Translation is not possible.

የወሎ ልጅ...

--------------

መከራ ያልናደው የትዕግስቱን መጠን፡

የሀበሻ ኩራት ሞደል የመሰልጠን፡

በፅናት የኖረ በዘመን መካከል፡

ትልቅ ውለታ አለው ለሀገር መስተካከል፡

በፍቅር ይሸኛል ሁሉን ተቀብሎ፡

ዛሬም አልሰለቸም ያስታውቃል ወሎ፡

---------------------

ወሎ የሰውን ልጅ በጃኬቱ አይለካም፡

ለትንሽ ለትልቅ ለሁሉም ነው መልካም፡

ሴቱንም ወንዱንም መመጥፎ አይን አይነካም፡

-------------------------

ጠላት ምን ቢለፋ ሁሌም ቢታገለን፡

በአሏህ ጥበቃ ሙሀባን ታድለን፡

ፍቅርን አርማ አድርገን ዛሬም ድረስ አለን..

ሰላም ነው አርማችን በሩቁ ይታያል፡

ቸርነት ደግነት ወሎላይ ይለያል፡

----------------------------

ታሪካችን ፈርሶ የዘመመው ጎጆ ደርሶ ባይቃናም፡

ደስ ይለናል እንጂ ምቀኝነት ይዞን በሰው ሀብት አንቀናም፡

በእምነታችን ብቻ በተደጋጋሚ ምን ብንታረድም፡

በኛ የደረሰው በሌሎች እንድደርስ በፍፁም አንፈቅድም፡

ወሎ ይታወቃል ሰውን አይሸውድም፡

ያገኘውን ሁሉ ያቅፋል እንደ ወንድም፡

ህጉ ቢቀያየር ቢጠብቅም ቢላላም፡

ባህሉ ነው ወሎ ብቻውን አይበላም፡

ውደታን ነው እንጅ ገንዘብ አያሰላም፡

---------------------

ለሰው ጦር አንሰብቅም ይህን ማንም ያውቃል፡

ሁሌም ታጋሾች ነን በጣም ያስደንቃል፡

ካጉረመረምን ግን፤

በድምፃችን ብቻ ብዙ ወንድ ይወድቃል፡

---------------------

ንፁህ ነን ለማንም፤

ሰበብ እየፈለግን ቂም አናንጠለጥል፡

ምንም አይገርመንም፤

ማንም ስማችንን እያነሳ ቢጥል፡

የውብ ህዝብ ልጅ ነን፤

የፍቅር ሰገነት የወሎ ቅምጥል፡

---------------------------

በጎጥ አንከለል በብሔር አናምንም በዘር አንመካም፡

ፍቅር ነው አርማችን ታሪክ ምስክር ነው ተንኮል አናቦካም፡

ወሎ በታሪክ ውስጥ፤

ማንንም አልገፋ ማንንም አልነካም፡

ከነውረኛወች ጋር አንልከሰከስም፡

ቃሉ ይታወቃል ወሎ የሚሉት ስም፡

አብሽር ወሎ

✍️

Send as a message
Share on my page
Share in the group