Translation is not possible.

ዑመር ረዐ ድንገት ረሱል ሰዐወ ወደተኙበት ደሳሳ ጎጆ ሲገባ ህመሙን

ሚያብስበት ትዕይንት ተመልከተ።

እዝያች ደሳሳ ጎጆ ውስጥ በተነጠፈች ብጣሽ የግመል ቆዳ ላይ ረሱል ሰዐወ

በሳር የተሰራ ትራስ ተንተርሰው ተኝተዋል።

የተኙባት ቆዳ አርጅታ ጫፍ ጫፏ ተበላልቷል። የቆዳው ድርቀት መላ ሰውነታቸው

ላይ ሰንበር አውጥቶ ገላቸው ተጎድቷል።

ከተኙበት ክፍል ቁና እማትሞላ ገብስ በስልቻ ተደርጎ ጥግ ላይ ተቀምጧል።

የድህነት መገለጫዎችን በሙሉ ዑመር ከረሱል ሰዐወ ቤት ሲመለከት ስሜቱ

አስገድዶት እንባውን ያፈስ ጀመር።

ነቢ እንባውን ተመለከቱት፦‹‹ዑመር ምን ሁነኃል? ለምን ታለቅሳለህ?››

አሉትም።

ዑመር ረዐ ሲቃ ከሚተናነቀው ድምፅ ጋር ግብግብ እየፈጠረ፦‹‹ነቢዋ! ገላዎት

ባለቀ የቆዳ ንጣፍ ሰንበር አውጥቶ እያየሁ እንዴት አላልቅስ?! ከርስዎ ክፍል

ይህችን ምታክል ገብስስ እየተመለከትኩ እንዴት አላልቅስ?!

የሮም እና የፐርሺያ ንጉሳን በወርቅ እና በአልማዝ ባሸበረቁ አልጋዎች ላይ የሀር

ጨርቅ አንጥፈው በፍራፍሬዎች እልፍኝ ተደላድለው ሲኖሩ እርሶ የአላህ ነቢይ

እና ውድ ሁነው እንዴት?! ›› ብሎ የቁጭት ለቅሶውን ቀጠለ።

ነቢ ፈገግታ ከፊታቸው እያስነበቡት እንዲህ አሉት፦‹‹ዑመር! እነሱ እኮ

ድሎታቸው የፈጠነላቸው ሰዎች ሲሆኑ በቅርቡ ከድሎት ይቋረጣሉ።

እኛ ደግሞ ፀጋዎቻችን ወደ ጀነት የተሸጋገረላቸው ህዝቦች ነን፤ ታድያ ዱንያ

ለነሱ ሁና አኪራ ለኛ እንድትሆን አትፈልግም እንዴ? ››

ዑመር ንግግራቸው ቢያሳምነውም ምቾት አልሰጠውም፦‹‹ነቢዋ! ታድያ ሌላው

እንኳ ቢቀር ለምን ከዚህ ለስለስ ባለ ምንጣፍ ላይ አይተኙም? ›› አላቸው

በስስት እየተመለከተ።

ነቢ ጉዳዩን ግልፅ ሊያደርጉለት ፈለጉና ጠንከር አሉ፦‹‹ዱንያ እና እኔን ምን

አገናኘን?! እኔ እና ዱንያ ማለት እኮ ልክ የበረኃ ተጓዥ በአንዲት ጥላ ተጠልሎ

ፀሀይዋ ስትበርድ ጉዞውን እንደሚቀጥለው ነው እኮ (ጥላዋ ስር እድሜ ልኩን

አይኖርም)›› አሉት።

ሰላሏሁ አላ ነቢዪና ሙሐመድ

ከumma media

Send as a message
Share on my page
Share in the group