በፒያሳ የሚገኘው ጥንታዊው የሙስሊም ት/ቤት የመጀመሪያው አወሊያ ሊፈርስ መሆኑ ተሰማ
በአወሊያ አዳራሽ በነበረው የወላጆች ስብሰባ ስለ አወሊያ የፒያሳው ቅርንጫፍ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ወቅታዊ ሁኔታ በትምህርት ዙሪያ በተጠራ ስብሰባ በበርካታ ወላጆች ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች ሲነሱ እንደነበር ተሰምቷል።
ወላጆቹ ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከልም ልጆቸው የት/ቤታቸው የመፍረስ አደጋ ስጋት እንደፈጠረባቸው አንስተው ስለጥንታዊ ተቋማቸው ወቅታዊ ሁኔታ ዘርዘር ያሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ለተቋሙ አስተዳደር ጥያቄ አቅርበዋል።
በጉዳዩ ላይ ለወላጆች ማብራሪያ የሰጡት የአወሊያ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰይድ አስማረም ጉዳዩ እውነት እንደሆነ አረጋግጠው በሂደቱ ላይ ግን ጉዳዩን የሚከታተል በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ስር አምስት አባላት ያሉት በኡስታዝ አቡበከር አህመድ ሰብሳቢነትና በኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ም/ሰብሳቢነት የሚመራ ኮሚቴ ክትትል እየተደረገበት እንደሆነ ስራ አስኪያጁ ለሬዲዮ ነጃሺ ገልጸዋል።
ኮሚቴው ከተዋቀረ ከ2 ወራት በላይ እንዳስቆጠረ ያወሱት ስራ አስኪያጁ ከመንግስት አካላት ጋር የቅርብ ጊዜ ስብሰባውን ያለፈው አርብ ጥቅምት 22/2017 እንዳደረገ አብራርተዋል። ስራ አስኪያጁ ``ሙስሊሙ የመንግስትና የልማት ደጋፊ`` መሆኑን ገልጸው ኮሚቴው ተለዋጭ ቦታ ለመረከብ አማራጭ ቦታዎችን እያማተረና የስምምነት ጫፍ ላይ እንደደረሰ`` አውስተዋል።
ስራ አስኪያጁ በገለጻቸው ት/ቤቱ በ2016 የት/ት ዘመን ክልላዊ ፈትና 100% የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን በማሳለፍ ውጤታማ የሆነ ት/ቤት ሲሆን በክ/ከተማ ደረጃም የዋንጫ ሽልማት እንዳገኘ ገልጸዋል።
ይህ ቦታ በዓለም አቀፍ የሙስሊም ሊግ ዋና ጸሃፊና በአዲስ አበባ ከንቲባ የጠ/ም/ቤቱ ባሉበት የዛሬ ዓመት ገደማ በአዲስ መልክ እንዲገነባ የ900,0000,000 /የዘጠኝ መቶ ሚሊዮን/ ብር የ19 ወለል (ፎቅ) ግንባታ ሊሰራበት የመሰረተ-ድንጋይ እንደተጣለበት በበርካታ ሚዲያዎች መዘገቡን በዛሬው ዕለት በነበረው ገለጻ ተወስቷል።
ለዚሁ አዲሱ ግንባታ ከሚያስፈልገው ተጨማሪ 5ሺ ካሬ ገደማም የአዲስ አበባ መሬት ማኔጅመንት በስሩ ከሚያስተዳድራቸው ቦታዎች ከ3ሺህ ካሬ በላይ የሚሆነውን ቦታ መስጠቱን የመሰረት ድንጋዩ በጣለበት ዕለት ከንቲባዋ ይፋ ማድረጋቸው አይዘነጋም።
Via ሀሩን ሚዲያ
#ዳጉ_ጆርናል