ከሐማስ ጥቃት በኃላ አንቶኒ ብሊንከን ጭሱ ሳይሰክን ቴል አቪቭ ተገኝቶ በሲቃ ታጅቦ ለእስራኤል አጋርነቱን ገልፀዋል። ፕረዚዳንት ጆ ባይደንም አረቦቹ ጋር የሚፈጥረውን ቅሬታ ወደ ጎን ብሎ ያውም 500 ሰው ከፈጀ የሆስፒታል ጥቃት መግስት ሪስክ ወስዶ ቴል አቪቭ ሄዶ አይዟችሁ ግፉበት ብሎ ሚሳይል ተሸካሚ የጦር መርከቦችን ለግሰዋል። የጀርመኑ ቻንሲለር ኦላፍ ሾልዝ'ም የፕረዝዳንት ባይደንን ዱካ ተከትሎ ቴል አቪቭ በመሄድ ሻሎም ለእስራኤል እልቂት ለጋዛ ብሎ ወደ በርሊን ተመልሰዋል። የብሪታንያው ሪሺ ሱናክ'ም ለቅሶ እንደሚደርስ ሰዉ ተጣድፎ ቴል አቪቭ በመሄድ የናንተ መጠቃት የኛም መጠቃት ነው ብለዋል። የፈረንሳዩ ኢማኑኤል ማክሮንም ለየትኛውም ድጋፍ አለንላችሁ ለማለት ተራውን ጠብቆ ቴል አቪቭ ደርሶ ወደ ፓሪስ ተመልሰዋል። በእስራኤል ውስጠ ፖለቲካ ሆድና ጀርባ ሆኖ የኖሩት ጀነራል ቤኒ ጋንዝ እና ጠ/ሚ/ር ቤንያሃሚን ኔታናሁ የአንድነት መንግስት መስርቶ ጦርነቱን በጋራ እየመሩ ነው።
አረቦቹስ...? ላለመስማማት ተስማምተዋል። አንዱም የአረብ መሪ ወደ ራማላህ ሂጄ እሳት የሚወርድባቸውን ፍልጤማዊያንን ላፅናና ያለ የለም። እንዳውም አረብ ያልሆኑት ኢራን እና ቱርኪዬ ያሳዩት አጋርነት ከፍ ያለ ነው። ለፍልስጤማውያን ህልውና የአረቦች አጋርነት እጅግ ወሳኝ ነው። ካታር በሕዝብ ግንኙነት በኩል እያተወጣች ያለውን ሚና ሌሎቹም ቢጋሩ ትልቅ ተፅዕኖ ማሳደር ይችሉ ነበር። ለአንድ ቀን ተባብሮ ነዳጅ ወደ ውጭ መላኩን ቢያቆሙስ አሊያም ቢቀንሱስ..? የዓለም ንግድ በሙሉ ቀጥ ይላል።በዚህም የግድ ወደ ድርድር ይገባል። በየ ሀገሮቻቸው ያሉትን የአሜሪካ አምባሳደሮችን ቢያባሩስ..? ብቻ በብዙ መንገድ ምዕራባውያንን ለድርድር ማስገደድ ይችሉ ነበር። ሕዝቡስ..? በመሉ ተነስቶ በየሀገሩ ያለውን ኤምባሲ ቢወር..? አሜሪካዊያን ዜጎች ለፍልስጤማውያን የጮኹትን ያህል የሰዉዲ አረቢያ ሕዝብ ስለ ፍልስጤም አልጮኸም።
የሆነ ሆኖ አረቦቹ በተናጠል ወደ እርምጃ ለመግባት ከሞከሩ ወዲያው ይመታሉ። ሌላው ቀርቶ Hezbollah ወደ ጦርነቱ ከገባ ሊባኖስ ሙሉ በሙሉ ትወድማለች። ሁቲ'ም የኢራንን ትዕዛዝ ተቀብሎ ብቻውን ከሄደ በእርስ በርስ ጦርነት የፈራረሰችው Yemen ላይ የመጨረሻው ሚስማር ይመታል። አረብ ያልሆነችው እና የተፈራችው ኢራን ወደ ጦርነቱ እንዳትገባ አሜሪካኖቹ በቻይና በኩል መልዕክት ልኮባታል። ሺ ጂንፒንግ የአያቶላውን ረጅም እጅ ያዝ ተብለዋል። ቴህራን እምቢ ብላ ከገባች ግን ሁሉም በእሳቱ ይለበለባል። የቴህራን ውለታ ያለባቸው Hezbollah, Houthi እና የሶሪያው በሻር አላሳድ መንግስት ሞትሽ ሞቴ ብሎ ኢራንን መከተላቸው አይቀርም። ራሺያም በተቸገረችበት ሰዓት በአደገኛ droneዎቿ የደረሰችለት ኢራን ናት። ቢሆንም ቭላድሜር ፑቲን እና ኤርዶጋን ከስሜት ይልቅ ስሌትን የሚያስቀድሙ በመሆናቸው ዘሎ እሳት ውስጥ ይገባሉ ተብሎ አይጠበቅም። አረብ ግን ቱ😑
TW