UMMA TOKEN INVESTOR

jelalu bedru пайларӗ
Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

2 Пӑхни
Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас
jelalu bedru пайларӗ
Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

"መስጂድ አል-አቅሷ" እና "ቁበቱስ-ሰኽራ"

በርካቶች "መስጂድ አል-አቅሷ" ሲባል በዚህ ፖስት በሁለተኛው ፎቶግራፍ ያለው ውብ ግንባታ ይመስላቸዋል። ይሁን እንጂ "አል-አቅሷ" ማለት በመጀመሪያው ፎቶግራፍ ላይ ያለው መስጂድ ነው። በሁለተኛው ምስል ላይ ያለው ውብ ቤት "ቁበቱ-ሰኽራ" (Dome of the Rock) ነው ይባላል። ሁለቱ ግንባታዎች እነርሱን ለመጠበቅ ተብሎ በተከለለ ቦታ ላይ ነው የሚገኙት። በመካከላቸውም የተወሰነ ርቀት አለ። ሁለቱም የሚገኙበትን ክልል በሶስተኛው ፎቶግራፍ ላይ ማየት ይቻላል።

---

እነዚህ ሁለት እስላማዊ ቅርሶች በሀገረ ፍልስጥኤም፣ በአል-ቁድስ ነው ያሉት። ሁለቱም ግንባታዎች በእስላማዊ ታሪክ ውስጥ በልዩ ሁኔታ ይዘከራሉ። መስጂድ አል-አቅሷ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) አስደናቂውን የሌሊት ጉዞ አድርገው ከእርሳቸው ከሚቀድሙት ነቢያት ጋር የተገናኙበትና ኢማም ሆነው ሰላት ያሰገዱበት የአላህ ቤት ነው። ቁበቱ-ሰኽራ ደግሞ ነቢዩ (ሰዐወ) ሚዕራጅ በሚባለው መሰላል መሰል መወጣጫ አማካኝነት ወደ ሰማይ አርገው የተመለሱበት ስፍራ ነው። በነቢዩ (ሰዐወ) ዘመን በቦታው ላይ ትልቅ ዓለት ነበር። የኡመያድ ኸሊፋ የነበረው ዐብዱልመሊክ ኢብን ሂሻም ዓለቱ ባለበት ስፍራ ላይ አሁን የሚታየውንና ወርቅማ ቀለም ያለውን "ቁባ" (dome) አሰርቷል።

መስጂድ አል-አቅሷን የገነባው ደግሞ ነቢዩ ሱለይማን (ዐሰ) ነበር። በሱለይማን ዘመን የተሰራው መስጂድ እየፈራረሰ በነቢዩ (ሰዐወ) ዘመን አጽሙ ብቻ ቀርቶ ነበር። ቢሆንም ከካዕባ በፊት የመጀመሪያ ቂብላ ሆኖ ያገለገለው ይኸው መስጂድ ነው። አል-አቅሷ በሙሉ ቅርጽና ቁመና እንደገና የተገነባው በኸሊፋ ዑመር ኢብን ኸጣብ ዘመን ነው። ከዑመር በኋላም የኡመያድ እና የአባሲድ ኸሊፋዎች መስጂዱን በማስፋፋት ገንብተውታል።

image
image
image
Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас
jelalu bedru пайларӗ
Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

እሁድን በሚሊኒየም አዳራሽ⁉️

=====================

✍ በረመዿን ዋዜማ የፊታችን እሁድ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ታላቅ ኢስላማዊ ኮንፈረንስ በሚሊኒየም አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል።

በዕለቱ ረመዿን ተኮር ዝግጅቶች፣ በርካታ ተጋባዥ እንግዶችና ጠቃሚ ስንድቶች ይኖራሉ።

እስካሁን የመግቢያ ትኬት ያልወሰዳችሁ ካላችሁ፤ በዚህ ድረ ገፅ ላይ ገብታችሁ በመመዝገብ ስማችሁ ያለበትን የመግቢያ ሰርቲፊኬት ዳውንሎድ በማድረግ በነፃ መውሰድ ትችላላችሁ። በር ላይ ስትገቡ ይህንን የነፃ ትኬት ማሳየት ብቻ በቂ ነው።

https://conference.nesiha.tv

ዝግጁ?

ለፕሮግራሙ ድጎማ በማድረግ የአጅር ተቋዳሽ ለመሆን 444 የንግድ ባንክ አካውንታቸውን ተጠቀሙ።

image
Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас
jelalu bedru пайларӗ
Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

5 Пӑхнисем
Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас
jelalu bedru пайларӗ
3 уйӑх Куҫарас
Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

✍አትታገስም!?

🚢የሰዎቹ መርከብ መገንጠል; ለውለታቸው ክፍያ ከሆነ፣

🔫ህፃኑን መግደል; አዘኔታ ከሆነ፣

💵የየቲሞቹ ብር እንዳይበላሽ ግድግዳው ማቃናት; "አናስተናግድም" ላሉ ህዝቦች ከሳ ከሆነ፣

አንተም; የትኛውም ሚስጥሩን የማታውቀው ጉዳይ ሲገጥምህ ሰብር አድርገህ የጌታህን ፈረጅ ጠብቅ።

📖{ لَا تَدْرِي لَعَلَّ اللَّهَ يُحْدِثُ بَعْدَ ذَلِكَ أَمْرًا }

{ከዚህ በኋላ አላህ (አዲስ) ነገርን ይፈጥር (ያመጣ) እንደሆነ አታውቅም}

https://t.me/hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼ ?????? @hamdquante አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል ?? @hamdquante_bot??
Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас