abu umer Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

abu umer shared a
Translation is not possible.

ይሄን ቻሌንጅ ተቀላቀሉ

ምንፅ ከሙራድ ታደሰ የቴሌግራም ገፅ የተወሰደ

ይህንን ቻሌንጅ ተቀላቀሉ‼

==================

✍ ይህንን ባለ 15 ገፅ የመንግስትንና የኃይማኖቶችን ግንኙነት በተመለከተ በዝርዝር ያብራራል የተባለለትን አዲሱን ረቂቅ አዋጅ ሶፍት ኮፒ በስልካችሁ ላይ ላለ ሰው ሁሉ፣ በምታገኙት ግሩፕና ቻነል እንዲሁም በማንኛውም ገፅ ላይ በማሰራጨት መረጃው በእያንዳንዱ ሙስሊም እጅ ላይ ደርሶ እንዲያነበው እናድርግ።

ለዚህ ረቂቅ አዋጅ ግብዓት ይሆን ዘንድ የቀረበውን ባለ 164 ገፅ ጥናት ማንበብ ለሚፈልግም ሶፍት ኮፒው በዚህ ሊንክ ይገኛል።

https://t.me/MuradTadesse/35708

*

ሰው ጽሑፉን ዝም ብሎ ቢያነበውም ከላይ ሲመለከታቸው አንቀፆቹ ጤነኛ ሊመስሉት ስለሚችሉ፤ ፍንጭ ይሰጠው ዘንድ ረቂቅ አዋጁ ከኛ ከሙስሊሞች ጋር የሚያጋጩትንና ጥያቄ የሚያጭሩ 15+ ነጥቦች የተጠቀሱበትን ይህንን ጽሑፍም ጨምሩለት።

https://t.me/MuradTadesse/35742

ይህንን የአዲሱን ረቂቅ አዋጅ PDF ለሁሉም በማሰራጨት መረጃው እንዲደርሰው እናድርግ። የላ ቻሌንጃችን ይጀመር!

አብዛሃኛው ሰው ከጀርባ ምን እየተካሄደ እንዳለ መረጃው የለውም። ጭራሽ አዲስ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ራሱ እንኳን ከመረጃው የራቀው ማኅበረሰብ ሚዲያ ላይ አለን የሚለው ራሱ በበቂ ሁኔታ የሰማ አይመስለኝም። ወሬውን ቢሰማም ዶክመንቱ በተጨባጭ ያልደረሰው ብዙ ነውና ይህንን በማድረግ ግንዛቤ እንፍጠር።

የፌዴራሉ መጅሊስም በዚህ ጉዳይ ተቃውሞ ያወጣውን ባለ 4 ገፅ መግለጫ አያይዘን እናሰራጨው። መግለጫው በዚህ ሊንክ ይገኛል።

https://t.me/MuradTadesse/35632?single

ከተቋማችንም ጎን እንቁም።

የላ! ከአሁኑ ይጀመርና ያሰራጨ ሰው ለማነቃቂያ ስክሪን ሹቱን ኮመንት ላይ አስቀምጡት!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
abu umer shared a
1 week Translate
Translation is not possible.

ሃናን ባቡልኸይር እያለቀሰች ስለወንድማችን አብደላ ስትናገር ልቤ ተነካ ። ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ የአብደላ መታመም ምን ያህል ጎዶለነት እንደሚፈጥር ሲገልጽ አየሁ ። በግሌ ወንድማችን አብደላን ከዚህ ቀደም አላውቀውም ነበር ። ግን በኸይር ስራዎች ላይ የሚያስተባብሩ ወንድም እና እህቶቻችን በደንብ ያውቁታል ። አዎ አንዳንድ ሰዎች አሉ ። ከፊት ወጥተው በሚዲያ የማይታወቁ ። ከጀርባ ሁነው በገንዘባቸውን ባላቸው ነገር ሁሉ ለኡማው የሚያገልግሉ ። ኸይር የሚሰሩ ወንድም እና እህቶችን ይኼው መኪናየን ውሰዱ ፣ይሄው ገንዘቤም ለኸይር ስራችሁ ተጠቀሙበት የሚሉ ። አብደላ የዚያ አይነት ሰው እንደሆነ ነው ያወቅኩት ።

ዱንያ የፈተና ሀገር ናት ። እርሱ እና ቤተሰቦቹ ያላቸውን ሁሉ በህክምና ጨረሱ ። ዛሬ ላይ እዚህ ደረሱ ። ለዚህ ወንድማችን እዚህ ደረጃም መድረስ አልነበርብንም ። ሁላችንም ተረባርበን የምንችለውን እናድርግ ።

ወንድም አብደላን ለማገዝ

የአካውንት ስም:— ፋጡማ ነስሩ ሃሰን

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:— 1000307233968

አዋሽ ባንክ :— 014251336744800

ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል:— 1338403800001

አቢሲኒያ:— 186746977

ዘምዘም ባንክ:- 0040743420101

ንብ ባንክ፡- 7000057909922

ዳሽን ባንክ :- 2907571242711

የአካውንት ስም:— አብደላህ በድሩ

ሂጅራ ባንክ :_ 1000643150001

#муслим

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
abu umer shared a
Translation is not possible.

‍ 🔰 ንስር እንደ ጥንካሬ

ሰማዩ ሲጠቁር ደመናው ወጀቡንም ሲያይል ሌሎች አዕዋፍት በየ አለቱና በየ ጢሻው ውስጥ ይደበቃሉ።

በቤት ታዛ ስርም ይደበቃሉ። ንስር ግን ደስ ይለዋል ወጀቡም ሲጀምር ንፋሱን በመሟገት የራሱን ጥንካሬ ይለካበታል።

የነፋሱን አቅጣጫ በመከተልም ይበራል። ራሱን ወደ ላይ ለማምጠቅ እና የከፍታውን ጫፍ ለመጨበጥ ይጠቀምበታል።

በዚህም ጥንካሬውን ይለካበታል። ንስር አሞራ ከአዕዋፍት ዘር ለ70 አመት የህይወት ዘመን የመቆየት እድል አለው።

ንስር አሞራ 70 አመት እድሜውን ለመኖር በ40ኛ አመቱ ላይ ከፍተኛ መሰዕዋትነት በሚጠይቅ ውሳኔ ላይ ይወድቃል። የንስር አሞራ የእግር ጥፍር በአግባቡ መስራች የሚችለው ለ40 አመት ብቻ ነው።

ንስር አሞራ ከተፈለፈለ ጀምሮ 40 አመት ከኖረ በኋላ በሰውነት ክፍሉ ላይ በሚታየው ለውጥ የተነሳ የአፍ መንቁሩ፣ የእግር ጥፍሩና ላባው እንደ በፊቱ ሊያገለግሉለት አይችሉም።

የእግር ጥፍሩ ደካማ በመሆኑ አደኑን በደንብ አይዝለትም። ረጅምና ስል መንቁሩ ይታጠፋል። ላባው በሰውነቱ ይለጣጠፍና ክብደት ስለ ሚጨምር እንደ ልቡ አይበርም።

በዚህ ወቅት ንስር አሞራ በሁለት ውሳኔዎች ላይ ይወድቃል።

ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠባበቅ! ወይም ደግሞ 5 ወር የሚፈጅበት ስቃይና መከራ ያለበት መሰዕዋትነት በመክፈል ቀሪ ዘመኑን እንደ ወጣት ንስር በደስታ መኖር!

30 ተጨማሪ እድሜ ለመኖር የ5 ወር መሰእዋትነት ይከፍላል።

ንስር አሞራ ቀሪ 30 አመት ለመኖር ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት ጎጆ ይቀልሳል። ንስር አሞራ በተራራው ላይ ጎጆውን ከቀለሰ በኋላ የመጀመሪያ ስራው የአፍ መንቁት ከአለት ጋር በመፋቅ ነቅሎ መጣል ነው።  ይህ ከፍተኛ ህመም እና ስቃይ አለው። ይሁን እንጂ አዲስ መንቁር ለማውጣት ይህን ማድረግ የግድ ነው። ከዚያ አዲስ መንቁር ከወጣለት ወይም ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁር አሮጌው የእግር ጥፍሩን ነቅሎ ይጥለዋል።

አዲሱ የእግር ጥፍሩን ከበቀለለት በኋላ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳሪያ በመጠቀም በሰውነቱ የተጣበቀውን ጥቅጥቅ ያለ ላባው ነቃቅሎ ጥሎ አዲስ እንዲበቅል ያደርጋል። ይህ ህመምና መከራ ያለው ድርጊት ነው።

ከዚያም የ5 ወር ማገገሚያ ጊዜ ካጠናቀቀ በኋላ እንደገና ራስን የመውለድ የትግል ሂደት ይጠናቀቅና ተጨማሪ 30 አመቱን በሰማይ እየበረረ እና እያደነ በደስታ ይኖራል።

➤ አንተም መከራና ፈተናን አትፍራ።

➤ በወጀብ እና በአውሎ ነፋስ ቢሆንም መንገድ አለና መከራውን ግብግቡን  የአዳዲስ ሀሳቦች መነሻ የጥንካሬህ መለኪያ አቅምህን የምትጠቀምበት አጋጣሚ ወደ ላይ የምትመጥቅበት  ከችግር ደመናዎች በላይ የምትንሳፈፍበት እድል አድርገው።

በህይወታችን ውስጥ የምንፈልጋቸው ለውጦች  አንዳንድ ጊዜ ባስቸጋሪ እና መራራ ሁኔታዎች ውስጥ እንድናልፍ የግድ ይሉናል።

የሰው ልጅ በህይወቱ መከራ ሲገጥመው ከዚህ አስቸጋሪ ህይወት ለመውጣት ወይም ለማምለጥ ብሎም ደስተኛ ለመሆን  የህይወት ልምዱን መለወጥ አሮጌ ልምዱን፣ ትዝታዎቹን የእለት እለት ኑሮውን አሸቀንጥሮ መጣል የግድ ይለዋል። እነዚህ አሽቀንጥረን የምንጥላቸው ነገሮች ግን ለማስወገድ ከፍተኛ መሰዕዋትነት ከከፈልን እንደ ንስር ቀሪ ዘመናችን በደስታ እንኖራለን።

እንደ ሌሎች ወፎች ከመከራውንም አንሸሽ ከችግሩንም አንደበቅ መከራን ለጥንካሬ እና ለበረከት እንጠቀምበት። እንደ ንስር ከፍ ብለን እንውጣ ዝቅ አንበል።  ከፍ ባልን ቁጥር ጥሩ እይታ ይኖረናል። ታጋሽ፣ አስተዋይ፣ ቻይ ያደርገናል። ከዛ በኋላ አሮጌ አስተሳሰባችን በማያስማሙን እኔ ብቻ የሚለው ስሜታችንን የሚያለያዩን ነገሮች ወደዚያ አሽቀንጥረን ነቅለን ጥለን በሚያስማሙን እና በሚያቻችሉን እንተካቸው......!!!!!!!

✍ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇

Telegram: t.me/SharpSwords1

Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1

YouTube: youtube.com/@SharpSwords1

Instagram: Instagram.com/sharp_swords1

Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
abu umer shared a
Translation is not possible.

ከቁርኣን ልዩ ባህሪያት

ጥንቅር ኢብን አሚን

ለተከበረው ቁርአን ቀድመውት ከወረዱት ሰማያዊ መጻሕፍት የሚለይበት ልዩ ባህሪያት አሉት፡-

1. ከዚህ በፊት የወረዱት መጻሕፍት ይዘውት የነበረውን መለኮታዊ የመልእክት ጭብጥ አጠቃሎ ያካተተ መሆኑ፣ በእነዚህ የተላያዩ መጻሕፍት ተበታትነው የሚገኙ መልካምና የላቁ አስተምህሮቶች ሰብስቦ መያዙ፣ ሁሉንም ያካበበና በነርሱ ላይ ተጠባባቂ መሆኑ፣ በሌሎች መጻሕፍት ውስጥ ያሉ እውነታዎችን የሚያረጋግጥና በነርሱም ውስጥ የተደረጉ ብረዛዎችንና ቅየራዎችን የሚያጋልጥ መሆኑ። አላህ እንዲህ ብሏል፡-

‘’ ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲሆን በውነት አወረድን…’’ አልማዒዳ፡48

2. አላህ (ሱ.ወ.) ለሁሉም የሰው ልጆች፣ ለሁሉም ዘመንና ቦታ እንደሚስማማ አድረጎ ያወረደው መሆኑና ለአንድ ለተለየ ሕዝብ ብቻ ያልወረደ መሆኑ። አላህ አንዲህ ብሏል፡-

‘’ ያ በባሪያው ላይ ፉርቃንን (ቁርአንን) ለዓለማት አስፈራሪ ይኾን ዘንድ ያወረደ(አምላክ) ክብርና ጥራት ተገባው።’’

3. ቁርአን አላህ እንደሚጠብቀው ቃል የገባለት ብቸኛ መለኮታዊ መጽሐፍ መሆኑ። የተናጋሪዎች ሁሉ አሸናፊ (አላህ) እንዲህ ብሏል፡-

‘’ቁርአንን እኛው አወረድነው፣ እኛም ለርሱ ጠባቂዎቹ ነን’’ (አል-ሂጅር 9)

ይህም የሆነበት ምክንያት የሰው ልጆች ይመሩበት ዘንድ የወረደውና የአላህ የመጨረሻ ቃል የሆነው የቁርአን አስተምህሮ ዘመን ሳይሽረው ለሁልጊዜም እንዲቆይ አላህ (ሱ.ወ.) በመፈለጉ ይህንን መልእክት የመበረዝ፣ የመቀየርም ሆነ የመለወጥ አደጋ እንዳይደርስበት አላህ እራሱ ስለጠበቀው ነው።

“እርሱ (ቁርአን) አሸናፊ የሆነ መጽሀፍ ነው፤ ከበስተፊቱም ከበስተኋላውም ስህተት የማይመጣበት ከጥበበኛውና ከምስጉኑ (አላህ) የተወረደ ነው) [ፉሲለት 14፣24]

4. አላህ (ሱ.ወ.) ንግግሩ ወደ ሰው ልጅ አእምሮና ጆሮ ውስጥ እንዲሰርፅና መልእክቱ እንዲደርስ ከዚያም ወደ ተጨባጭ ተግባር እንዲቀየር ይፈልጋል። ይህ ደግሞ ቁርአን በራሱ ገር ካልሆነ በስተቀር በቀላሉ ለማስታወስና ለመረዳት ስለማይቻል አላህ ገር አድርጎታል፡-

‘’ቁርአንን ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፣ ተገንዛቢም አለን?’’ አልቀመር፡17

#gaza #palestine #freepalestine

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
abu umer shared a
Translation is not possible.

♦️መተኛትህ ካልቀረ በሱና ላይ ሁነህ ተኛ

👉ሱና የዱንያም የአሔራ ብርሀን ነው።

✅ህይወት ያለ ሱና ድቅድቅ ጨለማ ነው::

ከሱናዎቹ መካከል...

➡️ፍራሹን ጠረግ ማድረህ፣-

ነብዩ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ለመተኛት ወደ ፍራሻችሁ ስትቀርቡ በሽርጣችሁ ውስጠኛውን ክፍል ሶስት ግዜ ጠረግ አድርጉት።

ለመተግበር ወደኋላ እንዳንል አደራ!!! ከረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር ሚሰበስበን ሱናቸው ነውና

Send as a message
Share on my page
Share in the group