UMMA TOKEN INVESTOR

About me

Free Palestinian 🙏🙏🙏

Translation is not possible.

ሰዉዲ አረቢያ ግን በምን ሚናዋ ነው የአረቡ ዓለም መሪ የምትባለው..? ዛሬ ታላለቅ የምዕራባውያን ከተሞች ውስጥ በርካታ ሰዎች ሰልፍ በመውጣት ጋዛ ላይ የታወጀውን እልቂት ተቃውመዋል፣ አውግዘዋል።

ሰውዲ ግን ሌላ ዓለም ውስጥ ነች። ሪያድ ሰርግና ምላሽ ያላት ይመስላል። ፌሽታ ላይ ናት። በመዝናኛው እንዱስትሪ በኩል ያሉ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ተሰብስቦ ሪያድ ከትመዋል። የዓለም ዝነኛ ስፖርተኞችም ሪያድ ውስጥ ተሰብስበዋል። አቅራቢያዋ ቀይ ደም ይፈሳል። ሪያድ ግን ቀይ ምንጣፍ አንጥፋ ከዝነኞች ጋር ትደንሳለች። አሁን የሪያድ አይን ጋዛ ላይ አይደለም። አይኖቿ የቦክስ ሪንግ ላይ ናቸው። ቡጢኞቹ Tyson Fury እና Francis Ngannou ሚሊየን ዶላሮችን ሰብስቦ ለመሄድ ሪንግ ውስጥ ከሪያድ ጋር ዳንስ ላይ ናቸው።

ትላንት በሰዉዲ ፕሮ ሊግ Neymar'ን ያስፈረመወ Al Hilal ጨዋታውን ሲያደርግ ሰዉዲ ድርብ ደስታ ውስጥ ያለች ይመስል ነበር። ስለ ጋዛ ሀዘን የለም።መፈክር የለም። ባንዲራ የለም። ሕመማቸው አልተሰማም። የሴልቲክ ደጋፊዎች ስለ ጋዛ ህፃናት ሲያለቅሱ አይተናል..በሊቨርፑል ስታዲየም በርካታ ባንዲራ እና የአጋርነት መፈክር ተመልክተናል። የ'ኡማው' መሪ የምትባለው ሰዉዲ አረቢያ ግን ስለ ጋዛ ሳይሆን በእግር ወለምታ ከሜዳ ስለራቀው Neymar Jr. ስታለቅስ ታየች። ያቺ ሀገር ግን ትልቅ ሰው የላትም ይሁን🤔

image
image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ከሐማስ ጥቃት በኃላ አንቶኒ ብሊንከን ጭሱ ሳይሰክን ቴል አቪቭ ተገኝቶ በሲቃ ታጅቦ ለእስራኤል አጋርነቱን ገልፀዋል። ፕረዚዳንት ጆ ባይደንም አረቦቹ ጋር የሚፈጥረውን ቅሬታ ወደ ጎን ብሎ ያውም 500 ሰው ከፈጀ የሆስፒታል ጥቃት መግስት ሪስክ ወስዶ ቴል አቪቭ ሄዶ አይዟችሁ ግፉበት ብሎ ሚሳይል ተሸካሚ የጦር መርከቦችን ለግሰዋል። የጀርመኑ ቻንሲለር ኦላፍ ሾልዝ'ም የፕረዝዳንት ባይደንን ዱካ ተከትሎ ቴል አቪቭ በመሄድ ሻሎም ለእስራኤል እልቂት ለጋዛ ብሎ ወደ በርሊን ተመልሰዋል። የብሪታንያው ሪሺ ሱናክ'ም ለቅሶ እንደሚደርስ ሰዉ ተጣድፎ ቴል አቪቭ በመሄድ የናንተ መጠቃት የኛም መጠቃት ነው ብለዋል። የፈረንሳዩ ኢማኑኤል ማክሮንም ለየትኛውም ድጋፍ አለንላችሁ ለማለት ተራውን ጠብቆ ቴል አቪቭ ደርሶ ወደ ፓሪስ ተመልሰዋል። በእስራኤል ውስጠ ፖለቲካ ሆድና ጀርባ ሆኖ የኖሩት ጀነራል ቤኒ ጋንዝ እና ጠ/ሚ/ር ቤንያሃሚን ኔታናሁ የአንድነት መንግስት መስርቶ ጦርነቱን በጋራ እየመሩ ነው።

አረቦቹስ...? ላለመስማማት ተስማምተዋል። አንዱም የአረብ መሪ ወደ ራማላህ ሂጄ እሳት የሚወርድባቸውን ፍልጤማዊያንን ላፅናና ያለ የለም። እንዳውም አረብ ያልሆኑት ኢራን እና ቱርኪዬ ያሳዩት አጋርነት ከፍ ያለ ነው። ለፍልስጤማውያን ህልውና የአረቦች አጋርነት እጅግ ወሳኝ ነው። ካታር በሕዝብ ግንኙነት በኩል እያተወጣች ያለውን ሚና ሌሎቹም ቢጋሩ ትልቅ ተፅዕኖ ማሳደር ይችሉ ነበር። ለአንድ ቀን ተባብሮ ነዳጅ ወደ ውጭ መላኩን ቢያቆሙስ አሊያም ቢቀንሱስ..? የዓለም ንግድ በሙሉ ቀጥ ይላል።በዚህም የግድ ወደ ድርድር ይገባል። በየ ሀገሮቻቸው ያሉትን የአሜሪካ አምባሳደሮችን ቢያባሩስ..? ብቻ በብዙ መንገድ ምዕራባውያንን ለድርድር ማስገደድ ይችሉ ነበር። ሕዝቡስ..? በመሉ ተነስቶ በየሀገሩ ያለውን ኤምባሲ ቢወር..? አሜሪካዊያን ዜጎች ለፍልስጤማውያን የጮኹትን ያህል የሰዉዲ አረቢያ ሕዝብ ስለ ፍልስጤም አልጮኸም።

የሆነ ሆኖ አረቦቹ በተናጠል ወደ እርምጃ ለመግባት ከሞከሩ ወዲያው ይመታሉ። ሌላው ቀርቶ Hezbollah ወደ ጦርነቱ ከገባ ሊባኖስ ሙሉ በሙሉ ትወድማለች። ሁቲ'ም የኢራንን ትዕዛዝ ተቀብሎ ብቻውን ከሄደ በእርስ በርስ ጦርነት የፈራረሰችው Yemen ላይ የመጨረሻው ሚስማር ይመታል። አረብ ያልሆነችው እና የተፈራችው ኢራን ወደ ጦርነቱ እንዳትገባ አሜሪካኖቹ በቻይና በኩል መልዕክት ልኮባታል። ሺ ጂንፒንግ የአያቶላውን ረጅም እጅ ያዝ ተብለዋል። ቴህራን እምቢ ብላ ከገባች ግን ሁሉም በእሳቱ ይለበለባል። የቴህራን ውለታ ያለባቸው Hezbollah, Houthi እና የሶሪያው በሻር አላሳድ መንግስት ሞትሽ ሞቴ ብሎ ኢራንን መከተላቸው አይቀርም። ራሺያም በተቸገረችበት ሰዓት በአደገኛ droneዎቿ የደረሰችለት ኢራን ናት። ቢሆንም ቭላድሜር ፑቲን እና ኤርዶጋን ከስሜት ይልቅ ስሌትን የሚያስቀድሙ በመሆናቸው ዘሎ እሳት ውስጥ ይገባሉ ተብሎ አይጠበቅም። አረብ ግን ቱ😑

TW

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🚩 የዓለማችን ዋና ዋና ሚዲያዎች በንፍቅና በሽታ የተዋጡና ጽዮናዊ አጀንዳ ብቻ የሚያስፈጽሙ ቢሆኑም… ሕዝብ ደግሞ መደበኛ ሚዲያውን እየሸሸ በማኅበራዊ ሚዲያ አጀንዳውን ሴት በማድረግ መታገሉ አይቀርም…

.

ምንም ያክል ሊሸፋፍኑት እና ሊያስቀይሱት ቢጥሩም ችግሩ የግፈኛዋ #እስራኤል አፓርታይዳዊ ቅኝ ግዛት መሆኑን የዓለም ሕዝብ እየተረዳ የመጣበት ወቅት ላይ እንገኛለን… ኢንሻአላህ የሙስሊሙ ዓለም 3ኛ ቅዱስ ሥፍራ #ፍልስጤም ነፃ ትወጣለች!

.

🇵🇸 #freepalestine #gazagenocide #apartheid

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ትላንት ማታ በተመድ አስቸኳይ ስብስባ ተካሄዶ ነበር! ስብሰባው በጋዛ አስቸኳይ ሰብአዊ ቶክስ መቆም ላይ ነበር!።በዚህም መሰረት 120 ሀገራት ኤርትራ ጨምሮ 🇪🇷🇪🇷🇪🇷 ውሳኔ ሀሰቡን ስደግፉ፣14 ሀገራት አሜርካን 🇺🇸 ጨምሮ ስቃወሙ፤ኢትዮጵያን 🇪🇹 ጨምሮ 45 ሀገራት ውሰኔ ሀሰቡ ላይ ድምፅ ተአቅቦ አድርጓል።በዚህም ውሰኔ መሰረት አስቸኳይ ሰብአዊ ቶክስ አቁም ሀሰብ በአብላጫ ድምፅ መፅደቅ ችለዋል 🙏።ኤርትራ በተደጋጋሚ ከPalestines ሀገር መሆን መብት እንደምትደግፍ እየገለፀች ትገኛለች 🙏🙏

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የዓለም ህዝብ ግን አይገርምም⁉️

=======================

(ዓለም በዚህ ዘመን አይታው የማታውቀው የጦር ወን'ጀልና የዘር ጭፍ'ጨፋ በጘዝ'ዛ)

||

✍ 365 km² ስፋት ባላት አነስተኛ ከተማ ውስጥ 2.3+ ሚሊዮን ዜጎች ተጠጋግተው ይኖሩባታል። በዚህች densely populated በሆነች ከተማ ላይ ለተከታታይ 3 ሳምንታት ያላባራ ከ12 ሺህ ቶን በላይ ቦም'ብ ሲዘንብ፤ በዚህም ሳቢያ፦

1) በትንሹ 7,028 የሚሆኑ ፈለስጢናዊ ሙስሊሞች ሲገ'ደሉ፣

2) ከ70% በላይ የሚሆኑት ህፃናትና ሴቶች ሲሆኑ (2,913 ህፃናትና 1,709 ሴቶች)፣

3) 18,482 የሚሆኑት ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ሲዳረጉ፣

4) ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 481 የሚሆኑት ሲገ'ደሉ (ከመካከላቸው 209 የሚሆኑት ህፃናት ናቸው።)፣

5) ከ1,650 በላይ የሚሆኑት ጀናዛቸው እንኳ ሳይገኝ እስካሁን ድረስ በቦ'ምብ በፈራረሱት ህንፃዎች ስር ሲሆኑ (ከመካከላቸው 940 ህፃናት አሉበት።)፣

6) 731 የሚሆኑ ፈለስጢናዊ ሙሉ ቤተሰቦች ሲገ'ደሉ፣

⑦) 101 የጤና ባለሙያዎች ሲገ'ደሉና 100 የሚሆኑት ሲቆስሉ፣

⑧) 12 ሆስፒታሎችና 32 የጤና ማዕከላት በነዳጅ እጥረትና በቦምብ ጥቃት ከአገልግሎት ውጭ ሲሆኑ፣

9) በኢንኩቤተር ውስጥ የሚገኙ ከ130 በላይ የሚሆኑ ህፃናት ያሉበት ሆስፒታል ባጋጠመው በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ነፍሳቸው በእንጥልጥል ላይ ሲገኝ፣

⑩) ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ንጹሐን ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፖች፣ በት/ቤቶች፣ በሆስፒታል ግቢዎች፣ በመስጂዶችና ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው ሳለ በዛው ባሉበት ጥቃቱ ሲያገኛቸው… (ከሰው ነፍስ አይበልጥምና ወደ አመድነት ስለተቀየሩት ውብ ህንፃዎችና መሠረተ ልማቶችማ አውርተን አንዘልቀውም።)

የሰለጠነ ተብዬው ዓለም አሁንም «ጦርነቱ ይቁም!» ከማለት ይልቅ «እስራኤል ራሷን የመከላከል መብት አላት፣ ሐማስ መጥፋቱን ማረጋገጥ አለባት፣ ከጎንሽ ነን፣ ሐማስ ሽብ'ርተኛ ነው፣ በሐማስ ጥቃት ለሞቱት እስራኤላዊያን አዝነናል!…» እያሉ ነው።

ትንሽ አሻሻልን የሚሉት ደግሞ ጦርነቱ መቆም የለበትም፤ ግን የተወሰነች እርዳታ ይግባላቸው ይላሉ።

እስካሁን በጋዛ መብራት የለ፣ ውሃ የለ፣ ምግብ የለ፣ ነዳጅ የለ…። በዚህ የተነሳ የቆሰሉትና መደበኛ ህመም የሚታመሙትም መታከም አልቻሉም።

ዙሪያውን በከበባ ስለሆነ ለጠናበት ታማሚ የውጭ ሕክምና እንዲያገኝ ማድረግ አልተቻለም።

እስራኤል ከላይ በአየር ከምታዘንበው የቦምብ ዝናብ ባሻገር ከምግብና ውሃ እንዲሁም ከሕክምና ከልክላ በጅምላ ጭፍ'ጨፋ የጦር ወን'ጀልና የዘር ማፅ'ዳት ወንጀል በመፈጸም ላይ ትገኛለች። ይህ ሁሉ የሚሆነው ዓለም እያዬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ተመድ ተብዬውም ሆነ የትኛውም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነኝ የሚል ተቋም ሁሉ የውሃ ሽታ ሆኗል። የነርሱ ህግ እነርሱን ለማዳን እንጂ ለሌላው አይሠራም። እነርሱ ዘንድ የሙስሊም፣ የዓረብና የአፍሪካዊ ሞት ከውሻ'ቸው ሞት በታች ነው።

ግን ነፍስ ሁሉ እኩል ናትና የእጃቸውን አንድ ቀን ማግኘት አይችሉም። ነገ ላይ በሌላ የነርሱ አካል ላይ ጥቃት ሲፈጸም በሚዲያቸውም ሆነ ባልተጻፈው ህጋቸው ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ሲለፍፉ እናገኛቸዋለን።

አላህ ውርደታቸውን ያቅርበው፤ ለተበዳዮች ነስሩን ያፍጥነው።

አላህ የአሸናፊዎች ሁሉ አሸናፊ የሆነ ጥበበኛና ታጋሽ ጌታ ነው። አንድ ቀን አይርላቸውም።

||

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group