UMMA TOKEN INVESTOR

About me

መኖራችን በኢስላም መሞታችን ለኢስላም ቀለማችን ከኢስላም ።

Followings
0
No followings
Translation is not possible.

ገድቦ ላያንቀሳቅስ

አስሮ ላያስገሰግስ

በኔ አካል ነግሶ

ስቃይ ሊቸር ደርሶ

ክፋቴ ብቻ ገኖ

ጥሩነቴ በኖ....

እስከመቼ ረቢ?

(ባለዕዳው )

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ከፍላፃ ይልቅ ምላስ ልብ ያቆስላል

ከሰይፍ አብሶ ክህደት ያደማል

ልቤ ባይጠገንም ቁስሌ ባይደርቅም

ለመድረቅ ተጣጥሮ መልሶ ቢደማም

ወድቄ አልቀርም አላህ ነው አንሺዮ

ሌላ ዞሬ አልቃኝም እሱ ነው ተስፋዮ

(ባለዕዳው )

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🔐

ፈገግታህስ

ቀሙኝ

ቀሙኝ ? ቀሙህ ወይስ ሰጠሀቸው?

አምኛቸው ነበረ ከዱኝ ረዳታቸው ለመሆን ጥሬ ነበር እርዳታቸውን ስሻ ሸሹኝ ለደስታቸው ተደስቼ ነበር ለሀዘኔ ተደሰቱ

ፈገግታህ ከክህደታቸው ይልቅ ውድ ነው አንተ ወጣት! ጥሩነትህ ከ ክፋታቸው የላቀ ነው ፈገግታህን ለመቀማት የሚችል አቅም የላቸውም ከቀሙህ ባንተ እርዳታ ነው ወጣቱ

እንዴት ያ ሸይኽ በኔ እርዳታ?

አንተ ወጣት እምነትህ ቦታው ከፈጣሪህ ነው እርዳታህ ምንጩ ከ ጌታህ ነው አንተ ወጣት ደስታህ በሰዎች ጫንቃ ላይ ላለመውደቅ እንዲያጣጥር ወስነህ አትስቀለው አንተ ወጣት ተዓደብ

(ባለዕዳው)

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አሉ ........

በጣም እንደምትወዳቸው ያላወካቸው እንደሚያስፈልጉህ ያልተረዳሀቸው ምናልባት ልብህ እነሱን ማስደሰትና ፈገግታቸውን ማየት አላማዋ ያረገችላቸው ሰዎች አሉ።

ከማንም በላይ ያስቡልሀል አትረዳቸውም። የነሱን ህመም ፣ችግር፣ስቃይ፣ሀዘን ችለህ ቆመህ ልታይ ፈፅሞ አትችልም ። ጉልበትህ ይተናል ልብህ ይደማል አይንህ ያነባል ጨጓራህ ይነዳል።

ከገቡበት እስኪወጡ ከተኙበት እስኪነቁ ከሄዱበት ደርሰው እስከሚመለሱ ብቻህን ትቀራለህ ሀሳብህ ልብህ ሁሉም ነገርህ እነሱ ጋር ይቀራል አንተን ተስፋ አሳቅፈው ይንክፋሉ ..

ልብህ እንዲሁም ሰውህ አብረው እስኪመለሱ እያነባህ በተስፋ መጠበቅ በዱዓህ መገደፍ ረቢን መጨቅጨቅ በቃ ህፃን መሆን!

ከጥልቅ ስሜት ጋር የተፃፈ ✍️ የታመሙትን ያሽርላቹ (ግልባጭ ለእህቶችም ነው...)

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

የምትወስደው እርምጃ ትክክል ከሆነ

ለተወሰነ ጊዜ ያሳምምሃና ቀሪው እድሜህን እረፍት ይሰጥሃል የተሳሳት ከሆነ ደግሞ ለተወሰነ ጊዜ ያስደስትህና ቀሪው እድሜህን ያደክምሃል

©️

Send as a message
Share on my page
Share in the group