💬 ተማሪዎች የተላለፈ መልዕክት🗨️
══════════════
በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝና ሩኅሩህ በሆነው።
ውድ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች!
📚 ሰኔ ወር ከ3 እስከ 11/2017 ዓ.ል የሚሰጠው ወሳኝ ፈተና ከፊታችሁ ይጠብቃል። ይህ ፈተና የትምህርት ጉዟችሁ ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን፣ ያላችሁን እውቀትና ክህሎት የምትፈትኑበት ትልቅ አጋጣሚ ነው።
✅ በተለይም የ6ኛ ክፍል ከተማቀፍ ፈተና ወደ ላቀ የትምህርት ደረጃ ለመሸጋገር የመጀመሪያው እርምጃ ሲሆን፣ የ8ኛ ክፍል አሀረቀፍ ፈተና ደግሞ የወደፊት የትምህርት አቅጣጫችሁን የሚወስን ወሳኝ ምዕራፍ ነው።
በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ የምሰጣችሁ ምክሮችና ለአላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ መልካም ፈቃድ በመታዘዝ የምታደርጉት ጥረት በእርግጠኝነት መልካም ውጤት እንደሚያስገኝላችሁ እምነቴ ነው።
ውድ ተማሪዎች!
➊ በአላህ ላይ ሙሉ በሙሉ ተመኩ: ማንኛውም ስኬት የሚገኘው በአላህ ፈቃድ ነው። ስለዚህ በምታደርጉት ጥረት ሁሉ አላህን አስቀድሙ። በዱዓ ወደ አላህ ተቃረቡ። አላህ ጥረታችሁን እንዲባርክላችሁና እንዲያግዛችሁ በልባችሁ ሙሉ እምነትን አሳድሩ።
"وَعَلَى ٱللَّهِ فَتَوَكَّلُوٓا۟ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ"
(አል-ማኢዳህ 5:23) - "ምእምናን ከሆናችሁ በአላህ ላይ ብቻ ተመኩቱ።"
❷ ጠንክራችሁ ተዘጋጁ: ፈተናው ከፊታችሁ ሁለት ወራት ብቻ ቀርተውታል። ይህ ጊዜ ለትጋትና ለጠንካራ ዝግጅት ወሳኝ ነው። ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት። ለእያንዳንዱ ትምህርት በቂ ጊዜ መድቡ። የ5ኛ እና 6ኛ ክፍል እንዲሁም የ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ትምህርቶችን በደንብ በመከለስና በመድገም እውቀታችሁን አጠናክሩ።
➌ እቅድ አውጡ: በየቀኑ ምን እንደምታጠኑ በግልፅ ያስቀምጡ። ሳምንታዊ እና ዕለታዊ የጥናት እቅድ በማውጣት ጊዜያችሁን በአግባቡ ተጠቀሙበት። ለእያንዳንዱ ትምህርት የተለየ ጊዜ መድቡ እንዲሁም የእረፍት ጊዜያችሁን አትርሱ።
❹ በትኩረት አንብቡ: በምታጠኑበት ጊዜ ሁሉ አእምሮአችሁን ሙሉ በሙሉ በንባቡ ላይ አድርጉ። ትኩረታችሁን የሚረብሹ ነገሮችን ከዙሪያችሁ አስወግዱ። ያልገባችሁን ነጥቦች ለመምህሮቻችሁ ወይም ለሚያውቋችሁ ሰዎች ለመጠየቅ አትፍሩ።
❺ የቀደምት ፈተናዎችን ተመልከቱ: በተቻለ መጠን የቀደምት ዓመታት የፈተና ጥያቄዎችን በመመልከት የፈተናውን ቅርፅና የጥያቄዎቹን አቀራረብ ለመረዳት ሞክሩ። ይህ ለፈተናው የተሻለ ዝግጅት እንድታደርጉ ይረዳችኋል።
❻ ቡድን በመሆን ተማሩ: ከአስተዋይ ጓደኞቻችሁ ጋር በመሆን በቡድን መወያየትና መማር ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ያልገባችሁን ነገር በመጠያየቅና በመወያየት የተሻለ ግንዛቤ ማግኘት ትችላላችሁ። ነገር ግን የቡድን ጥናታችሁ ከመወያየትና ከመማር የዘለለ እንዳይሆን ተጠንቀቁ።
❼ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ተከተሉ: ሰውነታችሁ ጤናማ ካልሆነ በአግባቡ ማጥናት አትችሉም። ስለዚህ በቂ እንቅልፍ ተኙ፣ የተመጣጠነ ምግብ ተመገቡ እንዲሁም የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አድርጉ። በተለይም በፈተናው ወቅት ጭንቀትን ለማስወገድ ዘና የሚያደርጉ ነገሮችን አድርጉ።
❽ ዱዓ አድርጉ: ከምንም በላይ አላህን በዱዓችሁ አደራ በሉ። አላህ ጥረታችሁን እንዲቀበልላችሁና መልካም ውጤት እንዲሰጣችሁ ሁል ጊዜ ተማጸኑት።
✅ በተለይም በሰላት ውስጥና ከሰላት በኋላ ዱዓ ማድረግን አትርሱ።
"وَقَالَ رَبُّكُمُ ٱدْعُونِىٓ أَسْتَجِبْ لَكُمْ"
(ጋፊር 40:60)
"ጌታችሁም አለ፡- «ለምኑኝ እኔም እቀበላችኋለሁ።»"
ውድ ተማሪዎች!
● እምነታችሁ ለስኬታችሁ ትልቅ መሠረት ነው። ሶላታችሁን በጊዜያችሁ ጠብቃችሁ ስገዱ። ቁርኣንን ቅሩ እንዲሁም መልካም ስነ ምግባርን ያዙ።
● ወላጆቻችሁን አክብሩና ምክራቸውን ስሙ። የአላህን ትዕዛዛት በመጠበቅና እርሱን በመፍራት ለዚህ ፈተና ብቻ ሳይሆን ለወደፊት ህይወታችሁም ስኬትን ታገኛላችሁ።
● ከፊታችሁ ያለው ጊዜ ፈታኝ ሊሆን ቢችልም በአላህ ላይ ሙሉ እምነት የሚኖራችሁ ከሆነ ይህንንም ጊዜ በተሳካ ሁኔታ ማለፍ ትችላላችሁ።
አላህ ከእናንተ ጋር ይሁን! መልካም የፈተና ጊዜ እመኝላችኋለሁ!
✅ በአላህ ፈቃድ ሁላችሁም ከተመኘችሁት ውጤት በላይ እንድታገኙ እመኛለሁ። ውጤቱንም አላህ ለማህበረሰቡ ግርማ-ሞገስ፣ ተድላና ስኬት ሰበብ እንዲሆን ያድርግላችሁ!!
አላህ ያግዛችሁ! 🤲 🤲 🤲
✍️ በወንድማችሁ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል