UMMA TOKEN INVESTOR

About me

{ وَلَا تَحۡسَبَنَّ ٱللَّهَ غَـٰفِلًا عَمَّا یَعۡمَلُ ٱلظَّـٰلِمُونَۚ إِنَّمَا یُؤَخِّرُهُمۡ لِیَوۡمࣲ تَشۡخَصُ فِیهِ ٱلۡأَبۡصَـٰرُ }

Translation is not possible.

#ibnu_munewor

እውን የኢብኑ ተይሚያ መታሰር የዐቂዳቸውን መበላሸት ያሳያልን?

~

ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ በፅንፈኛ ሱፊዮችና አሽዐሪዮች በሃሰት ተከሰው፣ በግፍ ታስረው ወህኒ ቤት እያሉ ነው የሞቱት። የሚደንቀው ታዲያ እነዚህ አካላት እራሳቸው ከስሰው ካሳሰሯቸው በኋላ ወህኒ ቤት ውስጥ መሞታቸውን ዛሬም ድረስ ለትችት መጠቀማቸው ነው። ፊት ለፊት ተከራክሮ መርታት፣ ተናግሮ ማሳመን፣ ፅፎ ፍርድን ለአንባቢ መተው ነበር እንጂ ሹማምንትን ተጠቅሞ ካፈኑ በኋላ መክሰስማ ከፍትህ እልፍ አእላፍ ማይል የራቀ ነው። ጭራሽ እራሳቸው እየከሰሱ እራሳቸው እየፈረዱ ካሳሰሩ በኋላ የትላንት ፍርደ ገምድል ውሳኔያቸውን ዳግም ለማሳጣት ማዋል ግን የሐያእ መቅለልንም የሚያሳይ ነው።

አዎ ትላንት ጠላቶቻቸው ተረባርበው የዘመቱባቸው መረጃን በመረጃ የመሞገት አቅሙ ስላልነበራቸው ነበር። “ማን ይናገር የነበረ” ነውና በዚያው ዘመን የነበሩት ኢብኑ ፈድሊላህ አልዑመሪይ እንዲህ ይላሉ፡-

“በግብፅም በሻምም የፉቀሃእ እና የቃዲዎች ህብረት ተነስቶ በእግር በፈረስ ዘምቶበታል። ግና ሁሉንም በጣጥሶ ግልፅ በሆኑ ማስረጃዎች ብርቱ አያያዝ ያዛቸው። መቋቋም ሲያቅታቸው ግን መኳንንትና ገዢዎችን ተጠቀሙ።” [አረዱል ዋፊር፡ 84]

በድሩዲን አልዐይኒይም እንዲህ ይላሉ፡- “የታሰረው በግፍና በበደል ነው። ስለዚህ በዚህ ላይ የሚነወርበት ነገር የለም። በርካታ ታላላቅ ታቢዒዮች ላይም ግ ድያ፣ ተጠፍሮ መታሰር፣ ወህኒ መግባትና ባደባባይ መንቋሸሽ ደርሷል። አልኢማም አቡ ሐኒፋ ረዲየላሁ ዐንሁ ታስረዋል፣ የሞቱትም በእስር ላይ እያሉ ነው። ከዑለማእ አንድ እንኳን መታሰራቸው ሐቅ ነው ያለ አለን? ኢማሙ አሕመድም እውነትን በመናገራቸው ሳቢያ ታስረዋል፣ ተጠፍረዋል። ኢማሙ ማሊክም በጂራፍ ከባድ ድብደባ ተደብድበዋል። ኢማሙ ሻፊዕይም ከየመን ባግዳድ ተጠፍረው ታስረው ተወስደዋል። ስለዚህ በዚህ ኢማም ላይ በነዚያ ታላላቅ ኢማሞች ላይ የደረሰው አይነት ቢደርስበት እንግዳ አይደለም።” [አሸሃደቱ ዘኪያህ፡ 76-77]

ስለዚህ መታሰርና መገፋት በኢብኑ ተይሚያ አልተጀመረም። አልዐይኒይ ከጠቀሷቸው ውጭ ሌሎችም በርካታ ዑለማዎች በግፍ ተገድለዋል፣ ታስረዋል፣ ተንገላተዋል። ሰዒድ ብኑ ጁበይር፣ ሰዒድ ብኑል ሙሰይብ፣ ሐሰኑል በስሪ፣ ቡኻሪ፣… ብዙ ግፍ ካስተናገዱ ዑለማዎች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው። ከዚህ ሁሉ ምሁራን በላይም ነቢያት ተንገላተዋል። ለዚህም ነው ነቢዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸው፡-

“ከሰው ሁሉ ፈተና የሚበረታባቸው ነቢያት ናቸው። ከዚያም ታላላቅ ሰዎች እንደ ደረጃቸው። ሰው በዲኑ ልክ ይፈተናል። ዲኑ ጠንካራ ከሆነ ፈተናው ይበረታል። ዲኑ ላይ መሳሳት ካለ በዲኑ ልክ ይፈተናል።” [አሶሒሐህ፡ 143]

አልኢማም ኢብኑል ቀይም ረሑመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “በጥንት ዘመን ሰልማኑል ፋሪሲይ የታደሉት ማስረጃ ከአባቶቻቸው የእሳት አምልኮ እምነት ከፍ ቢያደርጋቸው ጊዜ በዚህ የባእድ አምልኮት ላይ አባታቸውን መሞገት ያዙ። በማስረጃ ሲረቱት ጊዜ ግን መልሱ እስራት ነበር የሆነው። ይሄ የሀሰት ተጣሪዎች ከጥንት ጀምሮ የሚቀባበሉት መልስ ነው። ፊርዐውንም ለሙሳ የሰጠው መልስ ይሄው ነበር።

لَئِنِ ٱتَّخَذۡتَ إِلَٰهًا غَيۡرِي لَأَجۡعَلَنَّكَ مِنَ ٱلۡمَسۡجُونِينَ [الشعراء: 29]

‘ከኔ ውጭ አምላክን የምትይዝ ከሆነ በርግጥም ከእስረኞቹ አደርግሃለሁ’ በማለት። ጀህሚያዎች ለኢማሙ አሕመድ የሰጧቸው መልስም ይሄው ነበር፣ ያኔ በአለንጋ የገረፏቸው ጊዜ። የቢድዐ ሰዎች ለሸይኹል ኢስላም የሰጡት መልስም ይሄው ነበር።” [አልፈዋኢድ፡ 53]

ኢብኑል ወርዲ ረሒመሁላህ የኢብኑ ተይሚያን ሞት ተከትሎ ከገጠሙት ረጅም የግጥም መድብል (ረሣእ) ውስጥ ጥቂት ልጭለፍ፡-

“ከገድሉ መድረስ ቢያቅታቸው … ከደረሰበት መድረሱ

በሴራ ራሳቸውን አቃጥለው … በምቀኝነት ታመሱ።

ታካች ሰነፎች ቢሆኑም … ከመልካም ፈለጉ የራቁ

እሱን ለመጉዳቱ ግን … የበቁ ናቸው የነቁ!!”

“በናንተ የክፋት ስራ … አቤት አይሁድ ሲደሰት!

የባላጋራው መታወክ … ሰርግ ነውና ለጠላት

ሹመት አልነበር ምኞቹ … ሃብት አልጠየቀ የሰፋ

ቅልቅል የለው ከናንተ … ገንዘብ ፈልጎ አልተጋፋ።

እስኪ ስለምን ጠልታችሁ … ስለምንስ ታሰረ?

እንዲህ ትገፉት ዘንድስ … ምን ክፋት ነበር የፈጠረ?”

“በምን እንዳሰራችሁት … ያኔ እሳቤያችሁ ሲገለጥ

ሳንነግራችሁ አንቀርም … ነገ ሲተከል ሲራጥ።

ይሄው ሞተ እፎይ በሉ … ይሰማችሁ ደስታ

ያሰኛችሁን ለጥጡ … ያለምንም ይሉኝታ።

ፍቱ እሰሩ እንዳሻችሁ … እግር ዘርጉ በሉ ፈታ

ምንጣፉ ተጠቀለለ … ይሄው ያ ጀግና ተረታ።”

[ታሪኹ ኢብኒል ወርዲ፡ 2/275-276]

=

* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.....Munewor?mibextid=ZbW

* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0....029VaA3X1e5kg7BlsJbo

* ኡማ ላይፍ፦ https://ummalife.com/IbnuMunewor

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ - ረሒመሁላህ - ሲሞቱ ጊዜ ታስረውበት በነበረው ወህኒ ቤት ውስጥ በሳቸው የእጅ ፅሑፍ የተፃፉ እንዲህ የሚሉ አሳዛኝ የግጥም ስንኞች ተገኝተዋል። በግርድፉ ተርጉሜዋለሁ።

“እኔ ነኝ ደካማው ከጃይ … ከሰማያቱ ባለቤት

በሁለመናዬ ስንኩል … እኔው ነኝ ምስኪኑ ማለት።

እኔው ነኝ የራሴ ጠላት … ነፍሴ እራሷ ነች በዳዬ

ኸይር ሁሉ የሚገኘው … ከሱ ብቻ ነው ጌታዬ።

ለራሴ እንኳን የማልሆን … የማላቀርብ አንዳች ፋይዳ

መከላከል አይሆንልኝ … በክፉ እንዳልጎዳ።

ሌላ ፈጣሪም የለኝ … ከሱ ውጭ ‘ሚያስተናብር

አማላጅም አይኖረኝ … ወደ ጌታ የሚያሻግር

በሱ ፈቃድ ቢሆን እንጂ … በፈጠረኝ በረሕማኑ

የሰማያቱ ባለቤት … እንዳወሳው በቁርኣኑ

ቅንጣት የሌለኝ ከንቱ … ያለ ጌታዬ ይሁንታ

አንዳች ተጋሪም የለው … በየትኛውም ሁኔታ

አጋዥ አይፈልግ ደጋፊ … ረዳት አይሻ የኔ ጌታ

ልክ እንደሚያስፈልጋቸው … ለወልዮቹ አይነታ።

ችግር ድህነት አርማዬ … የኔ ቋሚ መገለጫ

መብቃቃቱ የጌታ ነው … የሁልጊዜ ባለብልጫ

አንጋጣጭ ነው ወደ ጌታ … ፍጡር ሲባል ጠቅላላ

ሁሉም ተዋርዶ ይቀርባል … ቢሻው ጠላ ቢሻው ደላ።

ከፈጠረው ጌታ ውጭ … ምኞት ፍላጎት የሚሻ

ቂ^ል፣ በ^ዳይ፣ አረ^መኔ … አጋሪ ነው መጨረሻ።

ይመስገነው ፈጣሪዬ … አለሙን በፀጋው የሞላ

ላለፈውም ለመጪውም … ላደረገልን በመላ።

ከዚያም ሶላቱ ይትረፍረፍ … በምርጡ ነቢያችን ላይ

የፍጡራን ቁንጮ አይነታ … የሁሉ ላይ የላይ በላይ።” [አልዑቁድ፡ 391]

=

* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor

* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.....Munewor?mibextid=ZbW

* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0....029VaA3X1e5kg7BlsJbo

* ኡማ ላይፍ፦ https://ummalife.com/IbnuMunewor

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

3 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አዲስ የተጀመረ ብልሹ ዐቂዳህና መንሃጅ መጥቷል አሉ። መጥተው የነበሩት እነ አሕባሽ ወደመጡበት ሳይመለሱ ሌላ ደግሞ እየተሳበልን ነው።

ይህ አዲሱ ዐቂዳ እነ ዶ/ር ጀይላንና ሌሎችም ታዋቂ ኡስታዞች በሚገኙበት አየር ጤና አንሷር መስጂድ መሰበኩ ደግሞ አሳሳቢ ነው። በርግጥ ዶ/ር ጀይላን ከደርሱ በኋላ ረድ ሰጥተዋል የሚል መረጃ ሰምቻለሁ።

የሚያሳዝነው አንዳንድ የአየር ጤና ወንድሞች አዲሱን አካሄድ «ትክክል ነው!» ብለው ለመከራከር እየሞከሩ ነው አሉ።

ለማንኛውም ስለዚህ መንገድ ቀደም ብሎ ሰበካው ያገኘው ኡስታዝ አቡበከር ሑሴን በቪድ የሚያውቀውን ያክል በሚገባ አብራርቷልና የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ ስላለው ከራሱ አንደበት አዳምጡት።

በመስጅድ፣ መድረሳና ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ ሽፋን የሚመጡ አዳዲስ አካሄዶች (በተለይም ይህ አብርሃማዊ ኃይማኖቶች) የሚለው እሳቤ ተያይዘው እንዳይመጡ መጠንቀቅ ያሻል የምንለው ለዚህ ነው።

ለገንዘብ ተብሎ ትክክለኛ ዐቂዳህ አይሸጥም። ከትክክለኛ ዐቂዳችን ጋር ድህነታችን ይበልጥብናል

ይህ አዲሱ ዐቂዳህ ግን የምን አራቱ አኢማዎች፣ የምን መዝሃብ፣ የምን ሰለፎች… ሁሉንም የሚያንኮታኩት አደገኛ አካሄድ ስለሆነ ሳይስፋፋ በአስቸኳይ ከሃገር መውጣት አለበት።

ከዘገየ ግን እያንዳንዱ የጥመት ተጣሪ ተከታይ አያጣም። እንኳን እነዚህ አስመሳዮቹ በፍቅርሲዚም የሚያምን ከንቱ መች ይጠፋል!

||

t.me/MuradTadesse

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

{ وَلَا تَحۡسَبَنَّ ٱللَّهَ غَـٰفِلًا عَمَّا یَعۡمَلُ ٱلظَّـٰلِمُونَۚ إِنَّمَا یُؤَخِّرُهُمۡ لِیَوۡمࣲ تَشۡخَصُ فِیهِ ٱلۡأَبۡصَـٰرُ }

Send as a message
Share on my page
Share in the group