Amuti amu Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.
عيد مبارك
🌜كل عام وانتم بخير
تقبل الله منا ومنكم صالح الاعمال 😊
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
ነገ ሐሙስ
✨ዙልሒጃ 9ኛው ቀን (ዐረፋ )
✨የዓረፋን_ቀን_መፆም
የዐረፋ ቀን | ዱዓእ ተቀባይነት ሊያገኝበት ከሚችልባቸው ቀናት መካከል አንዱ እና ልዩ ቀን ነው:: መልእክተኛው ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ በማለት የዓረፋ ቀን ዱዓእ ገልፀዋል:-
“ከዱዓኦች ሁሉ በላጩ የዓረፋ ቀን የሚደረግ ዱዓእ ነው::”
ስለሆነም በዚህ ቀን ለራሳችን ፣ ለወላጆቻችን ፣ ለልጆቻችን ፣ ለባለቤቶቻችን ፣ ለቅርብ ዘመዶቻችን ፣ በኛ ላይ ሀቅ ላላቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ሁሉ በርትተን ዱዓእ ልናደርግ ይገባል።
አቡ–ቀታዳ (ረዲየላሁ ዓንሁ) እንዳስተላለፉት:‐
«የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ስለ እለተ #ዓረፋ_ጾም ተጠየቁ ፤ እሳቸውም "ያለፈውን እና የመጪውን አመት ሀጢአት ያስምራል ብዬ በአላህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ" አሉ።»
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
  አላሁ አክበር…… አላሁ አክበር…… አላሁ አክበር
    የረሳ የተዘናጋ ሁሉ አስታውሱ!!
ከዚህ ሰዓት ጀምሮ………
   ከምድር እስከ ሰማይ ያለው እስኪናወጥ ድረስ
ድምፅ ከፍፍፍፍ አድርጎ ተክቢራ ማድረግ እጅግ በጣም እጅግ በጣም የተወደደ፤
      ግን ደግሞ  የተረሳ  ሱና ነው!!
  ተክቢራችሁ የሰማይ ከፍታ እስከ ሚደርስ ድረስ ተክቢራ አድርጉ።
🔊አላሁ አክበር…… አላሁ አክበር…… አላሁ አክበር
ላ ኢላሃ ኢለሏህ
አላሁ አክበር…… አላሁ አክበር
ወሊላሂል ሀምድ!!
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
"ስለ ዙል ሒጃ አስር ቀናቶች ጥቆማ‼️"
____
✍️በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ዛሬ ዕለተ ቅዳሜ ግንቦት 16 2017 ዓ.ል ነው።
በሒጅሪያህ አቆጣጠር ደግሞ ዙል ቂዕዳ 26, 1446 ነው።
የዙል ሒጃ ወር ሊገባ ሶስት ወይም አራት ቀናቶች ብቻ ይቀራሉ።
ስለዚህ ስለነዚህ ቀናቶች አንዳንድ ጥቆማዎችን እንቃኝ።
👉1✔️የዙል ሒጃ የመጀመሪያ አስር ቀናቶች ታላቅነት✔️
_____
እነዚህ አስርት ቀናቶች አላህ በቁርኣን ላይ የማለባቸው ቀናቶች ናቸው።
አላህ እንዲህ ይላል፦
"{وَالْفَجْرِ. وَلَيَالٍ عَشْرٍ} [الفجر:1-2]"
"በጎህ እምላለሁ።
በዐሥር ሌሊቶችም።"
[አል፡ፈጅር: 1-2]
|
ታላቁ የቁርኣን ሙፈሲር ኢማም ኢብኑ ከሢር
<<በዐሥር ሌሊቶችም>> በሚለው የተፈለገው
የዙል ሒጃን የመጀመሪያ አስርት ቀናቶች ነው በማለት
ኢብኑ ዓባስ፣ ኢብኑ ዙበይር፣ ሙጃሂድና ሌሎችም መናገራቸውን
ጠቅሰዋል።
{{(ተፍሲር ኢብኑ ከሢር ፥ 4/539-540).}}
ከነብዩ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ከተዘገቡ የሐዲሥ መዛግብቶች ውስጥም የሚከተሉት ይገኙበታል።
( ما من أيام العمل الصالح فيهن أحب إلى الله منه في هذه الأيام العشر . قالوا ولا الجهاد في سبيل الله !! قال : ولا الجهاد في سبيل الله ، إلا رجل خرج بنفسه وماله ولم يرجع من ذلك بشيء )
[ ከዙልሒጃህ 10 ቀናት የበለጠ አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆኑባቸው ምንም አይነት ቀናቶች የሉም።] በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን! ተብለው ሲጠየቁ ፦ [ አዎ. በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን , ነገር ግን ንብረቱንና ነፍሱን ይዞ ወጥቶ ከዛ በምንም ነገር ያልተመለሰ ሰው ሲቀር ብለዋል። ]
(ቡኻሪ: 2/457)
|
በተመሳሳይ ገለፃም
ከኢብኑ ዓባስ በተወራ ሐዲሥ ስለ ቀናቶቹ ትሩፋትና ታላቅነት
ኢማሙ ዳሪሚይ 1/357 በኢስናዳቸው ዘግበዋል።
ለተጨማሪ ማብራሪያም ተፍሲር ኢብኑ ከሢር 5/412 ላይ ይመልከቱ።
2✔️"በነዚህ ቀናቶች ውስጥ የሚወደዱ ተግባራቶች"
_____
✔️ሐጅና ዑምራ
✔️ፆም
✔️ ተክቢር፣ ተህሊልና ሌሎች ዚክሮችም ጭምር
✔️ተውበት፣ ከወንጀል መራቅ
✔️መልካም ስራንና ዒባዳን ማብዛት፡ ሶላት ሶደቃ፣ ጅሃድ
✔️የማረጃው ቀንም ኡዱሕያን መተግበርና ሌሎችም
👉كان النبي صلى الله عليه وسلم يصوم تسع #ذي_الحجة ويوم عاشوراء وثلاثة أيام من كل شهر . أول اثنين من الشهر وخميسين "
"ነብዩ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም
#የዙል_ሒጃን ዘጠነኛው ቀን፣
የዓሹራን ቀን፣
ከየወሩ ሶስት ቀናት፣
እንዲሁም በወሩ ውስጥ ሰኞንና ሐሙስን ይፆሙ ነበር።"
{{
"ነሳኢይ: 4/205"
"ኢማም አልባኒም በሶሒሕ አቡ ዳውድ 2/462 ላይ ዘግበውታል።
|
👉( ليشهدوا منافع لهم ويذكروا اسم الله في #أيام_معلومات على ما رزقهم من بهيمة الأنعام ) الحج/28
"ለነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ፣ #በታወቁ_ቀኖችም ውስጥ ከማለዳ እንሰሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ፣ (ይመጡሃል)፤ ከርሷም ብሉ፤ ችግረኛ ድኻንም አብሉ። "
[አል-ሐጅ: 22:28]
"أيام_معلومات" <<በታወቁ_ቀኖች>>
የሚለውን አገላለፅ ከኢብኑ ዓባስና ኢብኑ ከሢር በተገኘ ዘገባ የዙል ሒጃን አስርት ቀናቶች ለመጠቆም መሆኑ ተዘግቧል።
[( الأيام المعلومات : أيام العشر ) ]
👉( ما من أيام أعظم عند الله ولا أحب إليه العمل فيهن من هذه الأيام العشر فأكثروا فيهن من التهليل والتكبير والتحميد )
" ከዙልሒጃህ 10 ቀናት የበለጠ ታላቅና አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆኑባቸው ምንም አይነት ቀናቶች የሉም።
በነርሱም ውስጥ
ተክቢር (አላሁ አክበር ማለት)፣ ተህሊልና (ላ ኢላሀ ኢለሏህ ማለት) ተሕሚድን (አልሐምዱ ሊላህ ማለትን) አብዙ።]"
[አሕመድ: 7/224]
ኢማሙ ጦበራኒይም አል ሙዕጀሙል ከቢር ላይ ዘግበውታል።
አላህ ከመልካም ሰሪዎች ያድርገን።
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.
ተጠቀሙባት‼
===========
✍ በዕለተ ጁሙዓህ ከዐስር በኋላ እስከ መጝሪብ ድረስ ዱዓእ ተቀባይ የሚሆንባት አንድት ልዩ ወቅት አለች። አንድ ባሪያ አላህን ከልቡ ከጠየቀው፤ ያቺኑ የሰጠው ቢሆን እንጂ ዱዓእ የማይመለስባት ወቅት።
ውዱ ነቢይ እንዲህ ብለዋል፦
(يَوْمُ الجُمُعة ثِنْتَا عَشْرَةَ سَاعَةً ، لاَ يُوجَد فِيهَا عَبْدٌ مُسْلِمٌ يَسْأَلُ الله شَيْئاً إِلاَّ آتَاهُ إِيَّاهُ ، فَالْتَمِسُوهَا آخِرَ سَاعَةٍ بَعْدَ العَصْر)
رواه أبو داود (1048) والنسائي (1389) ، وصححه الألباني في " صحيح أبي داود " ، والنووي في "المجموع" (4 / 471) .
በአካል ተገኝተን ማገዝ ለኛ ከባድ ቢሆንም የማይስት በሆነው መሳሪያ "በዱዐ" የጋዛ ወንድሞቻችንን እናስታውስ,ከወንጀል በመራቅ ዱዐ ላይ እንበርታ,ለመልሱም አንቻኮል....አላህ ነስሩን ያቅርብልን
Send as a message
Share on my page
Share in the group