በዋሻው ውስጥ ከአስሀበል ካህፎች ጋር የነበረውን ውሻ ተመልከት። ደጋግ ለሆኑ የአላህ ባሮች ያለው ፍቅር ከእነሱ ጋር ዋሻ ውስጥ እንዲቆይ አደረገው። በዚህም እስከ ዛሬ በሚነበብ መፅሀፍ ታሪክ ሆኖ እንዲጠቀስ አላህ አድርጎታል። ቁርዐን ላይ ውሻው ሳይሆን "ውሻቸው" ተብሎ ተገልጻዋል። ምክንያቱም ከደጋግ ሰዎች (አስሀቡል ካህፍ) ጋር ያለው ቁርኝት እጅግ የጠበቀ ስለነበረ ነው። ታድያ አላሁ ሱብሀነሁ ወተዐላ የአስሀቡል ካህፍ ውሻ እንዴት እንደሚቀመጥና ከዋሻው የትኛው ስፍራ ላይ ይገኝ እንደነበር ሳይቀር ገልፆልናል።
وَكَلْبُهُم بَاسِطٌ ذِرَاعَيْهِ بِالْوَصِيدِ
" . . .ውሻቸውም ሁለት ክንዶቹን በዋሻው በር ላይ ዘርግቷል፡፡. . . "
ይህ ወዳጅ ውሻ ብቻ ነው። ነገር ግን የሰው ልብ ቢሆንስ ለደጋጎች ይሄን ፍቅር የተሸከመው?
አላህ ሆይ ፍቅርህን ፣ የምትወዳቸውን ሰዎች ፍቅር ለግሰን ፣ ወደ ፍቅርህ እንድንደርስ የሚያደርጉንን ድርጊቶች ሁሉ አስወድደን።
ሱረቱል ካህፍን እንድናነብ ፍቀድልን ፡ በልቡ ላይ ቁርኣንን ባወረድክበት እና በአንደበቱ እንዲነበብ ባደረግከው ነብይ ላይ ሶላትና ሰላምህን አውርድ።
©️