሱ መሆናቸውን አስጠንቅቋል። በጋዛ የሚኖሩ ሰዎች በትግሉ ወቅት እቃዎችን ለማግኘት እና በግዛቱ ውስጥ ለመዘዋወር በብዙ አጋጣሚዎች ወደ ቤታቸው ለመመለስ እና ጉዳቱን ለመገምገም እና የአየር ሁኔታው ዝናባማ እና ነፋሻማ በሚሆንበት ጊዜ የክረምት ልብሶችን በመፈለግ ላይ ቆይተዋል።

በቅርብ ቀናት ውስጥ በጋዛ እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ  የሙቀት መጠኑን ቀንሷል። ሁኔታው ግን በጣም መጥፎ ነው የተባለ ሲሆን በተለይ በድንኳን ውስጥ የሚኖሩ የተፈናቀሉ ቤተሰቦች በቂ የሚሞቅ ልብስ የላቸውም የሚል መረጃ ከስፍራ ይወጣል። ብዙዎቹ ከፍርስራሹ ስር ያረጁ ልብሶችን እና ብርድ ልብሶችን ለመፈለግ ወደ ፈራረሱ ቤታቸው ሲመለሱ የሚያሳይ ምስሎች እየተመላከቱ ይገኛል።

በአበረ ስሜነህ

#ዳጉ_ጆርናል #palestine #غزة #freepalestine #فلسطين #gazaunderattack #غزة_تحت_القصف #غزة_الآن

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group