ሰዉዲ አረቢያ ግን በምን ሚናዋ ነው የአረቡ ዓለም መሪ የምትባለው..? ዛሬ ታላለቅ የምዕራባውያን ከተሞች ውስጥ በርካታ ሰዎች ሰልፍ በመውጣት ጋዛ ላይ የታወጀውን እልቂት ተቃውመዋል፣ አውግዘዋል።
ሰውዲ ግን ሌላ ዓለም ውስጥ ነች። ሪያድ ሰርግና ምላሽ ያላት ይመስላል። ፌሽታ ላይ ናት። በመዝናኛው እንዱስትሪ በኩል ያሉ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ተሰብስቦ ሪያድ ከትመዋል። የዓለም ዝነኛ ስፖርተኞችም ሪያድ ውስጥ ተሰብስበዋል። አቅራቢያዋ ቀይ ደም ይፈሳል። ሪያድ ግን ቀይ ምንጣፍ አንጥፋ ከዝነኞች ጋር ትደንሳለች። አሁን የሪያድ አይን ጋዛ ላይ አይደለም። አይኖቿ የቦክስ ሪንግ ላይ ናቸው። ቡጢኞቹ Tyson Fury እና Francis Ngannou ሚሊየን ዶላሮችን ሰብስቦ ለመሄድ ሪንግ ውስጥ ከሪያድ ጋር ዳንስ ላይ ናቸው።
ትላንት በሰዉዲ ፕሮ ሊግ Neymar'ን ያስፈረመወ Al Hilal ጨዋታውን ሲያደርግ ሰዉዲ ድርብ ደስታ ውስጥ ያለች ይመስል ነበር። ስለ ጋዛ ሀዘን የለም።መፈክር የለም። ባንዲራ የለም። ሕመማቸው አልተሰማም። የሴልቲክ ደጋፊዎች ስለ ጋዛ ህፃናት ሲያለቅሱ አይተናል..በሊቨርፑል ስታዲየም በርካታ ባንዲራ እና የአጋርነት መፈክር ተመልክተናል። የ'ኡማው' መሪ የምትባለው ሰዉዲ አረቢያ ግን ስለ ጋዛ ሳይሆን በእግር ወለምታ ከሜዳ ስለራቀው Neymar Jr. ስታለቅስ ታየች። ያቺ ሀገር ግን ትልቅ ሰው የላትም ይሁን🤔