Edris Ayalew Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Edris Ayalew shared a
Translation is not possible.

አያያዙ ብርቱ ነው !

የተራቀቀ ስልጣኔና ውስብሰብ መሳሪያ ያላቸውን ጉልበተኞች ስታይ " አሁን እነኚህ በምን ይነቀነቃሉ ?! " አትበል

የባርነት ቀንበር ድካምን ፣ የቅኝ ግዛት ግፍን ፣ የአፍሪካውያንን

ደም ፣ የካሪቢያያን እምባ በከንቱ ይቀራል ብለህ አታስብ

ኃያላኑ " ሥልጡኖች " በአፍሪካ ጅረቶች ደም ባፈሰሱ 20 እና 30

ዓመታት ውስጥ ፣ የግፋቸውን ግፍ ለመቅመስ በመካከላቸው

የ 1ኛው ዓለም ጦርነት ተከሰተ ፣ ተጫረሱ ፣ ተፋጁ ።

ኡኡታቸው ቀለጠ ።

ዳግመኛም !

ያለፉት የጥቁር ሙታኖች ጩሃት ሊያስተጋባ ፣ የጥቁር ህፃናት

ሰቆቃ ሊሰማ ፣ የጥቁር ሴቶች እምባ ጠብ ሊል ፣ የእርስ

በእርሳቸው መተራረድ በ 2ኛው ዓለም ጦርነት ቀጠለ ።

ጀሊሉ እንዴት ይቀጣል ብለህ አትጠይቅ ! #አያያዙ_ብርቱ_ነው ። የቆሰቆሱት እሳት እርስ በእርሳቸው ሊያያይዛቸው ቢረፍድ እንጂ አይዘገይም ።

አላህ ሆይ 🤲

በፍልስጤም ጋዛ ረዳት ላጡት ባሮችህ ከለላ ሁናቸው በወራሪዎች ጥቃት ህይወታቸው እየተቀጠፉ ያሉትን ወንድም እና እህቶች ከሸሂዶች መድባቸው

የታላቁ አርሽ ጌታ ሆይ 🤲

ሀይልም ፣ አቅምም ፣ ብልሀትም ካንተ ውጪ ለማንም የለውም :: በጉልበታቸው ተምክተው ንፁሃንን እየጨፈጨፉ ለሚገኙት በዳዮች ኃይልህን አሳያቸው ባንተ መንገድ ላይ እየታገሉ የሚገኙትን ባሮችህን እርዳታህ አይለያቸው

ኢላሂ 🤲

በዚህ ሰዓት ፣ በዚህ ደቂቃ በጋዛ በጭንቅ ላይ ላሉት ባሮችህ ድረስላቸው የጅብሪል ፣ የሚካኤል እና የኢስራፌል ጌታ ሆይ

ወራሪዎች የሙስሊሞችን መሬት ወረው ቤትህ አል አቅሷን እያረከሱት ይገኛሉና ይህን መስጂድህን የምንጠብቅበትን አቅም ስጠን

አሚን 😥🤲

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

    እስልምና የማይዘለቅ ባሕር ነው!!

  እጅህን አንስተህ 🤲ያ…አላህ የፈለስጢን ወንድሞቻችን እርዳቸው🤲 በማለትህ ብቻ……

1ኛ, የጌታህን ትዕዛዝ እየፈፀምክ ነው።

  አላህ እንድትለምነው አዞሃል…

{وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ}

{ጌታችሁም ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና አለ፡፡ እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ጀሀነም በእርግጥ ይገባሉ፡፡}

2ኛ, የጌታህን ቃል ዕውን እያደረክ ነው።

{إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ}

{ምእመናኖች ወንድመማቾች ናቸው።}

3ኛ, ነብዩﷺ በተናገሩት መልኩ ሙእሚን ወንድምህ ከፊል አካልህ እንደሆነ እና የእሱ ህመም እረፍት እንደ ሚነሳህ እያስመሰከርክ ነው።

«مثل المؤمنين في توادهم وتراحمهم وتعاطفهم مثل الجسد إذا اشتكى منه عضو تداعى له سائر الجسد بالسهر والحمى»

«ምእመናኖች በመዋደዳቸው እና በመተዛዘናቸው ምሳሌያቸው እንደ አንድ ሰውነት ነው፤ ከእሱ አንድ አካሉ ከታመመ ሌሎቹ አካሎቹ በትኩሳት እና እንቅልፍ በማጣት ይቸገራሉ።»

4ኛ, የአላህ መልእክተኛﷺ አደራ ተፈፃሚ እያደረክ ነው።

«انصر أخاك ظالمًا أو مظلومًا، فقال رجل: يا رسول الله، أنصره إذا كان مظلومًا، أفرأيت إذا كان ظالمًا كيف أنصره؟ قال: تحجزه أو تمنعه من الظلم فإن ذلك نصره»

«ወንድምህ በዳይም ይሁን ተበዳይ እርዳው አሉ። አንዱ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ተበዳይ ከሆነ እረዳዋለሁ, በዳይ ከሆነ እንዴት ነው ምረዳው?" አላቸው፤ ከበደል ትከለክለዋለህ ይህ ለእሱ እርዳታ ነው አሉት።»

5ኛ, አንተ ብዙ ወንጀሎች የተሸከምክ፣ ዒባዳህ ያነሰ፣ ጥፋትህ የበዛ ሆነህ ሩቅ ፈለስጢን ላሉ ወንድሞችህ ዱዓ ስታደርግ;

  ከወንጀል የፀዱ፣ ምንም ስህተት የማይሰሩ፣ ለጌታቸው ፍፁም ታዛዥ የሆኑ መላኢካዎች ለአንተ ዱዓ ያደርጉልሃል።

  «مَا مِن عبْدٍ مُسْلِمٍ يَدعُو لأَخِيهِ بِظَهرِ الغَيْبِ إِلاَّ قَالَ المَلكُ ولَكَ بمِثْلٍ»

«አንድም ሙስሊም የሆነ ባሪያ ሩቅ ላለ ወንድሙ ዱዓ አያደርግለትም; መላኢካ "ለአንተም እንደዛው" ቢለው እንጂ።»

በሌላ ዘገባ

«دَعْوةُ المرءِ المُسْلِمِ لأَخيهِ بِظَهْرِ الغَيْبِ مُسْتَجَابةٌ، عِنْد رأْسِهِ ملَكٌ مُوكَّلٌ كلَّمَا دَعَا لأَخِيهِ بخيرٍ قَال المَلَكُ المُوكَّلُ بِهِ: آمِينَ، ولَكَ بمِثْلٍ»

«ሙስሊም የሆነ ሰው ሩቅ ላለ ወንድሙ የሚያደርገው ዱዓ ተቀባይነት አለው። አጠገቡ የተመደበ መላኢካ አለ; ለወንድሙ በመልካም ዱዓ ባደረገ ልክ መላኢካው "ኣሚን ለአንተም እንደዛው" ይለዋል።»

   ይህ በቲንሹ ነው። ብናሰፋው የበለጠ ማስፋት እና መዘርዘር ይቻል ነበር። ይህ ሁሉ እንዳለ ሆኖ አንተ ያደረከው ዱዓ አላህ "እሺ" ብሎ ተቀብሎህ የደረሰው በላእ ቢመልሰው እና ወንድሞችህ ሰላም ቢሆኑ ደግሞ የቂያማ ቀን ባደረካት ዱዓ ምክንያት የምታገኘው ክብር አላህ ራሱ ይወቀው።

  አዎን!!

    እስልምና ውስጥ ኪሳራ የለም!!

            🖌የቋንጤው

    https://t.me/hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼ ?????? @hamdquante አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል ?? @hamdquante_bot??
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Edris Ayalew shared a
Translation is not possible.

10ቶቹ ምርጥ ምክሮች

1⃣ ለሶላት ጥሪ (አዛን) ስትሰማ ስራህን እርግፍ አድርገህ በመተው ወደ ሶላት ( መስጅድ) ተቻኮል።

2⃣ ቁርአንን ቅራ ፣ መፅሀፍን አንብብ ፣ ጠቃሚ ድምፆችንም ስማ ፣ አለያም አሏህን አውሳ። ከጊዜህ ቅንጣትን ያለጥቅም አታባክን።

3⃣ ትክክለኛውን የአረብኛ ቋንቋ ለመናገር ሞክር።ይህ ከእስልምና ምልክቶች አንዱ ነው።

4⃣ በምንም ጉዳይ ላይ ደረቅ ክርክር አታብዛ ፣ ጭቅጭቅ ኸየር የለውምና።

5⃣ ሳቅ አታብዛ! ከአሏህ ጋ የተገናኘ ቀልብ የተረጋጋና ደበብተኛ ነው።

6⃣ ቀልድ አታብዛ ። ታጋይ ህዝብ ትግል እንጅ ሌላ አታቅም ።

7⃣ አድማጭህ ከሚያስፈልገው በላይ ድምፅህን ከፍ አታርግ። ምክንያቱም እሱ ድርቀትና ማስቸገር ስለሆነ።

8⃣ ግለሰቦችን ከማነወርና ቡድኖችን ከመተቸት ተቆጠብ። በመልካም እንጅ አትናገር።

9⃣ ካገኘኸው ሰው ጋ ሆን ብለህ ተዋወቅ። የጥሪያችን መሰረት ፍቅርና ትውውቅ ( መሆኑን ተገንዘብ)።

🔟 ያሉብን ግዴታዎች ( ሀላፍትናዎች) ከተሰጡን ጊዚያቶች በእጅጉ ይልቃሉ። በመሆኑም ሌሎችም ጊዚያቸውን እንዲጠቀሙ እርዳ። ስራ ካለህ ደግሞ አጠር አርገህ ተግብር።

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማነው ከላይ ያሉትን ምርጥ ምርጥ ምክሮች ለሌሎች ለላኢላሃ ኢለሏህ አማኞች አስተላልፎ የአጅሩ ተካፋይ የሚሆን

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Edris Ayalew shared a
Translation is not possible.

ተውሂድ ተውሂድ እያላችሁ ዑማውን

አትለያዩት ይሄ ዑማ የሚያስፈልገው አንድነት ነው እያሉ ለሚያምታቱ ሰዎች………

ተውሂድ የተፈጠርንለት አላማ ነው በላቸው!

وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡

እውነት ነው ተውሂድ ከሽርክና ከቢድዓ ባለቤቶች ትለያያለች። አንድነት በተውሂድ ብቻ ነው ከዛ ውጭ ያለ አንድነት ገደል ይግባ አለቀ ደቀቀ።

https://t.me/deawetu_selefiyya_Merssa

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🇵🇸

     "ለምን?" ብለህ እንዳትጠፋ!!

ምንም ጥርጥር የሌለው እውነታ ናቸው

🇵🇸ፈለስጢኖች ምስኪን የአላህ ባሪያ እና ተበዳዮች ናቸው፤

🔥ኢስራኢል እና አምሪካ ሙጅሪም በዳዮች ናቸው፤

🤲በዓለም ዙሪያ ያሉ ሙስሊሞች ቀን ማታ ቆመውና ተደፍተው ለአላህ እየለመኑት አላህ ቸላ አይላቸውም፤

☝️አላህ በደልን ስለ ሚጠየፍ በዳይ ይጠላል; ፍትሃዊ ስለሆነም ለተበዳይ ይረዳል፤

  ይህ ሁሉ ከመሆኑም ጋ አላህ ለሚፈልገው ጥበብ ሲል በዳዮች በዚህ ምድር ላይ ያቆያቸዋል፤ ጊዜ ይሰጣቸዋል።

  ወይ ተመክረው ሊመለሱ፤ አልያም በደላቸው በዝቶ ቅጣታቸው የበለጠ እንዲበረታ።

ይህ ስለ ሆነ;

"አላህ እንዴት ዝም ይላል? ወይስ እምነታችን ትክክል አይደለም ነው?" ብለህ እንዳትጠፋ ተጠንቀቅ።

   {لَا يُسْأَلُ عَمَّا يَفْعَلُ وَهُمْ يُسْأَلُونَ}

  {(አላህ) በሚሰራው ነገር አይጠየቅም፤ (ፉጡሮች) እነርሱ ግን ይጠየቃሉ}

  

Send as a message
Share on my page
Share in the group