በትናንሽ ስህተቶች ብቻ ለም እንበሻሸቃለን⁉️
እስቲ ትላንት አብረን ያሳለፍነውን ጊዜ እናስበው!
እስቲ ትላንት በጥሩ ሁኔታ ተጎራብተን የኖርነባቸውን አመታቶች ቆም ብለን እናስባቸው።
ለምን በትንሽ ስህተቱ ወንድማችንን እንራቀው!?
ለምን በትንሽ ስህተቷ እህታችንን እንራቃት!?
የራቅናቸውን ሰዎች እንደ ነጭ ወረቀት ብናስባቸው፤ ይህ ነጭ ወረቀት መሬት ወደቀ እንበል። ወረቀቱ ይዞ የተነሳው አቧራ ትንሽ ነው (የቆሸሸው የወረቀቱ ክፍል ኢምንት ነው)።
ያ! የቀረው ወይም አቧራ ያልነካው ቦታ ሁሉ እኛ የጠላነው ሰው ጥሩ ጎኑ ነው። የሱ ስህተት ደግሞ ያቺ ትንሿ አቧራ የነካት ቦታ ብቻ ናት።
ታዲያ ለዚህች ኢምንት ነገር ብለን ያሳለፍናቸውን በጎ ነገራቶችን በሙሉ ለምን እንርሳቸው⁉️
ለምንስ በዚህች ትንሽ ስህተቱ ብቻ እንበሻሸቅ?
ለምንስ እዚህ ግባ በማይባል ስህተት እንገፋፋለን፣ እንባላለን፣ እንጎሻሸማለን⁉️
ያን ትንሽ አቧራ ከማየት አቧራ ያልነካውን ትልቁን ቦታ ብናይስ? ግዴላችሁም በቃ ለሰው ልጅ ፍቅር እንስጥ፤ በማይረባ ነገር አንበሻሸቅ።
ለሰው ልጅ ፍቅርህንና አክብሮትህን የምትሰጠው ደግሞ ከገንዘብህ ወይም ከዕድሜህ ሳይሆን ከንፁህ ልብህ ነው!!
ግን ብዙዎቻችን ፍቅርን ከገነዘባችንና ከዕድሜያችን ቀንሰን የምንሰጥ ይመስለንና ለሰው ልጅ.......
ፍቅርን፣ አክብሮትን፣ ታማኝነትን፣ ሐቀኝነትን፣ ይቅር ባይነትን፣ መርዳትንና መደገፍን፣ መቻቻልን፣ ምክርንና ተግሳፅን እንሰስታለን፤ አረ አንደውም ይባስ ብለን እንደ አውሬ ለብቻችን መኖርን እንመርጣለን።
⇒ የተገላቢጦሽ ሆኖ ጭካኔ እና እራስ ወዳድነት የጥንካሬ ምልክቶች፤ የዋህነትና ይቅርባይነት የሞኝነት ባህሪ ይመስሉናል። እንደ መልካም ስራ ጥንካሬን የሚፈትን ምን ነገር አለ?
- እየተጠሉ መወደድ፤
- እየተዋረዱ ክብር መስጠት፤
- በጥላቻ መንፈስ እየታዩ ፍቅርን መስጠት
- እየተገፉ አለሁኝ ማለት፤ ጠንካራ ማንነትን ይጠይቃል።
⛔ ትዕግስት እንደ ፍርሃት፤ ይቅር ባይነት እንደ ውርደት፤ አክብሮት እንደ ማስመሰል እየተቆጠረ መልካምነት ከዘመኑ ጋር የማይሄድ ባህሪ እየመሰለን እየሸሸነው ነው።
⇒ ብዙዎቻችን ደግነትን እንደ ደካማ ጎን አድረገን እናየዋለን።
ደግነት ማለት ማየት ለማይችሉ አይን፤ መስማት ለማይችሉ ጆሮ ሆኖ የሚያገለግል መሣሪያ መሆኑን ማን በነገረን!!!
ደግነት የሚጀመረው ደግሞ በልባችን ስንመራ፣
o እንደራሳችን ቆጥረን ስለሌሎች ስንጨነቅ፣
o ዉለታን ሳንፈልግ ስናገለግል፣
o ሰው ስንቀን እኛ ግን ስናከብር
o ምላሽ ሳንጠብቅ መስጠት ስንጀምር ነው።
ዋሽተን ማሳመን ብልጠት፤ እራሳችንን ማስቀደም ብልህንት፤ ሌሎችን ማዋረድ ክብር የሚያስገኝልን እየመሰለን ከሰብዓዊው ማንነታችን ቀስ በቀስ እንሸሻለን። እውነታው ግን ይቅር እንደማለት፤ ሌሎችን እደማክበር፤
ፍቅር ለሚገባው ፍቅር እንደመስጠት ፈታኝ እና ጥንካሬን የሚጠይቁ ምን ነገሮች አሉ⁉
⇒ ግዴላችሁም ወንድምና እህቶቼ እስቲ ብንበደልም ይቅርታ እንጠይቅ ምክንያቱም ይቅርታ ለአዕምሮ ነፃነትን፣ ለልብ እርካታን፣ ለመላው ሰውነታችን ደግሞ ደስታን ይሰጣል።
ታዲያ ነፃነት፣ እርካታንና ደስታን ማይፈልግ አለን⁉
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
⭕️ በመጨረሻም የምላችሁ ነገር ቢኖር፦
❝ጊዜ የሳለ ጎራዴ ነው❞ ይላሉ አረቦች❗️
አዎ! ጊዜ የሳለ ጎራዴ ነው፤ ካልተጠቀምንበት ይቆርጠናል!!
እናም በዚህ ጎራዴ በሆነው ጊዜያችን ከመባላትና ከመጠላላት ይልቅ አብረን ተዋደን፣ ተከባብረን፣ ተደጋግፈን፣ አንዳችን አንዳችንን መክረን ወይም ገስፀን በሰላምና በፍቅር እንኑር። ካልሆነ ግን በጥላቻና በተንኮል ያሳለፍነው ጊዜ እራሳችንን ቆርጦ ይጥለናል።
✍️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
ለአስታያየት: t.me/ReshadMuzemil
ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇
Telegram: t.me/SharpSwords1
Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1
YouTube: youtube.com/@SharpSwords1
Instagram: Instagram.com/sharp_swords1
Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil