Translation is not possible.

‍ 🔰 ንስር እንደ ጥንካሬ

ሰማዩ ሲጠቁር ደመናው ወጀቡንም ሲያይል ሌሎች አዕዋፍት በየ አለቱና በየ ጢሻው ውስጥ ይደበቃሉ።

በቤት ታዛ ስርም ይደበቃሉ። ንስር ግን ደስ ይለዋል ወጀቡም ሲጀምር ንፋሱን በመሟገት የራሱን ጥንካሬ ይለካበታል።

የነፋሱን አቅጣጫ በመከተልም ይበራል። ራሱን ወደ ላይ ለማምጠቅ እና የከፍታውን ጫፍ ለመጨበጥ ይጠቀምበታል።

በዚህም ጥንካሬውን ይለካበታል። ንስር አሞራ ከአዕዋፍት ዘር ለ70 አመት የህይወት ዘመን የመቆየት እድል አለው።

ንስር አሞራ 70 አመት እድሜውን ለመኖር በ40ኛ አመቱ ላይ ከፍተኛ መሰዕዋትነት በሚጠይቅ ውሳኔ ላይ ይወድቃል። የንስር አሞራ የእግር ጥፍር በአግባቡ መስራች የሚችለው ለ40 አመት ብቻ ነው።

ንስር አሞራ ከተፈለፈለ ጀምሮ 40 አመት ከኖረ በኋላ በሰውነት ክፍሉ ላይ በሚታየው ለውጥ የተነሳ የአፍ መንቁሩ፣ የእግር ጥፍሩና ላባው እንደ በፊቱ ሊያገለግሉለት አይችሉም።

የእግር ጥፍሩ ደካማ በመሆኑ አደኑን በደንብ አይዝለትም። ረጅምና ስል መንቁሩ ይታጠፋል። ላባው በሰውነቱ ይለጣጠፍና ክብደት ስለ ሚጨምር እንደ ልቡ አይበርም።

በዚህ ወቅት ንስር አሞራ በሁለት ውሳኔዎች ላይ ይወድቃል።

ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠባበቅ! ወይም ደግሞ 5 ወር የሚፈጅበት ስቃይና መከራ ያለበት መሰዕዋትነት በመክፈል ቀሪ ዘመኑን እንደ ወጣት ንስር በደስታ መኖር!

30 ተጨማሪ እድሜ ለመኖር የ5 ወር መሰእዋትነት ይከፍላል።

ንስር አሞራ ቀሪ 30 አመት ለመኖር ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት ጎጆ ይቀልሳል። ንስር አሞራ በተራራው ላይ ጎጆውን ከቀለሰ በኋላ የመጀመሪያ ስራው የአፍ መንቁት ከአለት ጋር በመፋቅ ነቅሎ መጣል ነው።  ይህ ከፍተኛ ህመም እና ስቃይ አለው። ይሁን እንጂ አዲስ መንቁር ለማውጣት ይህን ማድረግ የግድ ነው። ከዚያ አዲስ መንቁር ከወጣለት ወይም ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁር አሮጌው የእግር ጥፍሩን ነቅሎ ይጥለዋል።

አዲሱ የእግር ጥፍሩን ከበቀለለት በኋላ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳሪያ በመጠቀም በሰውነቱ የተጣበቀውን ጥቅጥቅ ያለ ላባው ነቃቅሎ ጥሎ አዲስ እንዲበቅል ያደርጋል። ይህ ህመምና መከራ ያለው ድርጊት ነው።

ከዚያም የ5 ወር ማገገሚያ ጊዜ ካጠናቀቀ በኋላ እንደገና ራስን የመውለድ የትግል ሂደት ይጠናቀቅና ተጨማሪ 30 አመቱን በሰማይ እየበረረ እና እያደነ በደስታ ይኖራል።

➤ አንተም መከራና ፈተናን አትፍራ።

➤ በወጀብ እና በአውሎ ነፋስ ቢሆንም መንገድ አለና መከራውን ግብግቡን  የአዳዲስ ሀሳቦች መነሻ የጥንካሬህ መለኪያ አቅምህን የምትጠቀምበት አጋጣሚ ወደ ላይ የምትመጥቅበት  ከችግር ደመናዎች በላይ የምትንሳፈፍበት እድል አድርገው።

በህይወታችን ውስጥ የምንፈልጋቸው ለውጦች  አንዳንድ ጊዜ ባስቸጋሪ እና መራራ ሁኔታዎች ውስጥ እንድናልፍ የግድ ይሉናል።

የሰው ልጅ በህይወቱ መከራ ሲገጥመው ከዚህ አስቸጋሪ ህይወት ለመውጣት ወይም ለማምለጥ ብሎም ደስተኛ ለመሆን  የህይወት ልምዱን መለወጥ አሮጌ ልምዱን፣ ትዝታዎቹን የእለት እለት ኑሮውን አሸቀንጥሮ መጣል የግድ ይለዋል። እነዚህ አሽቀንጥረን የምንጥላቸው ነገሮች ግን ለማስወገድ ከፍተኛ መሰዕዋትነት ከከፈልን እንደ ንስር ቀሪ ዘመናችን በደስታ እንኖራለን።

እንደ ሌሎች ወፎች ከመከራውንም አንሸሽ ከችግሩንም አንደበቅ መከራን ለጥንካሬ እና ለበረከት እንጠቀምበት። እንደ ንስር ከፍ ብለን እንውጣ ዝቅ አንበል።  ከፍ ባልን ቁጥር ጥሩ እይታ ይኖረናል። ታጋሽ፣ አስተዋይ፣ ቻይ ያደርገናል። ከዛ በኋላ አሮጌ አስተሳሰባችን በማያስማሙን እኔ ብቻ የሚለው ስሜታችንን የሚያለያዩን ነገሮች ወደዚያ አሽቀንጥረን ነቅለን ጥለን በሚያስማሙን እና በሚያቻችሉን እንተካቸው......!!!!!!!

✍ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇

Telegram: t.me/SharpSwords1

Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1

YouTube: youtube.com/@SharpSwords1

Instagram: Instagram.com/sharp_swords1

Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group