UMMA TOKEN INVESTOR

About me

ትናንት ፤ ዛሬ ፤ ነገ t.me/kareem26moh

Followings
0
No followings
Translation is not possible.

የፍልስጤም ታሪክ

ምዕራፍ -2

እስራኤል ክፉ ፅንስ

ክፍል-6

[ተፃፈ-በአብዱልከሪም ሙሐመድ]

የመጀመሪያው ፍልስጤምን ለሁለት የመክፈል እቅድ የተዘጋጀው ብዙ ደም ያፋሰሰውን የ1936ቱን ታላቅ አመፅ ተከትሎ ነበር፡፡ በጁን 7/1937 የአረቦችንና የአይሁዳዊያን ፍላጎት ለማመላከት በሎርድ ቢል በቀረበው ሪፖርት መሠረት ያደረገ ነበር፡፡

እንግሊዝ ለአይሁዳዊያን ቃል የገባችላቸውን በሙሉ የፍልስጤም ምድር (እንደውም አንዳንድ ፅዮናውያን ዮርዳኖስን ጭምር ታሰቦላቸው እንደነበር ይናገራሉ) ሀገር የመመስረት ህልም ከንቱ ምኞት ሆኖባታል፤ አረቦች ሚያልሙትን አረባዊ ህብረት ተመስርቶ ከባድ ተቀናቃኝ ከሚፈጠር ደግሞ እንግሊዝ ሞቷን ትመርጣለች፡፡

በዚህም ደህና ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ እንዲሉ አስታራቂ ሃሳብ የሚመስል ሌላ ህልም በ ‹ግጭት ፈቺ› ኮሚቴው ታቀደ፤ የሁለቱ ጉዳይ ፍልስጤምን በመከፋፈል ካልሆነ በቀር ለመፍታት ማይቻል መሆኑን አመላከተ፡፡

የእቅዱ ዝርዝር ሀተታ እንደሚከተለው ነው ፡

1ኛ አይሁዳዊት ሀገርን በፍልስጤም መመስረት ሲሆን ግዛቷም ከሰሜንና ምዕራብ ክፍል ከሊባኖስ ድንበር እስከ ደቡብ ጃፍፋ (እነ ኤከር፣ሀያፋ፣ሳፋድ፣ጠበርሪያህ፣ናዛሬትና ቴል-አቪቭን) ያጠቃልላል፡፡

2ኛ ቅዱስ ስፍራዎችን (ቤተልሔም እና አል-ቁድስ (እየሩሳሌም)) በሞግዚቷ አንግሊዝ ቁጥጥር ስር እንዲሆኑና ከ ጃፍፋ፣አሉድ፣አል-ራምላ፣ናዝሬት የመሳሰሉ ከተሞች ጋር የሚያገናኝ መንገድ መስራት፡፡

3ኛ አረባዊት ሀገርን ደግሞ በደቡብና ምስራቅ ቦታዎች ላይ (ጃፍፋ ከተማን ጨምሮ እስከ ምስራቅ ዮርዳኖስ ድረስ) መመስረት፡፡

4ኛ አይሁዳዊቷ ሀገር ለአረባዊቷ የገንዘብ ድጋፍ እንድታደርግ እንዲሁም እንግሊዝ አንድ ሚሊዮን ስተርሊንግ ለዚች መሬት ለተወሰደባት መስጠት፡፡

5ኛ የሰዎች ልውውጥ ማለትም በአዲሲቷ ሀገር የሚገኙትን ወደ 325 ሺህ የሚሆኑ አረቦችን ወደ አረባዊቷ ሀገር ማዘዋወር እና እዛም ቦታዎችን ለነሱ ማመቻቸት፡፡

6ኛ ወደ ሁለቱ ሀገራት በሚገቡ እቃዎች ላይ ቀረጥን በጋራ ለመሰብሰብ ስምምነት ላይ እንዲደረሱ ማድረግ የሚሉት ናቸው፡፡

ሆኖም ይህ በፍልስጤዊያን ዘንድ ሌላ ቀልድ እየተቀለደባቸው እንደሆነ በማወቃቸው ሊስማሙ አልቻሉም፡፡ መቼም አንድ የሰፈር ጉልቤ አንድን ሰው በቤቱ መጥቶ የሚጋፋው ባዳ (ለዛውም በሀይማኖትም ይሁን በምንም የማይገናኝ) ጋር ውርስ ተካፈል ቢለው እምቢታው የሚያስገርም አይደለም፡፡ ይህ አለመስማማት ምክንያት ሀሳቡን እንዳይተገበር እንቅፋት ሆኖ ቆየ፡፡

በኖቬምበር 23 1938 የእንግሊዝ ቀኝ-ግዛቶች ሚኒስትር በዚህ ጉዳይ ላይ ወሳኝ የሆነን ንግግር ሲያስቀምጥ ማኅበረሰቡ ከአረቦች እይታ አንፃርም ሆኖ ነገሮችንም እንዲያይ አድርጎት ነበር፡፡

በመካከለኛው ዘመን አይሁዳዊያን በአውሮፓ ውስጥ ይደርስባቸው የነበረውን ግፍና ጭቆና እንዲሁም ጥገኝነትን የፍልስጤምን ዋጋ በመክፈል ማካካስ ትክክል እንዳልሆነ እና ከብዙ ዘመናት በፊት የሰፈሩት አረቦች አስተያየት ሳይጠየቅ የባልፎር ቃልኪዳን መግባት ትልቁ ስህተት እንደሆነ በግልፅ አስቀምጧል፡፡

በተጨማሪም የ20 ዓመት የጦርነት ገፈት ቀማሽ የሆነው፣ የመሬት ወረራን በባዕድ ህዝቦች የሚካሄድበት አረብ ተቃውሞውን በደማቅ እሳት ማሳየቱ እጣውም በራሳቸው መሬት ላይ ለሌላ አዲስ ማህበረሰብ ተገዢ ሆኖ እንዳይኖሩ መስጋታቸው ጥፋት አለመሆኑን አፅንኦት ሰጥቷል፡፡

ከዚህ ንግግሩ በኋላ ለንደን ኮንፈረንስ ላይ ላይ የግብፅ፣ ኢራቅ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ የመን፣ ምስራቅ ዮርዳኖስ ሰዎች ከፍልስጤማዊያንና አይሁዳዊያን በተጨማሪ ተገኝተው ነበር፡፡

ሆኖም በፌብሯሪ 7 1939 የክቡ ጠረጴዛ ኮንፈረንስ በጭቅጭቅ ያለ ስምምነት አለፈ፡፡ ከጊዜያት በኋላ የእንግሊዝ መንግስት ‹ነጩ መፅሀፍ› በሚል የሰየመውን ረቂቅ ሀሳብ ለተሳታፊዎቹ አስተዋወቀ፡፡ በዚህ ሀሳብ ላይ ለመወያየትና ተግባራዊ ለማድረግ እየታቀደ እያለ ነበር ሁለተኛው የአለም ጦርነት የተቀሰቀሰው፡፡

ምዕራፍ 2 በዚሁ ተጠናቀቀ፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የፍልስጤም ታሪክ

ምዕራፍ -2

እስራኤል ክፉ ፅንስ

ክፍል-5

[ተፃፈ-በአብዱልከሪም ሙሐመድ]

ፍልስጤም በእንግሊዝ ስር መዋል ከጀመረች በኋላ ውጥረት ነግሷል፤የሁለቱም ወገን እዚም እዚያም ሲጎሻሸም ቂም እንዳዘለ ቆይቷል፡፡ የሰላም አየር ተናፍቋል ይባስ ብሎ የዳኛውን ፊሽካ እንደሚጠብቁ የቦክስ ተጋጣሚዎች ፍጥጫው አይሏል፡፡

ለዚህም በፌብሯሪ 1936 የተከሰተው አጋጣሚ ማሳያ ሊሆነን ይችላል፡፡ ያፋህ ውስጥ በመንግስት ወጪ በሚሰሩ 3 ትምህርት ቤቶች ኮንትራክተር የነበረው አይሁዳዊ አንድም አረብ ሰራተኛ ለመቅጠር ፍቃደኛ አልነበረም፡፡ ፊት የተነፈጉት ሰራተኞች እሳት ለባሰው እሳት ጎርሰው በስራ ቦታው በመሰባሰብ አንድም አይሁዳዊ ወደዚያ ዝር እንዳይል አደረጉ፡፡

ከጥቂት ግዜያት በኋላ በኤፕሪል 15 አንድ አይሁድ ሲገደል ሌላኛው ክፉኛ ቆሰለ፡፡ አይሁዶች በአፀፋው አረብ ገበሬዎችን በቤታቸው ጨፈጨፏቸው፡፡ ይህ ክስተት ነው እንግዲህ የተርከፈከፈው ነዳጅ ላይ ክብሪት የለኮሰው፡፡ እዚም አዛም ፀብ እየተነሳ በሁለቱም ወገን ብዙ ሰው አለቀ፤ የእንግሊዝ ወታደሮች የሚወሰድ እርምጃ የሞት መጠን ሚዛኑ ወደ ፍልስጤማዊያን እንዲያጋድል አደረገው፡፡

ነገሮች ከድጡ ወደማጡ ሲሄዱ ምድሪቷ በደም ጨቀየች፡፡ የሀገሪቷ ዜጎች አድማና አመፅን በማወጅ ብሔራዊ ተቃውሞን አጠናክረው ቀጠሉ፡፡በቡድን አየተደራጁ ሲንቀሳቀሱ ሌሎች ፍቃደኛ አረቦች ከምስራቅ ዮርዳኖስ፣ ሶሪያ፣ ሊባኖስ እና ኢራቅ ተቀላቀሏቸው፡፡

ይህ መሆኑ አመፁን ወደ ጦረኛ አብዮት አሳደገው፡፡ ድልድይ በማፈራረስ፣ የባቡር ሀዲዶችንና የነዳጅ ማስተላለፊያዎችን በማፈንዳት እንዲሁም ወሳኝ ቦታዎች ላይ ቦምብ በመጣል ቀውጢ አደረጉት፡፡

የፈረጠመ ክንድ ያላት እንግሊዝ የአየር ሀይሏንና ከባባድ የጦር መሳሪያዎችን (መድፍ እና ሌሎችን) በመጠቀም አመፁን ለማዳፈን ብትሞክርም አልተሳካላትም፡፡ በዚህ ግዜ ብቸኛ አማራጭ ወደ ሆኑት ወደ ቀድሞ ወዳጆቿ ሮጠች፡፡

እነ ንጉስ ቢን ሳዑድ (አብዱልአዚዝ)፣ ንጉስ ጋዚ እና ልዑል አብዱሏህ ጥሪዋን በመቀበል በኦክቶበር 10 መከሩ፡፡ በዚህም ለፍልስጤማዊያን የሚከተለውን መልዕክት አስተላለፉ፡፡

‹‹በዚህ የፍልስጤም ሁኔታ እጅጉኑ አዝነናል፣ እናም እኛ የአረብ ንጉሶችና ልዑል አብዱሏህ ሰላማዊነት እንዲመለስ እና ደም መቃባት እንዲያበቃ ተስማምተናል፡፡ በአጋራችን በእንግሊዝ መንግስት በጥሩ ተነሳሽነት የታቀደውን ፍትህ ለማስፈፀም እኛም እናንተን ለመርዳት ጥረት እንደምናደርግ በመተማመን ነው፡፡››

የተደገሰላቸውን ያላወቁ የዋሆች ይህንን ጥሪ በመቀበል አመፁ እንዲቆም በማድረግና 2ሺህ የሚደርሱ ሰማዕታት ላይ ሰላት በመስገድ አብዮቱ ተጠናቀቀ፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የፍልስጤም ታሪክ

ምዕራፍ -2

እስራኤል ክፉ ፅንስ

ክፍል-4

[ተፃፈ-በአብዱልከሪም ሙሐመድ]

እስራኤል የሚባል ሀገር በፍልስጤም ምድር ላይ ከመወለዱ በፊት ሂደቱን ለማስቆም የተካሄዱ እርምጃዎች ነበሩ፡፡ ከነዚህም ውስጥ በ ዲሴምበር 1931 ከኢስራዕ-ወል-ሚዕራጅ ቀን ቀደም ብሎ የ22 ሙስሊም ሀገራት ተወካዮችና ታላላቅ ሰዎች በተገኙበት የተካሄደው ኢስላማዊ ኮንፈረንስ ይጠቀሳል፡፡

በዚህ ፕሮግራም ላይ ሙፍቲ ሙሀመድ አሚን አል-ሁሴይኒ ፍልስጤም እና አል-አቅሷን በኢስላማዊው አለም ውስጥ ያላቸውን ጠቀሜታ አበክረው አስምረውበታል፡፡ በተጨማሪም ኮንፈረንሱ በዚች አገር ውስጥ የፅዮናውያንና የእንግሊዝን እንቅስቃሴ እንዲሁም የአይሁዳዊያንን ፍልሰት እንዴት መግታት ይቻላል በሚለው ጉዳይ ላይ መክሯል፡፡

በመጨረሻም የደረሱበት ውሳኔም ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ በእየሩሳሌም (ቁዱስ) ለመስራት፣ ሁሉንም የአይሁዳዊያን ምርት ላይ አገዳ መጣል እና የእርሻ መሬት ወረራውን ለመከላከል ተቋም መመስረት የሚሉት ይገኙበታል፡፡ ከዚህ ቀደም ብሎ በጁላይ የጀነራል አርተር ግሬንፍል ዋቾፕ በፍልስጤም ከፍተኛ ኮሚሽነር ሆኖ ተሾመ፤ እሱም ወደ ፍልስጤም ሲገባ የአይሁዳዊያን መኖሪያ ቤት እውን የመሆን ዋነኛ ራዕይ አንግቦ ነበር፡፡

ለአረቦች የውሸት እቅዶችን በመቅረፅ ለማዘናጋት እና ፍላጎታቸውን ቸል በማለትና የአይሁዳዊያንን ብዛት በቻለው ሁሉ ከፍ ለማድረግ ሲሰራ ቆይቷል፡፡በዚህም እሱ ከመጣ በኋላ በ1932 ወደ 9553 የሚሆኑ ከዛም በ1933 ከ3 እጥፍ በላይ አድጎ 30327 እንዲሁም በ1934 መጨረሻ 42359 አይሁዳዊያን ስደተኞች ወደ ፍልስጤም እንደገቡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በኦገስት 1932 ቀኝ ግዛትንና የአይሁዳዊያንን ፍልሰት ለመዋጋት እንዲሁም አረባዊ አንድነትን ለማምጣት ያለመ ‹የነፃነት ፓርቲ› ተፈጠረ፡፡

ደጋፊና አባላቶቹም የሀገሪቱ በጀት ሲሶው ለመከላከያ ሃይል መዋሉ ለወደፊት ባዕድ ሀገር ያለፍላጎታቸው ለመመስረት እንደሆነ ተገንዝበዋል፤ በዚህም የባልፎር አዋጅን እና የእንግሊዝን ሞግዚትነት እንደሚቃወሙ ገለፁ፡፡

በዚሁ አመት በ1932 የፍልስጤም ወጣቶች እንዴት ለብሔራዊ ንቅናቄ መዘጋጀት እንዳለባቸው የሚያወያይ ኮንፈረንስ በያፋህ ተካሄደ፡፡

በፍልስጤማዊያን ከተወሰዱ እርምጃዎች ውስጥ በ1935 የተካሄደው የሼህ ዒዘዲን አል-ቃሲም አብዮት ተጠቃሽ ነው፡፡ ይህ እንቅስቃሴ ለገዢዋ እንግሊዝ የሁኔታው አደገኛነት የሚያሳይ ማንቂያ ደውል ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ሼህ ዒዘዲን አል-ቃሲም ከሌሎች ሙጃሂዶች ጋር በመሆን የፍልስጤምን መሬት ከጠላት ለመከላከል ጂሀድ አወጁ፡፡ በዚህም ጀኒን ላይ ከእንግሊዛ ጦር ጋር በመፋለም ምንኛ ያማረ ሰምዓትነትን ተቀዳጁ፡፡

ከአል-ቃሲም ሰምዓትነት 1 ወር በኋላ ከፍተኛ ኮሚሽነር ዋቾፕ በህግ አውጪ ምክር ቤት የተዘጋጀውን እቅድ በፍልስጤም የፖለቲካ ፓርቲዎች ቦርድ ለቀረበው ጥያቄ እንደምላሽ አቀረበ፡፡

አዲስ ህገ-መንግስት መቅረፅ፣ ዲሞክራሲያዊ አመራርን መተግበር፣ የመሬት ሽያጭ ሁኔታዎችን፣ የስደተኞች ብዛትን ከሀገሪቱ የመቀበል አቅም ጋር የሚያሰላ ስታቲስቲካል ቢሮን መመስረትንና የመሳሰሉትን እቅዱ ቢያካትትም ብዙ ለውጥ ለመፍጠር አልቻለም፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የፍልስጤም ታሪክ

ምዕራፍ -2

እስራኤል ክፉ ፅንስ

ክፍል-3

[ተፃፈ-በአብዱልከሪም ሙሐመድ ]

በ1925 ያ ወሮ-በላ ባልፎር የአል-ቁድስን (እየሩሳሌም) ምድር በድጋሚ ረገጠ፡፡ የመጣበትም አላማ አዲሱን የሂብሩ ዩኒቨርሲቲ ምርቃት ፕሮግራም ላይ ለመገኘት ነበር፡፡ የሚገርመው ደግሞ የተገነባው አል-ዛይቱውን ተራራ ላይ ሲሆን በ1918 ከባለቤቶቹ (ፍልስጤማዊያን) የእንግሊዝ ወታደሮች ቀምተው ለፅዮናዊያን የሰጡት መሬት ነበር፡፡

ይህ ጉብኝት ታላቅ ተቃውሞን (አመፅ) አስከተለ ፤ ታላቅ አድማን ፍልስጤም በባልፎር ላይ አወጀች፡፡ ይህንን የተመለከቱ ወታደሮች ወደ ቤይሩት (ሊባኖስ) ከዛም በመርከብ ተሳፍሮ ወደ ሃገሩ እግሬ አውጪኝ እንዲል አደረጉት፡፡

በመጀመሪያዎቹ 10 አመታት ብቻ 76400 አይሁዳዊያን (አብዛኞቹ ከምስራቅ አውሮፓ) ወደ ፍልስጤም እንደገቡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የቁጥሩ ማሻቀብ ስጋት የገባቸው ፍልስጤማዊያን የፅዮናውያንን እንቅስቃሴ በቻሉት ሁሉ ለማስቆም መታገል እንዳለባቸው አሰቡ፡፡

ይህ በንዲህ እንዳለ በሴፕቴምበር 1928 የተፈጠረው የአል-ቡራቅ ክስተት በሁለቱ ጎራዎች መካከል ሰላማዊ አየር ሊነፍስ እንደማይችል ያመላከተ ፍንጭ ነበር፡፡

አይሁዳዊያን የእኛ ብቻ የሆነውን የአል-ቁድስ መስጂድ ምዕራባዊ ግድግዳ ላይ እጃቸውን ለማሳረፍ ሙከራ አደረጉ፡፡ ይህ ነው ደም አፋሳሽ ክስተቶች የያዘውን የቡራቅ አብዮት እንዲፈነዳ ምክንያት የሆነው፡፡ ከዚህ በኋላ ፍልስጤማዊያን በ አል-ኸሊል (ሄብሮን)፣ናቡለስ፣ባይሳን እና ሳፋድ ውስጥ የሰፈሩ አይሁዳዊያን ላይ ጥቃት አደረሱ፡፡

በአፀፋው የእንግሊዝ ወታደሮች ከአይሁዶች ጋር በመሆን ወደ ግብፅ የጦር ሃይል እርዳታን በጠየቁት ላይ እርምጃ ወሰዱ ፡፡ የእግረኛ ጦራቸውን፣ግዙፍ የጦር መርከባቸውን እና የአየር ሃይላቸውን በመጠቀም አመፁን ለማፈን ጥረት ሲያደርጉ ዴር ያሲን እና ሊፍታን የመሳሰሉ መኖሪያ ቦታዎች ፈራረሱ፡፡

ፍልስጤም ትኩሳት ያዛት ፤ እዚም እዛም ፀብ፣ብጥብጥ፣እልቂት ሆነ፡፡ በዚህም ከአንድ ሺህ በላይ (አብዛኞቹ አረቦች ነበሩ) ሰዎች ፍርድ ቤት ሲቀርቡ 26ቱ የሞት ፍርድ ተፈረደባቸው (25ቱ አረቦች ነበሩ)፡፡

በ1930 የፈላሾች ቁጥር 104750 ከዛም በቀጣይ 6 አመታት 284645 (ሳይመዘገቡ እና በህገወጥ መንገድ የገቡ ሳይቆጠር) ደርሶ ነበር፡፡

ክፍል 4 ይቀጥላል…ኢንሻአሏህ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የፍልስጤም ታሪክ

ምዕራፍ -2

እስራኤል ክፉ ፅንስ

ክፍል-2

[ተፃፈ-በአብዱልከሪም ሙሐመድ]

ከአንደኛው አለም ጦርነት በኋላ የእንግሊዝ ወታደሮች ትልቅ ውዥምብርን ፈጥረው ወደ ፍልስጤም ምድር ሲገቡ ከወራሪነት ይልቅ እንደነፃ አውጪ ግንባር ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸው ነበር፡፡ ሆኖም ግን የወቅቱ ኃያልን እግር በግር ተከትለው የመጡት ፅዮናውያን የአረቡን አለም ከረፈደም ቢሆን እንዲነቃ አድርጓል፡፡ የወራሪዋ ወታደራዊ አገዛዝም ፍልስጤምን ለአይሁዳዊያን ብሔራዊ መኖሪያ ለማድረግ ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም፡፡

92% አረቦች ባሉበት ሀገር ላይ ለመስማት የሚሰቀጥጥ ፣ ለአይን የሚከብድ ፣ ለህሊና የሚቆረቁር የፅዮናውያን ኮሚቴ የሚያልሙትን መኖሪያ ቤት የመደረብ ቅጥፈትን አለም መስክራለች፡፡ ለታሪክ እንደተቀመጠውም የሆነው ይህ ነው፡፡ በሊግ ኦፍ ኔሽን (የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት) ውሳኔ መሰረት ወራሪዋ እንግሊዝን የፍልስጤም ሞግዚት በአደራ መልክ የማስተዳደር ስልጣን በ1923 ሰጣት፡፡

ሊግ ኦፍ ኔሽን ከመጀመሪያው አለም ጦርነት በኋላ የተመሰረተ ሲሆን በጦርነቱ የተሸነፉ ሃገራትን ለመጫን እንዲሁም አሸናፊዎቹን (ዋና መስራቾቹ ማለት ነው) ደግሞ የደረሰባቸውን ኪሳራ የትም ፍጪው እንደሚለው አባባል መሸፈን እንዲችል በአለም ላይ የሾመ ቀጣፊ ድርጅት ነው፡፡ በሁለተኛው አለም ጦርነትም ጀርመን ፀብ እንድትጭር ሆድ ያስባሳትና ያ ሁሉ እልቂት እንዲፈጠር ይህ በአጭሩ የተቀጨው ህብረት የጎላ አስተዋፅኦ ነበረው፡፡

ለእንግሊዝ ይህንን መወሰኑም አዲስ ነገር ሳይሆን ቀድማ የነበራትን ቁጥጥር ህጋዊ ማስመሰል ነበር፡፡ በዚህም መሰረት እስከ 1948 ድረስ ለዳግም ወረራ ለአይሁዳዊያን ስታመቻች ቆየች፡፡

ፍልስጤማዊያንም ተሰባስበው የተቃውሞ ድምፅ በሚያሰሙ ግዜ አንዳንዴ ከወታደሮች ጋር ሌላ ግዜ ደግሞ ከፅዮናዊያን ጋር ግጭት ውስጥ መግባት የለትተለት ስራቸው ሆኖ ነበር ማለት ይቻላል፡፡

የባልፎር አዋጅ በኖቬምበር 2 1917 እንግሊዘኛው አርተር ጀምስ ባልፎር ያቀረበው ሀሳብ ለእስራኤል በመመስረት ከምንም በላይ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተ ነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ ያንን እያነሱ የሚከራከሩ ብዙ እስራኤላዊያን አሉ፡፡

Balfour Declaration 1917

November 2nd, 1917

Dear Lord Rothschild,

I have much pleasure in conveying to you, on behalf of His Majesty's Government, the following declaration of sympathy with Jewish Zionist aspirations which has been submitted to, and approved by, the Cabinet.

"His Majesty's Government view with favour the establishment in Palestine of a national home for the Jewish people, and will use their best endeavours to facilitate the achievement of this object, it being clearly understood that nothing shall be done which may prejudice the civil and religious rights of existing non-Jewish communities in Palestine, or the rights and political status enjoyed by Jews in any other country."

I should be grateful if you would bring this declaration to the knowledge of the Zionist Federation.

Yours sincerely,

Arthur James Balfour

ክፍል 3 ይቀጥላል ... ኢንሻአሏህ

Send as a message
Share on my page
Share in the group