UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

አንድ ቀን ነገም ሊሆን ይችላል ልብህ ተውበትን ትሻለች እናም ወደ አላህ ለመመለስ ስትጣደፍ የተውባህ በሮች ተዘግተዋል😥

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

وَلَا تُصَعِّرۡ خَدَّكَ لِلنَّاسِ وَلَا تَمۡشِ فِي ٱلۡأَرۡضِ مَرَحًاۖ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخۡتَالٖ فَخُورٖ(18)

"ጉንጭህንም (በኩራት) ከሰዎች አታዙር፡፡በምድርም ላይ ተንበጥርረህ አትሂድ፡፡ አላህ ተንበጥራሪን ጉረኛን ሁሉ አይወድምና!!"

Surah Luqman;18

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

«ጥንቃቄ‼️

ሼርርርር‼️ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ብዙ ወጣት ሴቶች በሚዝናኑባቸው ቦታዎች ትላልቅ ከተማዎች ላይ GHB የሚባል ኬሚካል ተበራክቷል። "ጋባዦች" አንድ መጠጥ ውስጥ የGHB ጠብታ ሲጨምሩበት ተጠቂዎች (አብዛኛውን ጊዜ ሴቶች) በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ያሉበት፣ አብረዋቸው የነበሩበትን እና የተወሰዱበትን ቦታ አያስታውሱም። ገንዘብ ተከፍሏቸው የደነዘዙ ሴቶችን ለማስደፈር የሚያቀርቡ ውጣት ወንዶችም ሴቶችም ይሄንን እየሰሩ የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው። በተለይ "የቤት ልጅ" አይነት የሚባሉ (ተማሪዎች) እና ሌሎች ወጣት ሴቶች የዚህ ወንጀል ተጠቂ እየሆኑ ነው። GHB ከሰውነታቸው ወጥቶ ሲነቁ በማይታወቅ ቦታ ብዙ ጉዳት ደርሶባቸው ራሳቸውን ያገኛሉ። ምን እንደተፈጠረ አያውቁም። GHB የሰው ሕይወት ሊያጠፋ ይችላል። በከተሞች መዝናናት እና መገባበዝ ደግሞ የተለመደ ስለሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። እንዲህ አይነት ወንጀሎች በቅርብ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ውጪ ከኖሩ ኢትዮጵያውያን ነው።»

©: ኢብኑ ሙነወር

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ከትናንቱ የሼይኽ ተውፊቅ ሳይግ የጁምዓ ኹጥባ በጥቂቱ የተወሰደ

ከምስራቅ አፍሪካውቷ ሀገረ ኤርትራ ተገኝተው በአለም አቀፍ ደረጃ ተደማጭነትን ካገኙ ቃሪዖች እና ኻጢቦች መካከል አንዱ መሆን የቻሉት ሼይኽ ተውፊቅ ሳይግ ስለ ሀበሻ ታላቅነት በሚያስደምም የንግግር ጥበባቸው የዘነጋነውን ቦታችንን አስታውሰውናል

በጁምዓ ኹጥባቸው በፍልስጤም ምድር እየሆነ ባለው አሳዛኝ እልቂት ሁላችንም ልባችን እየደማ መሆኑን ከማስታወስ ጋር ለኢስላም የዳዕዋ ጥሪ ጥላ ከለላ መሆን በቻለችው የሀበሻ ምድር ላይ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል::

አርደል መህሸር (የመሰብሰቢያው መሬት) ከተባለቺው ሻም አስቀድሞ ፣ ኢማን የመናዊ ነው ከተባለላት የመን አስቀድሞ ከምርጦቹ ሀገር ሚስርም አስቀድሞ፣ ሌላው ቀርቶ ከታላቋ የስሪብ መዲናም አስቀድሞ የታላቁ ነብይ ባልደረቦች  የመጀመሪያው የኢስላምን ብርሀን ሊተክሉ የመጡት እዚሁ የሀበሻ ምድር ላይ መሆኑን፣ እንዲሁም በድርቁ ወቅት በረከቱል ሀበሺያ የረሱል ተንከባካቢ እንደነበረችው ሁሉ ሀበሻም እንዲሁ በከባዱ ወቅት ለሳቸውን ዳዕዋ መጠጊያ ሆና ጥላ ከላላ የሰጠች የተባረከች ሀገር መሆኗን አስታውሰዋል::

የሀበሻ ምድር ላይ ሰሀቦች ብቻ ሳይሆን ፣ የረሱለላህ ሴት ልጅና የሰይደና ዑስማን ባለቤት የሆነቺው ሩቅያን ጨምሮ ብዙ አህለል በይቶችም እንደተመላለሱባት በማስታወስ ከሁሉም ቀዲም እና ፊት የሆነች ሀገር እንዳለን በማስታወስ ጥንት ብቻ ሳይሆን ዛሬም የሀበሻ ሙስሊሞች ቦታው ኃላ ሳይሆን ከፊት መሆኑን አውቆ በሁሉም ነገር ቀዳሚ እና ፊት መሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል::

ትውልዱ የትላንት ታሪኩን ሌሎች ከሚመሰክሩለት በላይ ሊያውቅ እና ዛሬም እንደ ጥንቱ የኢስላምን ብርሀን በመጠበቅ እና በማዳረስ ቀዳሚ መሆን እንደሚገባው በተለይ ወጣቱ ሊዘነጋው አይገባም::

ኡማ ቲቪ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ኡሁድ ተራራ!

ከአነስ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿هَذَا جَبَلٌ يُحِبُّنَا وَنُحِبُّهُ﴾

“ይህ ተራራ እሱም ይወደናል እኛም እንወደዋለን።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 4083

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group