Translation is not possible.

"መስጂድ አል-አቅሷ" እና "ቁበቱስ-ሰኽራ"

በርካቶች "መስጂድ አል-አቅሷ" ሲባል በዚህ ፖስት በሁለተኛው ፎቶግራፍ ያለው ውብ ግንባታ ይመስላቸዋል። ይሁን እንጂ "አል-አቅሷ" ማለት በመጀመሪያው ፎቶግራፍ ላይ ያለው መስጂድ ነው። በሁለተኛው ምስል ላይ ያለው ውብ ቤት "ቁበቱ-ሰኽራ" (Dome of the Rock) ነው ይባላል። ሁለቱ ግንባታዎች እነርሱን ለመጠበቅ ተብሎ በተከለለ ቦታ ላይ ነው የሚገኙት። በመካከላቸውም የተወሰነ ርቀት አለ። ሁለቱም የሚገኙበትን ክልል በሶስተኛው ፎቶግራፍ ላይ ማየት ይቻላል።

---

እነዚህ ሁለት እስላማዊ ቅርሶች በሀገረ ፍልስጥኤም፣ በአል-ቁድስ ነው ያሉት። ሁለቱም ግንባታዎች በእስላማዊ ታሪክ ውስጥ በልዩ ሁኔታ ይዘከራሉ። መስጂድ አል-አቅሷ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) አስደናቂውን የሌሊት ጉዞ አድርገው ከእርሳቸው ከሚቀድሙት ነቢያት ጋር የተገናኙበትና ኢማም ሆነው ሰላት ያሰገዱበት የአላህ ቤት ነው። ቁበቱ-ሰኽራ ደግሞ ነቢዩ (ሰዐወ) ሚዕራጅ በሚባለው መሰላል መሰል መወጣጫ አማካኝነት ወደ ሰማይ አርገው የተመለሱበት ስፍራ ነው። በነቢዩ (ሰዐወ) ዘመን በቦታው ላይ ትልቅ ዓለት ነበር። የኡመያድ ኸሊፋ የነበረው ዐብዱልመሊክ ኢብን ሂሻም ዓለቱ ባለበት ስፍራ ላይ አሁን የሚታየውንና ወርቅማ ቀለም ያለውን "ቁባ" (dome) አሰርቷል።

መስጂድ አል-አቅሷን የገነባው ደግሞ ነቢዩ ሱለይማን (ዐሰ) ነበር። በሱለይማን ዘመን የተሰራው መስጂድ እየፈራረሰ በነቢዩ (ሰዐወ) ዘመን አጽሙ ብቻ ቀርቶ ነበር። ቢሆንም ከካዕባ በፊት የመጀመሪያ ቂብላ ሆኖ ያገለገለው ይኸው መስጂድ ነው። አል-አቅሷ በሙሉ ቅርጽና ቁመና እንደገና የተገነባው በኸሊፋ ዑመር ኢብን ኸጣብ ዘመን ነው። ከዑመር በኋላም የኡመያድ እና የአባሲድ ኸሊፋዎች መስጂዱን በማስፋፋት ገንብተውታል።

image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group