Translation is not possible.

እስራኤል እና ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ለሁለት ቀናት ለማራዘም መስማማታቸውን ኳታር አስታወቀች

ለአራተኛ ተከታታይ ምሽት የተወሰኑ የእስራኤል ታጋቾች በሃማስ እና በእስራኤል መካከል በተደረገው ጊዜያዊ የእርቅ ስምምነት መሰረት ከፍልስጤማውያን እስረኞች ጋር ተለዋውጠዋል። 33 ፍልስጤማውያን ከእስራኤል እስር ቤት የተፈቱት በሃገር ውስጥ አቆጣጠር ከእኩለ ሌሊት በኋላ ነው። ቀደም ሲል ሃማስ 11 እስራኤላውያንን እስረኞችን የለቀቀ ሲሆን የፈረንሳይ፣ የጀርመን ወይም የአርጀንቲና ጥምር ዜግነት ያላቸው እስራኤላውያን መሆናቸው ታውቋል።

ትላንት የኳታር አሸምጋዮች እንዳሉት የእርቅ ስምምነቱ ለሁለት ቀናት መራዘሙን አስታውቀዋል። ኋይት ሀውስ መራዘሙን አረጋግጧል። ነገርግን እስራኤል በዚህ ዙሪያ ማረጋገጫ ከመስጠት ዘግይታለች።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለጋዛ ዜጎች የሚደርሰውን አስቸኳይ የእርዳታ አቅርቦት ለመጨመር የተኩስ አቁሙን ተጠቅሞበታል።

ነገር ግን የሚመጣው የረድኤት ድጋፎች እየቀነሱ መሆናቸውን አስጠንቅቋል። በጋዛ የሚኖሩ ሰዎች በትግሉ ወቅት እቃዎችን ለማግኘት እና በግዛቱ ውስጥ ለመዘዋወር በብዙ አጋጣሚዎች ወደ ቤታቸው ለመመለስ እና ጉዳቱን ለመገምገም እና የአየር ሁኔታው ዝናባማ እና ነፋሻማ በሚሆንበት ጊዜ የክረምት ልብሶችን በመፈለግ ላይ ቆይተዋል።

በቅርብ ቀናት ውስጥ በጋዛ እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ  የሙቀት መጠኑን ቀንሷል። ሁኔታው ግን በጣም መጥፎ ነው የተባለ ሲሆን በተለይ በድንኳን ውስጥ የሚኖሩ የተፈናቀሉ ቤተሰቦች በቂ የሚሞቅ ልብስ የላቸውም የሚል መረጃ ከስፍራ ይወጣል። ብዙዎቹ ከፍርስራሹ ስር ያረጁ ልብሶችን እና ብርድ ልብሶችን ለመፈለግ ወደ ፈራረሱ ቤታቸው ሲመለሱ የሚያሳይ ምስሎች እየተመላከቱ ይገኛል።

በአበረ ስሜነህ

#ዳጉ_ጆርናል #palestine #غزة #freepalestine #فلسطين #gazaunderattack #غزة_تحت_القصف #غزة_الآن

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group