UMMA TOKEN INVESTOR

About me

Islam is the only solution ☪️

Translation is not possible.

በአላህ ስም

*🍃 4ቱን እዝነትህን አትንፈጋቸው*

① ሚስትህን

② ልጆችህን

③ ቤተሰብህንና

④ ጓደኞችህን

*🍃 4 ነገሮችን ቀንስ*

① እንቅልፍን

② ምግብን

③ መሰላቸትንና

④ ንግግርን

*🍃 4ቱ ላይ አትጨክንባቸው*

① የቲም ላይ

② ሚስኪን ላይ

③ ድሃ ላይና

④ ህመምተኛ ላይ

*🍃 4 ሰዎችን ቅረባቸው*

① ሙኽሊስ የሆነ ሰው

② ቃሉን ጠባቂ

③ አዛኝንና

④ ታማኝን

*🍃 4 ሰዎችን ራቃቸው*

① ጃሂልን

② ተከራካሪን

③ ቂልንና

④ ባዶን

*🍃 4 ሰዎችን ጓደኛ* አታድርጋቸው

① ውሸታምን

② ሌባን

③ ምቀኛንና

④ ራስወዳድን

*🍃 4 ነገሮችን አትቁረጣቸው*

① ሰላት

② ቁርአን

③ ዚክርንና

④ ዝምድናን

*🍃 በ4ቱ ተዋብባቸው*

① በትእግስት

② በቻይነት

③ በእውቀትና

④ በቅንነት

*🍃 ከ4 ነገሮች በአላህ* ተጠበቅ

① ከትካዜ

② ከሀዘን

③ ከድብርትና

④ ከስስት

*2, ፊትህ እንዲበራ ትፈልጋለህ ?*

®= የሌሊት ሶላት አደራ ፡፡

3, ጤና ትፈልጋለህ ?

_®= ፆምን አጥብቀህ ያዝ ፡፡_

_4, ከጭንቅ ለመዉጣት ትፈልጋለህ ?_

_እሥቲግፋርን እንዳትለቅ ፡፡_

_5, ትካዜን ማሥወገድ ትፈልጋለህ ፡፡_

_ዱአን ሙጭጭ አድርገህ ያዝ ፡፡_

_6, የህይወትን አድካሚ ችግሮች ለማሥወገድ ትፈልጋለህ ?_

_®= "ላሀወላ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ " ማለት አብዛ ፡፡_

_7, በረካ ትፈልጋለህ ?_

_®= በነብዩ ሙሃመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሠለም ) ላይ ሠለዋት አዉርድ ፡፡_

_8, ዘና ማለት ትፈልጋለህ_ ?

_®= ቁርአንን ረጋ ብለህ በማሥተንተን አንብብ ፡፡

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የባህሪ ለውጥ ምክንያቶች

~

አንዳንዴ ለዘመናት በመልካምነት የምናውቃቸው ሰዎች የማናውቃቸው እስከሚመስለን ድረስ ባህሪያቸው ተቀይሮ ለመሸከም የሚከብዱ ይሆናሉ። ምክንያቱ ምን ይሆን? የችግሮቹን መንስኤዎች ማወቅ ለማስታመም፣ ለማለፍ፣ ለመረዳት፣ ... ያግዘናል። የሰዎችን ባህሪ ከሚቀይሩ ነገሮች ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው።

1- ስልጣን፦

ስልጣንና ኃላፊነት ሲያገኙ የሚቀየሩ ብዙ ሰዎች አሉ። የሚያውቁትን እንደማያውቁት ይሆናሉ። ንቀትን ንቃት ያደርጋሉ። ውለታ ይረሳሉ።

2- ስልጣን ማጣት፦

ከስልጣንና ኃላፊነት ሲነሱ በብስጭት፣ በቁጭት እየተብከነከኑ ለሩቁ ቀርቶ ለቅርብ ሰዋቸው ጭምር ባህሪያቸው የሚፈትኑ ይኖራሉ።

3- ሃብት፦

ትሁትና ደግ የነበሩ ሰዎች ሃብት ካገኙ በኋላ ትእቢት፣ ንቀትና ኩራት የሚባሉ ነውሮችን ጌጥ የሚያደረጉ የዋሆች አሉ።

4- ድህነት፦

አግኝቶ ማጣት ትልቅ ህመም አለው። ድህነት ሲዳብሳቸው መልካም ባህሪያቸው ከገንዘባቸው ጋር ጥሏቸው የሚጠፋ ሰዎች አሉ። መቼም አመላችን እንደ መልካችን ብዙ አይነት ነው።

5- ሱስ፦

በሱስ በመጎዳታቸው የተነሳ ከጊዜ ጊዜ ትእግስት እንደ ቁምጣ እያጠራቸው የሚሄድ፣ ይሉኝታ የማያውቁ፣ "ሰው ምን ይለኛል?" የማይገዳቸው ሰዎች ቁጥራቸው ከብዙም የበዛ ነው።

6- ሃሳብ፦

የሰው ልጅ በህይወቱ ለተለያዩ ሃሳቦች መጋለጡ የሚጠበቅ ነው። የሃሳብ መደራረብ፣ የአእምሮ መወጠር ደግሞ የሰው ባህሪ ላይ ግልፅ ተፅእኖ ያሳድርበታል።

7- ህመም፦

ህመም ባህሪን ይቀይራል። ያነጫንጫል። ከሰው ቀርቶ ከእንስሳ፣ ከግድግዳ ጋር ሁሉ ያጋጫል።

8- እርጅና፦

እርጅና እንደ ልጅ ያደርጋል። እንዲያውም ሊብስ ይችላል። ልጅን ተቆጥተህ ታስደነግጠዋለህ። ከእርጅና ጋር የሚመጣ ክፉ ባህሪ ግን ለገላጋይ አይመችም። እርጅና ላይ ሌሎች ገፊ ችግሮች ሲደረቡበት ደግሞ በቡሃ ላይ ቆረቆር ይሆናል።

ምንጭ፦ አብዛኛው ሃሳብ ከሸይኽ ዐብደላህ አልፈውዛን (ሚንሐቱል ዐላም፡ 10/295 - 296) የተወሰደ ነው።

Ibnu Munewor

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የንጉሥ አስሃማ ቢን አብጀር ነጃሺ መስጂድና ኢስላማዊ የምርምር ማዕከል ከ 10ሺ በላይ ምዕመናን እንደሚያስተናግድ ተገለጸ።

••••••••••••••••••••••••••••••

Mujib Amino

የንጉሥ አስሃማ ቢን አብጀር-ነጃሺ መስጂድና ኢስላማዊ የምርምር ማዕከል ዐቢይ ኮሚቴ ከፌደራል መጅሊስ አመራሮችና ስራ አስፈጻሚ፣ ከባለሙያዎች ፣ ከየክልሎች የመጅሊስ ተወካዮችና ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በአዲስ አበባ ኤሊያና አዳራሽ በቀጣይ ግንባታዎችና አቅጣጫዎች ዙሪያ ምክክር አድርጓል።

ሊሰራ በታቀድዉና በቅርቡ በሚጀመርዉ የንጉሦ ነጃሺ መስጂድ የግንባታ ዲዛይንና ይካተታሉ ከተባሉ ፕሮጀክቶች ዙሪያ ገለጻ ተደርጎ ከታደሚዎች መሻሻል ስለሚገባቸዉ ጉዳዮች ላይ መክሯል።

ኡስታዝ አቡበክር አህመድ Ustaz Abubeker Ahmed/ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ.የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤ ፕሬዝደንት ልዩ አማካሪና የግንባታዉ ብሄራዊ ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ የንጉሥ ነጃሺ ግንባታ ኢስላማዊነቱንና የማህበረሰቡ መገለጫነቱን በጠበቀ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን አንድነት በሚያሳይ መልኩ እንደሚገነባ አበስረዋል።

የንጉሥ አስሃማ ቢን አብጀር ነጃሺ መስጂድና ኢስላማዊ የምርምር ማዕከል 3 ዋና ዋና የግንባታ መዋቅር ያለዉ ሲሆን አንደኛዉና ዋነኘዉ የመስጂድ ስፋራ ነዉ። ይህ የመስጂድ ስፍራ ከ 12-18 ሺ ምዕመናን እንደሚያስተናግድ እቅድ ተይዞ በሀገራችን ትልቁን ስፍራ እንደሚይዝ ይገመታል። ከዚሁ የመስጂድ ስፍራ በታችም እስከ 1500 ተሽከርካሪዎችን የመያዝ አቅም ያለዉ ፓርኪንግም ይሰራል ተብሏል።

በፕሮጀክቶቹ ላይ ከተካተቱት ዉስጥ የማህበረሰብ አቀፍ ማዕከል ሲኖር የባህልና ኢግዚብሽን ፣ሙዚየምና ላይብረሪ ፣የአካል ብቃትና ጤና ማዕከል፣ ለወጣቶችና ለልጆች (ለህፃናት) አገልግሎት የሚሰጡት ማዕከላትን ያካትታል ተብሏል።

ሶስተኛዉ የፕሮጀክቱ አካል የሆነዉ የንግድ ማዕከል ሲሆን ንግድና የችርቻሮ ሱቆች ይኖሩታል ተብሎ ይጠበቃል።

የኮሚቴዉ ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ከባለድርሻ አካላት የቀረቡትን ጥያቄና አስተያየት በመቀበል ግብዓት ወስደዋል።

የንጉሥ አስሃማ ቢን አብጀር ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ በቅርቡ ወደስራ ይገባል።

ኢንሻ አሏህ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አንድ ታዋቂ የቻይና አፕሊኬሽን እስራኤልን ከአለም ካርታ ሰርዟታል።

እስራኤልን ከአለም ካርታ የሰረዘው ኦንላይን ካርታ በታዋቂዎቹ በባይዱና በአሊባባ እየታየ ነው ‼️

ኢንሻላህ በገሀዱ አለምም ተዋርደው ይጠፋሉ።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group