UMMA TOKEN INVESTOR

omer abate shared a
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
omer abate shared a
Translation is not possible.

አሰላሙ አለይኩም። በመካከለኛው ምስራቅ እጅግ አስከፊ የሆነ ጦርነት በወራሪዋ እስራኤል እና በሀማስ እየተካሄደ ይገኛል። አለም በሁለት ጎራ ተከፍሎ ስለጦርነቱ የተለያዩ ሀሳቦች እየተሰነዘሩ ይገኛል። ወራሪዋ የጋዛ ንፁሀንን ደም እያፈሰሰች ነው። በሆስታሎች፣በገቢያ ማዕከላት እና በሀይማኖት ተቋማት ጭምር የቦምብ እሳት እያዘነበች ትገኛለች። ጭራቋ አሜሪካና ምዕራባዊያን ተከታዮቿ የፍልስጤናውያን ደም መፍሰስ ከቁብ ሳይቆጥሩት ግፋ በለው እያሉ ነው ። የመካከለኛው ምስራቅ እና ሌሎች ሙስሊም ሀገራት ከማውገዝና የተወሰኑት ደግሞ ከማስጠንቀቅ በዘለለ ይህ ነው የሚባል ነገር ሲያደርጉ አይታይም። ለዚህ ደግሞ አንድም ጦርነቱ ወደ ሌላኛው የአረብ ክፍል ተስፋፍቶ ተጨማሪ ውድመት እንዳያስከትልና ሀያላን ሀገራት በሙስሊሙ አለም የሚፈልጉትን ውድመት እውን እንዳይሆንላቸው ጥንቃቄ ከማድረግም ጭምር ይመስለኛል። ታዳ ሁኔታው ይህ ሆኖ ሳለ አንዳንድ የተንሸዋረረ እይታ ያላቸውና ቀደም ብለው ያቀረሸባቸው ጥላቻ ሳኡዲ አረቢያን በተለያየ መልኩ ሲወርፉ እየተስተዋለ ነው ።ሳኡዲ እንደማንኛውም አረብ ሀገር እና የሙስሊም ሀገር በተለያዩ አጋጣሚዎች ወይም ኮንፍረንሶች ጠንካራ ትችት በወራሪዋ ላይ እየሰነዘረች ነው። ለጋዛ ተጠቂዎችም ሰብአዊ እርዳታ ለመላክ እየተሰናዳች ነው።ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ ሳኡዲ የምትገዛው መሳሪያ ሙስሊሙን አለም እንጂ ከሀዲያንን አትወጋበትም፣ ጀቶቿ እና ታንኮቿ ጭምር በፎቶ እያስደገፉ በላያቸው ላይ የሳኡዲ ባንዲራ ላኢላሀ ኢሏህ ሙሀመደን ረሱሏህ የሚለውን የምስክርነት ቃል የያዘውን ባንድራ እያሳዩ ላኢላሀ ኢለላህ ያሉትን ነው የምትወጋው እያሉ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ከፍተዋል። በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ በዚች ቅድስት ሀገር የሚኖሩ፣ ሰርተው የተለወጡ፣ እየተለወጡ ያሉ፣ቤተሰቦቻቸው እየረዱ ያሉ ናቸው እንዲህ አይነት ነውረኛ ዘመቻ የከፈቱባት። ለዚህ ነውራቸው እንደ ምክንያት የሚያቀርቡት የሳውዲ መንግስት አምባገነን ነው ፣ የመንግስት ስልጣኑን የተቆጣጠሩት በዘር ነው። የሚል የወደቀ አመክኒዮ ነው። ማጣቀሻቸውም የቱርክ እና የግብፅ የመንግስት ስርዓት መከተል አለባት ብለው የሚሞግቱ የመንግስት ስርዓት መቀዳት ያለበት ከምዕራቡ አለም የዴሞክራሲ አስተሳሰብ መሆን አለበት እያሉ ነው። መሬት ላይ ያለው ሀቅ ግን የሳዑዲ ህዝብ የተጨቆነ ሳይሆን ደስተኛና በማህበራዊ ህይወቱም ጠንካራ የሆነ ህዝብ ነው። የኑሮ ደረጃውም መልካም የሚባል ነው። የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሁኔታ ከፍተኛና በመካከለኛው ምስራቅ ጠንካራ ኢኮኖሚ እና ጠንካራ ሀገር አድርጓታል። በመንፈሳዊው ወይም በሀይማኖት ጠንካራ እስልምናና ጠንካራ ሙስሊም ያለባት ሀገር ናት። በሱና ደረጃ መልካም የሆነ፣ ኡለሞች የተከበሩባት፣ የሚሰሙባት፣ ያለምንም ጫና የሚያስተምሩባት፣ ስለ ሀገራዊ ጉዳይ የሚመክሩባት፣ምክራቸው የሚሰማባት ሀገር ናት። #እዚህ ላይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ወደ ፖለቲካው ያዘመሙ እና በአንዳንድ ሙስሊም ሀገራት ያለውን ህዝባዊ አመፅ እንዲነሳ የሚፈልጉትን አያካትትም። እነሱ እንደ ሁኔታው በሀገሪቱ ህግ ተቀጥተው ወይም እየተቀጡ ይሆናል። መንግስት ቅዱስ ቦታዎች በሚገርም ሁኔታ ለአለም ሙስሊም ምእመን ምቹ አገልግሎት እንዲሰጡ አድርጎ እያስፋፋ ይገኛል። ምንም እንኳ በቂ ባይሆንም አብዛኛውን የአለም ሙስሊም አምልኮውን በቅዱሳን ቦታዎች በደስታ ፈፅሞ ወደ ሀገሩ ይመለሳል።እንዲህ አይነት የደመቀ ስራ እየታየ ጥላቻው ለምን? በአሁኑም ጦርነት ቢሆን መልካም እንቅስቃሴ እና ትክክለኛ የመፍትሔ መንገድ ከወንድም ሙስሊም ሀገራት ተማክራ እንዲሁም ኡለሞቿን አድምጣ የምትንቀሳቀስ ቅድስት ሀገርን ለማንቋሸሽ የሚጋጋጡት ምን ያህል ጭፍንተኛ ቢሆኑና ጥቅመኛ ቢሆኑ ነው? ጦርነቱ ወደ ሌሎች የሙስሊም ሀገራት ቢስፋፋስ ጠላቶች ቀድመው ለማውደም የሚቋምጡትና የሚዘጋጁት ይህችን ሀገር መሆኑን ለምን ይዘነጋሉ?

ለማንኛውም እስላም ጉዳትና ጥቅም ያመዛዝናል። ትላንትና ዛሬ አንድ አይደለም። እውቀቱንና ማመዛዘኑን ቅድሚያ ለኡለሞችና ለሀገር መሪዎች እንተወው ባይ ነኝ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
omer abate shared a
Translation is not possible.

ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ቢያያት ኖሮ መነሻው እርሱ ዘንድ መድረሻው ፍልስጤም የሆነን ሠራዊት አሰልፎ ጽዮናውያንን ከምድረ-ገጽ ባጠፋቸው ነበር።

ሠይፉላሂል መስሉል ኻሊድ ኢብኑል ወሊድ በህይወት ቢኖር ሰማንያ ሰይፍ እጁ ላይ በተሰበረ ልቡም ሳይቀዘቅዝ ጠላትን አንቀጥቅጦ ምሽጋቸውን ባፈራረሰ።

ጀግናው ሰላሐዲን ቢያያት ኖሮ ከጦርነቱ በፊት መቀበርያ ጉድጓዳቸውን በገዛ እጃቸው ባስቆፈራቸው።

የዘመኔ ባለስልጣናትና ነገስታት አይተዋታል። አሊሙም ሊቃውንቱም ተመልክተዋታል። ከውግዘት ፈትዋ በቀር ግን ምንም አላየንም።

እንደው አላህን እንዴት ትገናኙት ይሆን?!

መልሳችሁስ ምን ይሆን?!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
omer abate Сhanged his profile picture
6 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
omer abate Сhanged his profile picture
6 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group