1 уйӑх Куҫарас
Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

ከቁርኣን ልዩ ባህሪያት

ጥንቅር ኢብን አሚን

ለተከበረው ቁርአን ቀድመውት ከወረዱት ሰማያዊ መጻሕፍት የሚለይበት ልዩ ባህሪያት አሉት፡-

1. ከዚህ በፊት የወረዱት መጻሕፍት ይዘውት የነበረውን መለኮታዊ የመልእክት ጭብጥ አጠቃሎ ያካተተ መሆኑ፣ በእነዚህ የተላያዩ መጻሕፍት ተበታትነው የሚገኙ መልካምና የላቁ አስተምህሮቶች ሰብስቦ መያዙ፣ ሁሉንም ያካበበና በነርሱ ላይ ተጠባባቂ መሆኑ፣ በሌሎች መጻሕፍት ውስጥ ያሉ እውነታዎችን የሚያረጋግጥና በነርሱም ውስጥ የተደረጉ ብረዛዎችንና ቅየራዎችን የሚያጋልጥ መሆኑ። አላህ እንዲህ ብሏል፡-

‘’ ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲሆን በውነት አወረድን…’’ አልማዒዳ፡48

2. አላህ (ሱ.ወ.) ለሁሉም የሰው ልጆች፣ ለሁሉም ዘመንና ቦታ እንደሚስማማ አድረጎ ያወረደው መሆኑና ለአንድ ለተለየ ሕዝብ ብቻ ያልወረደ መሆኑ። አላህ አንዲህ ብሏል፡-

‘’ ያ በባሪያው ላይ ፉርቃንን (ቁርአንን) ለዓለማት አስፈራሪ ይኾን ዘንድ ያወረደ(አምላክ) ክብርና ጥራት ተገባው።’’

3. ቁርአን አላህ እንደሚጠብቀው ቃል የገባለት ብቸኛ መለኮታዊ መጽሐፍ መሆኑ። የተናጋሪዎች ሁሉ አሸናፊ (አላህ) እንዲህ ብሏል፡-

‘’ቁርአንን እኛው አወረድነው፣ እኛም ለርሱ ጠባቂዎቹ ነን’’ (አል-ሂጅር 9)

ይህም የሆነበት ምክንያት የሰው ልጆች ይመሩበት ዘንድ የወረደውና የአላህ የመጨረሻ ቃል የሆነው የቁርአን አስተምህሮ ዘመን ሳይሽረው ለሁልጊዜም እንዲቆይ አላህ (ሱ.ወ.) በመፈለጉ ይህንን መልእክት የመበረዝ፣ የመቀየርም ሆነ የመለወጥ አደጋ እንዳይደርስበት አላህ እራሱ ስለጠበቀው ነው።

“እርሱ (ቁርአን) አሸናፊ የሆነ መጽሀፍ ነው፤ ከበስተፊቱም ከበስተኋላውም ስህተት የማይመጣበት ከጥበበኛውና ከምስጉኑ (አላህ) የተወረደ ነው) [ፉሲለት 14፣24]

4. አላህ (ሱ.ወ.) ንግግሩ ወደ ሰው ልጅ አእምሮና ጆሮ ውስጥ እንዲሰርፅና መልእክቱ እንዲደርስ ከዚያም ወደ ተጨባጭ ተግባር እንዲቀየር ይፈልጋል። ይህ ደግሞ ቁርአን በራሱ ገር ካልሆነ በስተቀር በቀላሉ ለማስታወስና ለመረዳት ስለማይቻል አላህ ገር አድርጎታል፡-

‘’ቁርአንን ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፣ ተገንዛቢም አለን?’’ አልቀመር፡17

#gaza #palestine #freepalestine

image
Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас