UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

ኢማሙል_ቡኻሪይ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«ከሙስሊሞች በላጩ ከመልእክተኛው ﷺ ሱናዎች ውስጥ የተዘነጋችን ሱና ህያው ያደረገ ነው። የሱንና ባለቤቶች ሆይ! አላህ ይዘንላችሁና ፅኑ። እናንተ አናሳዎች ናችሁና።»

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሙስሊም አማራ አለ ግን?

~

በተያያዘው ቪዲዮ ላይ የሚታዩት ማኅበረ ደና ቁራ ን እንደሚያስተጋቡት የአማራ ህዝብ የአይሁድ ነገድ አይደለም። ይሄ ፍጥጥ ያለ ውሸት ነው። እንዲያውም "የአይሁድ ነገድ ነን" የሚል አካል በራሱ ላይ "መጤ ነኝ" ብሎ እየመሰከረ ነው። በርግጥ መጤነት የሰለጠኑ ሰዎች ዘንድ ነውር አይደለም። ነውር የሚሆነው በመጤነታቸው የሚኮፈሱ አካላት ሌሎችን "መጤዎች" እያሉ ሊያነውሩ ሲሞክሩ ነው። እንዲህ አይነቶቹን ነውር ጌጡዎች በ"ነውራችሁ" አታጊጡ ብለን እናስታውሳለን።

መታወቅ ያለበት ሐቅ ብሄርና ቋንቋ በዘመናት ውስጥ ውልደት፣ እድገትና ሞት ያስተናግዳሉ። አንድ የነበረ ቋንቋ በአካባቢ መለያየትና መራራቅ የተነሳ በሂደት የተለያየ ቋንቋ ወደመሆን ሊቀየር ይችላል። ይሄ ውልደት ነው። ከሌሎች ቋንቋዎች እየወሰደ የሚዳብርና የሚሰፋም አለ። የቋንቋ እድገት አንዱ መገለጫ ይሄ ነው። የተለያዩ ቋንቋዎች በሌሎች ተውጠው ሊጠፉም ይችላሉ። ይሄ የቋንቋ ሞት ነው። በውጭው በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በዐረብኛ፣... ተውጠው ብዙ ቋንቋዎች ሞተዋል። በሃገራችንም የከሰሙና በመክሰም ላይ ያሉ ቋንቋዎች አሉ።

የአማራ ብሄርና ቋንቋም በዘመናት ውስጥ ሌሎች ህዝቦች የቋንቋው ተናጋሪ በሆኑ ቁጥር እየሰፋ የመጣ ቅይጥ ማንነት ነው። የጋፋት ቋንቋ በዚህ ዓይነት ሂደት ጠፍቷል። የአርጎባ ህዝብ የራሱን ቋንቋ ጥሎ የአማርኛና የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሆኗል። ይሄ የአማርኛ ብቻ ሳይሆን የብዙ ቋንቋዎች የጋራ ባህሪ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በታሪክ አማራ የሚለው ቃል ክርስቲያን ማለት እንደነበር እስከ ቅርብ ጊዜ የሚታወቅ ነው። ይህ የሆነው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪው በአመዛኙ ክርስቲያን በመሆኑ እንጂ አማራነት በራሱ ክርስትና ስለሆነ አይደለም። ብሄር ማለት የጋራ ቋንቋና ማንነት ያላቸውን ህዝቦች ለመግለፅ እስከዋለ ድረስ በእምነት ቢለያዩም አማርኛ ቋንቋ የሚያገናኛቸው ህዝቦች አሉ፣ ዛሬ። ትኩረቴ አማራ ከሚለው ጥሬ ቃል ላይ አይደለም። ወደ ኋላ ረዘም ያለ ዘመን ብንመለስ ብዙ ብሄሮችን የዛሬ ስማቸውን ከነ ጭራሹ አናገኝም። ይሄ ማለት የጋራ ማንነት አልነበረም ማለት አይደለም።

ስለዚህ ዛሬ የትናንቱ የአማራነት ፅንሰ ሃሳብ የለም። አማራ ማለት ዛሬ ብሄር እንጂ ሃይማኖት ገላጭ አይደለም። በብሄር መለኪያ ከአማርኛ ተናጋሪው ክርስቲያን ጋር አንድ የሆኑ ሙስሊሞችን "አማራ አይደላችሁም" አይባልም። ብሄሩ ውስጥ የመሸጉ ገፊ አካላት መኖራቸውም የሚቀይረው ነገር የለም። "ትግሬ ብሎ ሙስሊም የለም" ብለው የሚያምኑ አግኣዚያን ስለኖሩ ሙስሊም ትግሬዎችን ትግሬነታቸውን መግፈፍ አይቻልም። "የኦሮሞ ነባር እምነት ዋቄፈና ነው" የሚሉ አካላት ስላሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊምና ክርስቲያን ኦሮሞዎችን ኦሮሞነታቸውን መግፈፍ ይቻላል? አይሆንም። በብሄርና በቋንቋ የለየንኮ ፈጣሪ እንጂ ፖለቲከኞች አይደሉም። ከአፋር ቤተሰቦች የተወለደን አካል አፋርነቱን መፋቅ ይቻላልን? እንኳን ሌሎች ራሱም መቀየር አይችልም። የአማራ ሙስሊሞችም ጉዳይ እንደዚያ ነው።

ጉዳዩ በቁጥር ማነስና መብዛት የሚወሰንም አይደለም። በዐረቡ ዓለም ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖች 5% አይሞሉም። ቁጥራቸው ስላነሰ ዐረብነታቸውን መንጠቅ እንችላለን? አይሆንምኮ! በአማራ ፖለቲከኞች አግላይ አካሄድ ሰበብ በክልሉ ውስጥ ያሉ ከ17% (በመንግስት ህዝብና ቤት ቆጠራ ከተቀመጠው) በላይ ሙስሊሞችን ብሄር የለሽ ናቸው ልንል ነውን? አንችልምኮ! ደግሞም ራሱን በሆነ ብሄር የሚገልፅ አካል "እናንተ ግን ብሄር የላችሁም" ማለት አለበት ወይ? አይባልም። ስለሆነም ሙስሊም ወገኖቻችንን ራሳቸውን በአማራነት ስለገለፁ የምንተችበት አካሄድ ፈፅሞ የተሳሳተ ነው። ማድረግ ያለብን ዘረኝነት ሲጎትታቸው ካየን ከየትም ብሄር ቢሆኑ አላህን እንዲፈሩ ማስታወስ ብቻ ነው። እንጂ አማራ ተብለው እየተገደሉበት፣ እየተገፉበት ያለን ማንነት የለም አይደላችሁም አይባልም።

ስለዚህ  ዛሬ አማራነትን ክርስቲያን ማለት አድርጎ የሚገልፅ ካለ ምሁርም ይሁን መሀይም፣ ደጋፊም ሆነ ነቃፊ ያለ ጥርጥር ተሳስቷል። ይሄ አተረጓጎም የህዝቦችን ማንነትና ማህበራዊ ውቅር ተለዋዋጭነት (dynamism) ከግንዛቤ ያላስገባ ግልብ ድምዳሜ ነው። ስያሜዎች በዘመናት ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች እንደ አካባቢው ሁኔታ ይለዋወጣሉ።

* ትናንት ቱርክ፣ ደይለም፣ ፋርስ የሚሉት መጠሪያዎች ሙስሊም ያልሆኑ ህዝቦችን ለመግለፅ የዋሉበት ዘመን ነበር፣ ለሚታወቅ ምክንያት። ያ ዘመን ካለፈ በኋላ እነዚህ ስያሜዎች ሃይማኖትን ገላጭ የነበረው ይዘታቸው ቀርቷል። አማራም ላይ ያለው እውነታ ተመሳሳይ ነው።

* በፊት አጎራባቾቹ አማራና አርጎባ መሀል የነበረው እውነታም ይህንን አጉልቶ ያሳያል። ሰሜን ሸዋ ላይ አንድ ክርስቲያን አማራ ወደ ኢስላም ሲገባ "እከሌ አርጎባ ሆነ" ነበር የሚባለው። አንድ አርጎባ ወደ ክርስትና ሲገባ ደግሞ "አማራ ሆነ" ነበር የሚባለው። ዛሬ ግን አርጎባነት ዘር እንጂ ሃይማኖት እንዳልሆነ ግልፅ ነው። አንድ ሰው ሃይማኖቱ ስለተቀየረ ዘሩ እንደማይቀየር ማወቅኮ ያን ያህል ውስብስብ ሂሳብ አይደለም።

* ሲዳማ የሚለው ቃል ሃይማኖትን ሲገልፅ የነበረበት ዘመንም ነበር። ዛሬ የሲዳማ መስሊሞችን "ሲዳማ አይደላችሁም፣ ሙስሊሞች ናችሁ" ልንላቸው አንችልም። ምክንያቱም ሲዳማነት እንደ ትላንቱ ሃይማኖትን ሳይሆን የሲዳማ ቋንቋ በወል የሚያገናኛቸው ህዝቦችን የሚገልፅ የብሄር ስያሜ እንደሆነ ግልፅ ነውና። ይሄ ቀላል ግንዛቤ አማራ ዘንድ ሲደርስ መልኩን የሚቀይርበት ስሌት የለም።

ስለዚህ የአማራ ሙስሊሞች ከብሄር አንፃር እንዴት ራሳቸውን አማራ ብለው ይጠራሉ የሚል አተካራ ውስጥ መግባት አያስፈልግም። ይሄ ብሄር ተኮር ጥላቻና መነቋቆርን ከማምጣት ባለፈ የሚያመጣው ኸይር የለም። ማድረግ ያለብን በየትኛውም ብሄር ውስጥ ያደፈጡ ዘረኛ ቡድኖች መጠቀሚያ እንዳንሆን ተቆርቋሪነት በሚታይበት መልኩ እርስ በርሳችን መመካከር ነው። ዋናው ነገር ኢስላማዊ ወንድማማችነታችን የዘር አጥር የሚገድበው አለመሆኑ ነው። የላ ኢላሀ ኢለላህ ገመድ ከዘርና ከቋንቋ በላይ ነው። ዛሬ ስለታመምን እንጂ ለሙስሊሙ አማራ ከነሷራው አማራ በላይ ሙስሊሙ ኦሮሞ ነው የሚቀርበው። ለሙስሊሙ ኦሮሞ ከነሷራው ኦሮሞ በላይ ሙስሊሙ አማራ ነው የሚቀርበው። በጠጣነው ፖለቲካዊ መርዝ ሳቢያ ቢተናንቀንም እውነታው ያ ነው። በዘር ቢሆን ለውዱ ነብያችን ﷺ ከሐበሻው ቢላል በላይ አጎታቸው አቡ ለሃብ በስጋ ይቀርባቸው ነበር። ኢስላማዊው መለኪያ ግን ሌላ ነው። ኢማንና ዘር እኩል ሚዛን ላይ አይቀመጡምና።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ 27/1445፣ (ታህሳስ ዐ1/2016))

=

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የወሎ ልጅ...

--------------

መከራ ያልናደው የትዕግስቱን መጠን፡

የሀበሻ ኩራት ሞደል የመሰልጠን፡

በፅናት የኖረ በዘመን መካከል፡

ትልቅ ውለታ አለው ለሀገር መስተካከል፡

በፍቅር ይሸኛል ሁሉን ተቀብሎ፡

ዛሬም አልሰለቸም ያስታውቃል ወሎ፡

---------------------

ወሎ የሰውን ልጅ በጃኬቱ አይለካም፡

ለትንሽ ለትልቅ ለሁሉም ነው መልካም፡

ሴቱንም ወንዱንም መመጥፎ አይን አይነካም፡

-------------------------

ጠላት ምን ቢለፋ ሁሌም ቢታገለን፡

በአሏህ ጥበቃ ሙሀባን ታድለን፡

ፍቅርን አርማ አድርገን ዛሬም ድረስ አለን..

ሰላም ነው አርማችን በሩቁ ይታያል፡

ቸርነት ደግነት ወሎላይ ይለያል፡

----------------------------

ታሪካችን ፈርሶ የዘመመው ጎጆ ደርሶ ባይቃናም፡

ደስ ይለናል እንጂ ምቀኝነት ይዞን በሰው ሀብት አንቀናም፡

በእምነታችን ብቻ በተደጋጋሚ ምን ብንታረድም፡

በኛ የደረሰው በሌሎች እንድደርስ በፍፁም አንፈቅድም፡

ወሎ ይታወቃል ሰውን አይሸውድም፡

ያገኘውን ሁሉ ያቅፋል እንደ ወንድም፡

ህጉ ቢቀያየር ቢጠብቅም ቢላላም፡

ባህሉ ነው ወሎ ብቻውን አይበላም፡

ውደታን ነው እንጅ ገንዘብ አያሰላም፡

---------------------

ለሰው ጦር አንሰብቅም ይህን ማንም ያውቃል፡

ሁሌም ታጋሾች ነን በጣም ያስደንቃል፡

ካጉረመረምን ግን፤

በድምፃችን ብቻ ብዙ ወንድ ይወድቃል፡

---------------------

ንፁህ ነን ለማንም፤

ሰበብ እየፈለግን ቂም አናንጠለጥል፡

ምንም አይገርመንም፤

ማንም ስማችንን እያነሳ ቢጥል፡

የውብ ህዝብ ልጅ ነን፤

የፍቅር ሰገነት የወሎ ቅምጥል፡

---------------------------

በጎጥ አንከለል በብሔር አናምንም በዘር አንመካም፡

ፍቅር ነው አርማችን ታሪክ ምስክር ነው ተንኮል አናቦካም፡

ወሎ በታሪክ ውስጥ፤

ማንንም አልገፋ ማንንም አልነካም፡

ከነውረኛወች ጋር አንልከሰከስም፡

ቃሉ ይታወቃል ወሎ የሚሉት ስም፡

አብሽር ወሎ

✍️

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

➴ስሚኝማ እህቴ አንደየ ልንገርሽ

➴  እዉቀትን  ተማሪ ሌላዉንም ትተሽ

➴በየኮሜንቱ ስር መለቅለቁን ትተሽ

➴በየሶሻል ሚዲያ መደለቁን ትተሽ

➴የመዳም ሸበካ ከተመቼኝ ብለሽ

➴ባሻሽ አትሩጪ ተማሪ ቁጭ ብለሽ

➴ያየሚያይሽ ሁሉ እዉነት እንዳይመስልሽ

➴በቃል እያሻሸ ማሻአላህ ቢልሽ

➴ላይሽም ተዉቦ ቃሎች ደልለዉሽ

➴ዉስጥሽ በንፍቅና  የተሞላሽ ከሆንሽ

➴የዛኔ ጅህልና ይመጣል ሊወርሽ

➴ስለዚህ እህቴ  ተማሪ ቁጭ ብለሽ ::

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ለፃፈልሺ ሁሉ መልስ አታዘጋጅ አይተሺ እዳላየሺ መተውን ልመጅ!

የአሁኑ ጅጀና በጣሙን ይገርማል ሰላምታ ጀምሮ ሶለዋት ያወርዳል የአላህን ስም ጠርቶ ወሬ! ይጀምራል  ለእንደዚህ አይነቱ ሰላምታ አትመልሺ።

በመጣበት ይሂድ አስፈጥረሺ አውጭ ብሎክ አድረጊና!!

አጠናግረሺ ሸኝ በርሺን ኮልሊ 

አሳምረሺ ዝጊ ላኳኳልሺ ሁላ በሩን አትክፈች!!

አቤት በቃ ቤት ባይመታም ግጥም ተገጠመ¡

Send as a message
Share on my page
Share in the group