Translation is not possible.

🙈

አጂጂጂብ

ልቦና ያለውን ሰው ሁሉ የምታስለቅስ

ቆንጆ ታሪክ

ከረሱል (ሰዐወ) የህይወት ማህደር!

መነበብ እና ለሌሎች መተላለፍ የሚገባው !

ነብዩ (ሰዐወ) ጠዋፍ እያደረጉ ሳለ አንድ

ዓእራብይ /የአረብ ገጠሬ/ …‘ያ ከሪም!’ /ቸሩ

ፈጣሪ ሆይ እንደማለት/… እያለ ሲጣራ

ሰሙት። እርሳቸውም ከኋላው ሆነው …’ያ

ከሪም!’… አሉ። ዓእራብዩም አቅጣጫ

በመቀየር …’ያ ከሪም!’… እያለ መጣራቱን

ቀጠለ ነብዩም (ሰዐወ) ከኋላው ተከትለው

…’ያ ከሪም!’… አሉ።

ዓእራብዩም ፊቱን ወደ እርሳቸው በማዞር:-

“አንተ ባለግርማ እና በሻሻ ፊት ሆይ!…

ዓእራብይ ስለሆንኩ ነው የምታሾፍብኝ?…

በአላህ እምላለሁ! የፊትህ ሞገስ እና በሻሻነት

ባልነበረ ወዳጄ ሙሐመድ (ሰዐወ) ዘንድ

ወስጄ እከስህ ነበር!” አላቸው።

ነብዩም (ሰዐወ) ፈገግ ብለው:- “አንተ አረብ

ወንድሜ ሆይ! ነብይህን አታውቀውም ማለት

ነው?” አሉት

ዓእራብዩም “አዎን!” ሲል መለሰላቸው።

“ለመሆኑ በእርሱ ላይ ያለህ እምነት

ምንድነው?” ሲሉ ጠየቁት

ዓእራብዩም:- “በነብይነቱ አመንኩኝ! አይቼው

ግን አላውቅም፣ ረሱልነቱን ተቀበልኩኝ!

አግኝቼው ግን አላውቅም።” ሲል

መለሰላቸው።

ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ ዓእራብይ ሆይ!

የዱንያው ነብይህ እና የአሄራ አማላጅህ እኔ

መሆኔን እወቅ!” አሉት።

ዓእራብዩም የነብዩን(ሰዐወ) እጅ በፍጥነት

መሳም ያዘ

ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ አረብ ወንድሜ

ሆይ! ሌሎች ህዝቦች ንጉሶቻቸውን

እንደሚያደርጓቸው አታድርገኝ፤ አላህ (ሱወ)

ኩራተኛ እና አጉራዘለል አድርጎ አላከኝም፤

ይልቁንም አብሳሪ እና አስጠንቃቂ አድርጎ

በእውነት ልኮኛል።” አሉት

በዚህን ጊዜ ...

ጅብሪል ወደ ነብዩ መጣና:- “ሙሐመድ

ሆይ አላህ (ሱወ) ሰላምታን ያቀርብልሀል!

በክብር እና ልቅናም ከሌሎች አስበልጦሀል፤

ለዚህ ለዓእራብይ:- የአላህ ቸርነት እና ቻይነት

እንዳያዘናጋው!፣ ነገ በትንሹም ይሁን በትልቁ፣

በልምጩ ይሁን በቅሉ እንደሚተሳሰበው

ንገረው”… አላቸው።

ዓእራብዩም:- “አንቱ የአላህ መልእክተኛ

(ሰዐወ) ሆይ! ጌታዬ ይተሳሰበኛል ማለት

ነው?” ብሎ ጠየቃቸው

“አዎን ከፈለገ ይተሳሰብሀል!” አሉት

“እንግዲያውስ በአሸናፊነቱ እና በልቅናው

ይሁንብኝ! የሚተሳሰበኝ ከሆነ እኔም

እተሳሰበዋለሁ!” አለ።

ነብዩም (ሰዐወ):- “አንተ አረብ ወንድሜ

ሆይ! ጌታህን በምን ትተሳሰበዋለህ?” አሉት።

“ጌታዬ በወንጀሌ ከተሳሰበኝ እኔ በምሕረቱ

እተሳሰበዋለሁ፣ በጥፋቴ ከተሳሰበኝ እኔ በይቅር

ባይነቱ እተሳሰበዋለሁ፣ በስስታምነቴ

ከተሳሰበኝ እኔ በቸርነቱ እተሳሰበዋለሁ!”…

አለ።

~~

ነብዩ (ሰዐወ) ፂማቸው እስኪረጥብ ድረስ

አለቀሱ።

ጅብሪል ወደ ነብዩ ወርዶ:- “ሙሐመድ ሆይ!

አላህ ሰላምታን ያቀርብልሀል። ለቅሶህንም

ቀንስ! የአርሽ ተሸካሚ መላኢካዎችን ተስቢህ

ከማድረግ አዘግይታቸዋለችና ይልሀል።

ለዓእራብዩ ወንድምህ ደግሞ:- እንዳይተሳሰበን

ንገረው! እኛም አንተሳሰበውም! እርሱ የጀነት

ጎረቤትህ ነው!።”… አላቸው።

አላህ በታላቋ ጀነተል ፊርደውስ ውስጥ

የነብዩን (ሰዐወ) ጉርብትና ከሚያገኙት

እንዲያደርገን እንለምነዋለን።

ያ አላህ ይህንን መልእክት አንብበው

ለሚያስተላልፉ ሁሉ ከነቤተሰቦቻቸው

ምሕረትህን ለግስ መመንዳትንም

አትንፈጋቸው …ያ ከሪም!።

ከአላህ ውጭ በእውነት የሚመለክ አምላክ

የለም! ሀይልም ሆነ ብልሀት በርሱ ቢሆን

እንጂ አይገኝም!።

~~

‘አላሁመ ሰሊ አላ ሙሐመድ ወ አላ አሊ

ሙሐመድ’ …ጌታዬ ሆይ ምሕረትህን

እለምንሀለሁ ወዳንተም ንሰሀ እገባለሁ!።

ከመካከላችን ሰደቀተል ጃሪያን የሚፈልግ

ማነው? ከሞትን በኋላ እንኳ በቀብራችን

ውስጥ ሆንነን አጅር የምንቋደስበትን!።

እንግዲያውስ ይህንን መልካም ስራ በነፍሳችን

ላይ አናስመልጥ!

}} በነብዩ (ሰዐወ) ላይ አስር ሶላዋትን

እናውርድ ለአስር ሰዎችም መልእክቱን

እናስተላልፍ የቂያም ለት በሚዛናችን ላይ

ሚሊየን ሰላዋት ሆኖ እናገኘዋለን

Send as a message
Share on my page
Share in the group