UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

🙈

አጂጂጂብ

ልቦና ያለውን ሰው ሁሉ የምታስለቅስ

ቆንጆ ታሪክ

ከረሱል (ሰዐወ) የህይወት ማህደር!

መነበብ እና ለሌሎች መተላለፍ የሚገባው !

ነብዩ (ሰዐወ) ጠዋፍ እያደረጉ ሳለ አንድ

ዓእራብይ /የአረብ ገጠሬ/ …‘ያ ከሪም!’ /ቸሩ

ፈጣሪ ሆይ እንደማለት/… እያለ ሲጣራ

ሰሙት። እርሳቸውም ከኋላው ሆነው …’ያ

ከሪም!’… አሉ። ዓእራብዩም አቅጣጫ

በመቀየር …’ያ ከሪም!’… እያለ መጣራቱን

ቀጠለ ነብዩም (ሰዐወ) ከኋላው ተከትለው

…’ያ ከሪም!’… አሉ።

ዓእራብዩም ፊቱን ወደ እርሳቸው በማዞር:-

“አንተ ባለግርማ እና በሻሻ ፊት ሆይ!…

ዓእራብይ ስለሆንኩ ነው የምታሾፍብኝ?…

በአላህ እምላለሁ! የፊትህ ሞገስ እና በሻሻነት

ባልነበረ ወዳጄ ሙሐመድ (ሰዐወ) ዘንድ

ወስጄ እከስህ ነበር!” አላቸው።

ነብዩም (ሰዐወ) ፈገግ ብለው:- “አንተ አረብ

ወንድሜ ሆይ! ነብይህን አታውቀውም ማለት

ነው?” አሉት

ዓእራብዩም “አዎን!” ሲል መለሰላቸው።

“ለመሆኑ በእርሱ ላይ ያለህ እምነት

ምንድነው?” ሲሉ ጠየቁት

ዓእራብዩም:- “በነብይነቱ አመንኩኝ! አይቼው

ግን አላውቅም፣ ረሱልነቱን ተቀበልኩኝ!

አግኝቼው ግን አላውቅም።” ሲል

መለሰላቸው።

ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ ዓእራብይ ሆይ!

የዱንያው ነብይህ እና የአሄራ አማላጅህ እኔ

መሆኔን እወቅ!” አሉት።

ዓእራብዩም የነብዩን(ሰዐወ) እጅ በፍጥነት

መሳም ያዘ

ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ አረብ ወንድሜ

ሆይ! ሌሎች ህዝቦች ንጉሶቻቸውን

እንደሚያደርጓቸው አታድርገኝ፤ አላህ (ሱወ)

ኩራተኛ እና አጉራዘለል አድርጎ አላከኝም፤

ይልቁንም አብሳሪ እና አስጠንቃቂ አድርጎ

በእውነት ልኮኛል።” አሉት

በዚህን ጊዜ ...

ጅብሪል ወደ ነብዩ መጣና:- “ሙሐመድ

ሆይ አላህ (ሱወ) ሰላምታን ያቀርብልሀል!

በክብር እና ልቅናም ከሌሎች አስበልጦሀል፤

ለዚህ ለዓእራብይ:- የአላህ ቸርነት እና ቻይነት

እንዳያዘናጋው!፣ ነገ በትንሹም ይሁን በትልቁ፣

በልምጩ ይሁን በቅሉ እንደሚተሳሰበው

ንገረው”… አላቸው።

ዓእራብዩም:- “አንቱ የአላህ መልእክተኛ

(ሰዐወ) ሆይ! ጌታዬ ይተሳሰበኛል ማለት

ነው?” ብሎ ጠየቃቸው

“አዎን ከፈለገ ይተሳሰብሀል!” አሉት

“እንግዲያውስ በአሸናፊነቱ እና በልቅናው

ይሁንብኝ! የሚተሳሰበኝ ከሆነ እኔም

እተሳሰበዋለሁ!” አለ።

ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ አረብ ወንድሜ

ሆይ! ጌታህን በምን ትተሳሰበዋለህ?” አሉት።

“ጌታዬ በወንጀሌ ከተሳሰበኝ እኔ በምሕረቱ

እተሳሰበዋለሁ፣ በጥፋቴ ከተሳሰበኝ እኔ በይቅር

ባይነቱ እተሳሰበዋለሁ፣ በስስታምነቴ

ከተሳሰበኝ እኔ በቸርነቱ እተሳሰበዋለሁ!”…

አለ።

~~

ነብዩ (ሰዐወ) ፂማቸው እስኪረጥብ ድረስ

አለቀሱ።

ጅብሪል ወደ ነብዩ ወርዶ:- “ሙሐመድ ሆይ!

አላህ ሰላምታን ያቀርብልሀል። ለቅሶህንም

ቀንስ! የአርሽ ተሸካሚ መላኢካዎችን ተስቢህ

ከማድረግ አዘግይታቸዋለችና ይልሀል።

ለዓእራብዩ ወንድምህ ደግሞ:- እንዳይተሳሰበን

ንገረው! እኛም አንተሳሰበውም! እርሱ የጀነት

ጎረቤትህ ነው!።”… አላቸው።

አላህ በታላቋ ጀነተል ፊርደውስ ውስጥ

የነብዩን (ሰዐወ) ጉርብትና ከሚያገኙት

እንዲያደርገን እንለምነዋለን።

ያ አላህ ይህንን መልእክት አንብበው

ለሚያስተላልፉ ሁሉ ከነቤተሰቦቻቸው

ምሕረትህን ለግስ መመንዳትንም

አትንፈጋቸው …ያ ከሪም!።

ከአላህ ውጭ በእውነት የሚመለክ አምላክ

የለም! ሀይልም ሆነ ብልሀት በርሱ ቢሆን

እንጂ አይገኝም!።

~~

‘አላሁመ ሰሊ አላ ሙሐመድ ወ አላ አሊ

ሙሐመድ’ …ጌታዬ ሆይ ምሕረትህን

እለምንሀለሁ ወዳንተም ንሰሀ እገባለሁ!።

ከመካከላችን ሰደቀተል ጃሪያን የሚፈልግ

ማነው? ከሞትን በኋላ እንኳ በቀብራችን

ውስጥ ሆንነን አጅር የምንቋደስበትን!።

እንግዲያውስ ይህንን መልካም ስራ በነፍሳችን

ላይ አናስመልጥ!

}} በነብዩ (ሰዐወ) ላይ አስር ሶላዋትን

እናውርድ ለአስር ሰዎችም መልእክቱን

እናስተላልፍ የቂያም ለት በሚዛናችን ላይ

ሚሊየን ሰላዋት ሆኖ እናገኘዋለን

Send as a message
Share on my page
Share in the group
neima shemsu shared a
Translation is not possible.

ሠላምታን አብዙ 👋 ሠላምታን አብዙ ! 

አላህ በተከበረዉ ቃሉ እንዲህ ይለናል :-

وَإِذَا حُيِّيتُم بِتَحِيَّةٍۢ فَحَيُّوا۟ بِأَحْسَنَ مِنْهَآ أَوْ رُدُّوهَآ ۗ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ حَسِيبًا

❝ በሰላምታ በተከበራችሁም ጊዜ ከርሷ ይበልጥ ባማረ ሰላምታ አክብሩ ፤ ወይም እርሷኑ መልሷት። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነዉና። ❞

ነብያችንም (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል:-

❝ ነፍሴ በእጁ በሆነችዉ (ጌታ) እምላለሁ። ጀነት አትገቡም አስክታምኑ ድረስ ፤ አመናችሁም አይባልም እስካልተዋደዳችሁ ድረስ። ብትሰሩት የሚያዋድዳችሁን ነገር ላመላክታችሁን አሉ ? ሰላምታን በመካከላችሁ አብዙ። ❞[ ሙስሊም ዘግበዉታል ]

ሰላምታን ማብዛት እና መጨባበጥ ዉዴታን ይጨምራል። ሽኩቻና ምቀኝነትን ያጠፋል። በእስልምና ባእድ ወንዶች እና ሴቶች መጨባበጥ የለባቸዉም። ክልክል ነዉና። ሰላምታን ግን አይከለከሉም።

👉https://ummalife.com/ibnudelil

ibnudelil | UmmaLife

ibnudelil | UmmaLife

ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦ 1) ከቁርኣን፣ 2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ] 3) ከታማኝ ዑለማዎችና 4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል። √ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ። √ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላትነው። ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ። ጀዛኩሙል`ሏህ
Send as a message
Share on my page
Share in the group
neima shemsu shared a
Translation is not possible.

ዑመር ረዐ ድንገት ረሱል ሰዐወ ወደተኙበት ደሳሳ ጎጆ ሲገባ ህመሙን

ሚያብስበት ትዕይንት ተመልከተ።

እዝያች ደሳሳ ጎጆ ውስጥ በተነጠፈች ብጣሽ የግመል ቆዳ ላይ ረሱል ሰዐወ

በሳር የተሰራ ትራስ ተንተርሰው ተኝተዋል።

የተኙባት ቆዳ አርጅታ ጫፍ ጫፏ ተበላልቷል። የቆዳው ድርቀት መላ ሰውነታቸው

ላይ ሰንበር አውጥቶ ገላቸው ተጎድቷል።

ከተኙበት ክፍል ቁና እማትሞላ ገብስ በስልቻ ተደርጎ ጥግ ላይ ተቀምጧል።

የድህነት መገለጫዎችን በሙሉ ዑመር ከረሱል ሰዐወ ቤት ሲመለከት ስሜቱ

አስገድዶት እንባውን ያፈስ ጀመር።

ነቢ እንባውን ተመለከቱት፦‹‹ዑመር ምን ሁነኃል? ለምን ታለቅሳለህ?››

አሉትም።

ዑመር ረዐ ሲቃ ከሚተናነቀው ድምፅ ጋር ግብግብ እየፈጠረ፦‹‹ነቢዋ! ገላዎት

ባለቀ የቆዳ ንጣፍ ሰንበር አውጥቶ እያየሁ እንዴት አላልቅስ?! ከርስዎ ክፍል

ይህችን ምታክል ገብስስ እየተመለከትኩ እንዴት አላልቅስ?!

የሮም እና የፐርሺያ ንጉሳን በወርቅ እና በአልማዝ ባሸበረቁ አልጋዎች ላይ የሀር

ጨርቅ አንጥፈው በፍራፍሬዎች እልፍኝ ተደላድለው ሲኖሩ እርሶ የአላህ ነቢይ

እና ውድ ሁነው እንዴት?! ›› ብሎ የቁጭት ለቅሶውን ቀጠለ።

ነቢ ፈገግታ ከፊታቸው እያስነበቡት እንዲህ አሉት፦‹‹ዑመር! እነሱ እኮ

ድሎታቸው የፈጠነላቸው ሰዎች ሲሆኑ በቅርቡ ከድሎት ይቋረጣሉ።

እኛ ደግሞ ፀጋዎቻችን ወደ ጀነት የተሸጋገረላቸው ህዝቦች ነን፤ ታድያ ዱንያ

ለነሱ ሁና አኪራ ለኛ እንድትሆን አትፈልግም እንዴ? ››

ዑመር ንግግራቸው ቢያሳምነውም ምቾት አልሰጠውም፦‹‹ነቢዋ! ታድያ ሌላው

እንኳ ቢቀር ለምን ከዚህ ለስለስ ባለ ምንጣፍ ላይ አይተኙም? ›› አላቸው

በስስት እየተመለከተ።

ነቢ ጉዳዩን ግልፅ ሊያደርጉለት ፈለጉና ጠንከር አሉ፦‹‹ዱንያ እና እኔን ምን

አገናኘን?! እኔ እና ዱንያ ማለት እኮ ልክ የበረኃ ተጓዥ በአንዲት ጥላ ተጠልሎ

ፀሀይዋ ስትበርድ ጉዞውን እንደሚቀጥለው ነው እኮ (ጥላዋ ስር እድሜ ልኩን

አይኖርም)›› አሉት።

ሰላሏሁ አላ ነቢዪና ሙሐመድ

ከumma media

Send as a message
Share on my page
Share in the group
neima shemsu Changed her profile picture
1 year
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group