ዐሽረል አዋኺር (አሥርቱ ቀናት)
****
በተባረከው የረመዷን ወር ዉስጥ የሚገኙት አሥሩ የመጨረሻ ውድ ቀናት መጡ። በነኚህ ቀናት ዉስጥ አምልኮም ሆነ ማንኛዉም መልካም ሥራ የተወደደና ከፍ ያለ ደረጃ ያለው ነው፡፡
ጅማሮ -
አሥርቱ ቀናት የሚጀምሩት በረመዷን 21ኛው ምሽት ላይ ነው፡፡ ወሩ ሙሉ ከሆነ እስከ ረመዷን 30ኛው ቀን ምሽት ይቆያሉ፡፡
ምሽቶቹን ምን ልዩ ያረጋቸዋል?
ለይለቱ ቀድር የምትባል ምሽት ከአሥርቱ ቀናት በአንዱ ዉስጥ አለች፡፡ ይህችን ቀን በነኚህ ቀናቶች ዉስጥ በርትተን እንድንፈልግ ረሱል ሰ.ዐ.ወ. መክረዉናል፡፡
ለይለቱል ቀድር ምንድናት?
ከሺህ ሌሊቶች የምትበልጥ ትልቅ ደረጃ ያላት ምሽት ናት፡፡
ቀኗ በትክክል ይታወቃል?
በትክክል አይታወቅም፤ ነገርግን በተለይም ዋናነት በምሽቶቹ ነጠላ ቀናት ዉስጥ ማለትም በ21፣ በ23፣ በ27፣ በ29 ዉስጥ ፈልጉ ተብሏል፡፡
ለይለቱል ቀድር የሚባል ዱዓ ይኖራል? - እናታችን ዓኢሻ ረ.ዐ አላህ ለይለተል ቀድርን ከወፈቀኝ ምን ልበል? በማለት የአላህን መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ ጠይቃቸው “ አልሏሁም ኢንነከ ዐፉዉን ቱሒቡል ዐፍው ፈዕፉ ዐንኒ” በይ ብለዋታል፡፡ “አላህ ሆይ አንተ ይቅር ባይ ነህ፤ ይቅር ማለትን ትወዳለህ፤ ይቅር በለኝ፡፡” ማለት ነው ትርጉሙ፡፡
ረሱል ሰ.ዐ.ወ በነኚህ ቀናት ዉስጥ ምን ያደርጉ ነበር?
በነኚህ ቀናት ዉስጥ ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ. በአምልኮ ከሌላው ጊዜ በበለጠ በእጅጉ ይበረቱ ነበር፡፡ ቤተሰቦቻቸዉንም ያነቁ ነበር፡፡ ከሌላው ጊዜ በበለጠ ይለግሳሉ፡፡ ሌሊቱን በዚክር እና በዒባዳ ያሳልፋሉ፡፡ ኢዕቲካፍም ይገባሉ፡፡
ኢዕቲካፍ ምንድነው?
ኢዕቲካፍ ማለት አምልኮና ወደ አላህ መቃረብን በማሰብ ራስን ከዓለማዊ ጉዳዮች አርቆ ለተወሰነ ጊዜ፣ ሰዓታት፣ ቀን ወይም ሌሊት መስጂድ ዉስጥ መቆየት ነው፡፡ ኢዕቲካፍ ነቢያዊ መንገድ ነው፡፡ በአሥርቱ ቀናት ዉስጥ እስከሚሞቱ ድረስ ኢዕቲካፍን አልተዉም ነበር ብላለች እናታችን ዓኢሻ፡፡
የኢዕቲካፍ ጥቅሙ ምንድነው?
ኢዕቲካፍ ከዓለማዊ ጉዳዮች ያርቃል፣ ሙሉ በሙሉ ቀልብን ወደ አላህ በመመለስ ከአላህ ጋር መገለልን ያስገኛል፡፡ ነፍስን ያጠራል፣ መንፈስን ያድሳል፣ ቀልብን ያንፃል፡፡ ራሣችን እንድንፈትሽና እንድንገመግም ዕድል ይሠጠናል፡፡
በኢዕቲካፍ ጊዜ ምን ይወደዳል?
በኢዕቲካፍም ሆነ በአሥርቱ ቀናት ዉስጥ ሶላት ማብዛት፣ ኢስቲግፋር (አላህን ምህረትን መለመን) ማብዛት፣ ቁርኣን መቅራት፣ ዚክር ማድረግ፣ ሶደቃ መስጠት፣ ዱዓ ማድረግ፣ መልካም ሥራዎችን ማብዛት ይወደዳል፡፡ በአጠቃላይ ማንኛዉንም መልካም ነገር ሁሉ ሳይሠለቹ አብዝቶ መሥራት ይወደዳል፡፡
አላህ ሆይ ከሚጠቀሙበት አድርገን ለይለተል ቀድርንም ወፍቀን ያ ረብ!!!