UMMA TOKEN INVESTOR

kumel bonge shared a
Translation is not possible.

👒🌸 ሴቶችዬ አይመለከችሁም ። 🌸👒

👥 ወንዶችዬ ነቃ ብላቹ አንብቡት

🌸 #ኢማም አህመድ ኢብን ሀንበል(አላህ ይዘንላቸው )ልጃቸው ሲያገባ የመከሩት ምክር

💡 "ልጄ ሆይ እነዚህን አስር ነገሮች ለባለቤትክ መፈፀም ካልቻልክ በትዳር ህይወትህ ደስተኛ መሆን ስለማትችል ምክሬን ጠበቅ አድርገህ ለመያዝ ሞክር "

🌸 "1⃣_ሴት ልጅ ምቾትን ስለምትፈልግ ያለህን ነገር ሳትሰስት አጋራት።

🌸 2⃣ሴት ፍቅርህን እንድትገልፅላት ትሻለች ።(ባገኘኸው አጋጣሚ) ፍቅርህን ከመግለፅ ወደ ኃላ አትበል።

🌸 3⃣ሴቶች ግትር ወንዶችን ይጠላሉ።ደካማ ወንዶችን ደግሞ ይንቃሉ።አንተ ጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር ለመሆን ሞክር።

🌸 4⃣_ሴቶችን መልካም ንግግር፣ውብ ገፅታ፣ንፁህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ስለሚማርካቸው ሁሌም እነዚህ ነገሮች እንዲኖርህ ጥረት አድርግ።

🌸 5⃣ለሴት ቤቷ የቤተ መንግስት ያህል ክብር የምትሰጠው ስፍራ ነው።ቤቷ ስትሆን ዙፏኗ ላይ በክብር የተቀመጠች ንግስት ያህል ክብር ይሰማታል።በምንም ተአምር ይህን ቤተ መንግስቷን የሚያፈርስባት ነገር እንዳትፈጵም ።ከንግስና ዙፏኗ ላይ ልታወርዳት እንዳትሞክር።ይህን ካደረክ ንግስናዋን እንደመቃወም ይቆጠራል። ለንጉስ ንግስናውን ከመቀናቀን የበለጠ ትልቅ ወንጀል የለምና ጥንቃቄ አድርግ።

🌸 6⃣ሴት የቱን ያህል ብትወድህም ቤተሰቧን ማጣት አትፈልግም።አንተን ከቤተሰቧ በላይ እንድትወድህ ለማድረግ አትጣር ።ይህን ማድረግ ፋፃሜው የማያምር ጠላትነትን ሊያመጣብህ ይችላል።

🌸 7⃣_ሴት ከጎንህ(ጠማማ አጥንት)መፈጠሯን አትዘንጋ።ይህ አፈጣጠሯ የውበቷ ሚስጥር መሆኑን አወቅ ።ትንሽ ስህተት ባየህ ቁጥር አቃናታለው እያልክ እንዳትሰብራት ተጠንቀቅ።ስብራቷ ፍቺ ነው።ላቃናት ከሞከርኩ ትሰበራለች በማለትም የባሰ እንድትጠም መንገድ አትክፈትላት ።መካከለኛ ሰው ሁንላት ።

🌸8⃣_ሴት አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች (ስትናደድ) ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል።ነገር ግን እንዲህ አደረገች ብቻ በማለት እንዳትጠላት።ይህን ባህሪዋን ባቶድላት ሌሎች ሚስቡህ ባህሪዎች እንዳሏት አትዘንጋ።

🌸 9⃣ሴት አካላዊ ድካምና ስነ ልቦናዊ ጫና ሊያርፍባት ይችላል።በዚህ ወቅት አላህ(ሱብሀነሁ ወተአላ) የግዴታ አምልኮዎችን (ሰላትና ፆም)ሳይቀር ውድቅ አድርጎላታል።በዚህ ጊዜ እዘንላት: ትእዛዝ አታብዛባት።

🌸 🔟_ሴት አንተ ዘንድ ያለች(የፍቅር) ምርኮኛህ መሆኗን አትዘንጋ።ምርኮኛህን በጥሩ ሁኔታ ያዛት።እዘንላት፣ በድክመቷ የምትፈፅመውን ስህተት እለፋት ።ምርጥ የህይወትህ አጋር ትሆንሀለች።

🌸👒 መልካም ትዳር ለሁላችንም 🌸👒.

Send as a message
Share on my page
Share in the group
kumel bonge shared a
Translation is not possible.

ሙዓዊያ እና ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁማ በተጋጩ ግዜ ሁለት

ኢስላማዊ ስረወ መንግስት ተመሰረተ የሮሙ ንጉስ ይህን ሰምቶ

እንዲህ ሲል ደብዳቤ ፃፈ።

<<ከሮም ንጉሰ ነገስት ለ ሙስሊሞች መሪ ሙዐዊያ አቡ ሱፍያን!!

ባንተ እና በዐሊይ መካከል የተከሰተውን ግጭት

ሰምተናል።ስለዚህም ለሙስሊሞች መሪ አንተ መሆን

እንዳለብህም ስለምናምን አንተ ፍቃድህ ከሆነ የዐሊይን ጭንቅላት

ቀንጥሶ የሚያመጣልህን ወታደር ልላክልህ>>

ይህ ደብዳቤ ሙዐዊያ ጋር እንደደረሰም ሙዓዊያም

<<ከሙዓዊያ ለሮም መሪ!!! ሁለት ወንድማማቾች ስለተጣሉ

አንተ ምን አገባህ? አፍህን የማትዘጋ ከሆነ ጅማሬው እኔ ጋ የሆነ

እና ፍፃሜው አንተ ጋ የሆነ ሰራዊት ልኬ አንገትህን በማስቀንጠስ

ለዐሊይ በስጦታ መልኩ አበረክትለታለሁ>>

#ይህ_ትክክለኛ_ሙስሊሞች_ሳለን_ነው

_____

___

ካሊድ ኢብን ወሊድ ለፐርሺያው ንጉሰ ነገስት እንዲህ ሲል

ደብዳቤ ፃፈለት

<<ስለም ትድናለህ። እንቢ ያልክ እንደሆን ግን፤ እናንተ ህይወትን

የምትወዱትን ያህል ሞትን የሚወዱ ሰራዊቶችን ይዤልህ

እመጣለሁ።>>

ንጉሱ ይህን ደብዳቤ ካነበበ በኋላ የቻይናውን ንጉስ የጦር እርዳታ

ሊለምነው ደብዳቤ ፃፈለት።

የቻይናውም ንጉስ እንዲህ ሲል ደብዳቤ መልሶ ላከለት።

<<ንጉስ ሆይ! ተራራን እንኳን ለመናድ ካሰቡ ምንም

ከማያግዳቸው ወታደሮች ጋር ለመጋፈጥ አቅሙ ስለሌለኝ

ጥያቄህን መፈፀም አልችልም።>>

# ምን_ያህል_ሀያላን_እንደነበርን_ተመልከቱ

_____

____

በደውለቱል ዑስማኒያ የአገዛዝ ዘመን የሙስሊም ወታደሮች የጦር

መርከቦቻቸውን ይዘው በአውሮፓ ደሴቶች ሲያልፉ በአከባቢው ያሉ

አብያተ ክርስትያናት በሙሉ ሙስሊሞች መጥተው ፈትህ

እንዳያደርጉ በመፍራት ከበሮ ከመምታት እና ምንም አይነት ድምፅ

ከማሰማት ይቆጠቡ ነበር።

#ያኔ_ጀግና_ሳለን

_____

____

በደውለቱል ኡስማኒያ የአገዛዝ ዘመን በያንዳንዴ ቤት ደጅ ላይ

ሁለት የበር ማንኳኩያዎች ይኖራሉ። አንዱ ትልቅ ሲሆን አንዱ ትንሽ

ነው። በትልቀኛው ከተንኳኳ አንኳኪው ወንድ ነው'ና በሩን ሊከፍት

ሚመጣው ወንድ ይሆናል። ነገር ግን በትንሸኛዋ ከተንኳኳ

አንኳኪዋ ሴት መሆኗ ስለሚታወቅ ሴት ትከፍትላታለች።

በዚያ ምርጥ ዘመን አንድ ቤት ውስጥ ሰው ከታመመ ደጅ ላይ

ቀይ አበባ ይንጠለጠል ነበር። ያን አበባ የተመለከቱ ሰዎች ሁሉ

እዝያ ቤት በሽተኛ መኖሩን ስለሚያውቁ በበሩ ሲያልፉ ድምፃቸውን

ዝቅ ያደርጉ ነበር።

#ሹፍ_ምን_እንመስል_እንደነበር !!!

_____

_

ግዜው ሰላሁዱን አል አዩቢ በይተል መቅዲስን ባስመለሰበት ግዜ

ነበር። እና ጦርነቱ ነገውን ሊጀመር ማታ ላይ የጦር መሪው

ሰላሁዲን የወታደሮቹን ድንኳን እየዞረ ሲያዳምጥ፤ ግማሹ ለይል

ይሰግዳል፣ ሌላው ቁርአን ይቀራል፣ የተቀሩት ደግሞ ይዘክራሉ።

ግን ድንገት በሆነ ድንኳን አጠገብ ሲያልፍ በድንኳኑ ውስጥ ያሉት

ሁሉም ተኝተው ነበር። ይህን ግዜ፦"በዚህች ድንኳን አዳሪዎች

ምክንያት ልንሸነፍ እንችላለን" ብሎ አለፈ።

#ማንተኛበት_ዘመን

_____

___

ቀደምት ዑለማኦች በሶስት ነገራት አደራ ይባባሉ ነበር።

1፦ሰውዬው በሱ እና በአላህ መካከል ያለውን ግንኙነት ካሳመረ፤

በሱ እና በሌሎች መካከል ያለው ግንኙነት ያምርለታል።

2፦ሰውዬው ሚስጥራዊ ተግባሩን ካሳመረ አላህ ይፋዊ ተግባሩን

ያሳምርለታል።

3፦ሰውዬው የአኪራው ጉዳይ ካስጨነቀው አላህ የዱንያውንም

የአኪራውንም ጉዳይ ያግራራለታል።

_____

_

#ትልቁ_ኪሳራ_ማለት_ይህ_ነው

ጀነት ስፋቷ የምድርን እና የሰማያትን ያህል ሁና ላንተ በሷ ቦታ

ሳይኖርህ ሲቀር...ትልቅ ኪሳራ ነው።

በእለታዊ ፕሮግራምህ ውስጥ ቁርአንን መቅራት ካልተካተተ ትልቅ

ኪሳራ ነው።

ይህን ፅሁፍ በማሰራጨት ጓደኛህን እንድታነቃው ይከጀላል!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
kumel bonge shared a
Translation is not possible.

#ሸይኽ ኢብን ባዝ ተጠየቁ ፡ ሙቅ ውሃን በምናፈስበት ጊዜ

ቢስሚላህ እንላለንን፣ ይህም ጂን ቦታው ላይ ይኖራል ብሎ

በመፍራት ነው

መልስ፡

"አዎን! ቢስሚላህ ይበል ምን አልባት ቦታው ላይ ጂን ካለ

እንዲነቃ ለማድረግ ነው" ከዛም ሽይኹ እንዲህ አሉ" በርግጥም

በአንድ ወቅት አንድን ሰው ጂን ይዞት በሚቀራበት ቦታ ተገኝቼ

ነበር

#ሩቃ የሚያደርገው ሰው በሰውየው ላይ ለተደበቀው ጂኒ "ለምን

ያዝከው "አለው

#ጂንውም "የሞቀ ውሃ በአንዱ ልጄ ላይ ደፋና ገደለው "አለ

#የሚቀራዉ ሰውዬ ደግሞ "እሱ ልጅህ በቦታው መኖሩን

ስላላወቀ ነው" አለው

#ጂኒው ደግሞ "ለምን ቢስሚላህ አይልም ነበር እንዲያሳውቀው

(እንዲያነቃው)"

#ሽይኽ ዘይድ አል መድኸሊ ረሂምሁሏህ እንዲህ አሉ ፡

"ለማንኛውም የሞቀ ውሃ በፍሳሽ ትቦዎችም ይሁን በመሬት ላይ

አይደፋም ምክኛቱም መሬት በነዋሪዎች የተሞላች ነች

ምናልባትም በጂኖች አለም ወይም በትንንሽ ፍጡሮች ላይ ያርፋል

በዚህም ለበቀል ይነሳሱና ይይዙታል።ስለዚህ አንድ ሰው የሞቀን

ውሃ መድፋት ከፈለገ በቀዝቃዛ ውሃ ቅዝቃዘው የማያስቸግር

እስኪሆን ያብርደውከዛም ከፈለገ የፍሳሽ ትቦዎች ውስጥ ከፈለገ

መሬት ላይ ያፍሠው" ንግግራቸው እዚህ ጋር አለቀ ረሂመሁሏህ.

፟፟=========================

#ጉዳዩ አደገኛ ነው ሙስሊሞች ሆይ ነቃ በሉ ለወንድሞቻችሁ

ለእህቶቻችሁ ለእናቶቻችሁ አድርሱላቸው ስንትና ስንት እህቶች

በዚህ ሰበብ ችግር ውስት ይገባሉ ፓስታ የቀቀሉበትን ውሃ

አውጥተው በመድፋት ስንቱ ተለክፎዋል ስለዚህ አድርሱላቸው!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
kumel bonge shared a
Translation is not possible.

✍️የሰላተል ጀናዛ አሰጋገድ‼️

===============

🔘ወደ ሰላት ከመገባቱ በፊት

💫እንደ የትኛውም ሰላት ሙሉ የሆነ ውዱእ ይደረጋል።

💫እንደ የትኛውም ሰላት ወደ ቂብላ ይቀጣጫል።

💫እንደ የትኛውም ሰላት ሰፍ ይስተካከላል።

💫እንደ የትኛውም ሰላት ማእሙኖች ኢማሙን ተከትለው ይቆማሉ።

🔘የሰላቱ አሰጋገድ

✍️የመጀመሪያው ተክቢራ ይባልና…

ሱረቱል ፋቲሃ ይቀራል።

{بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ}

{الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ

إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ

اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ

صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ

غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ}

ይህንን ሲጨርስ ሁለተኛው ተክቢራ ይላል።

✍️ከሁለተኛው ተክቢራ በኋላ……

በነብዩﷺ ላይ ሰለዋት ያወርዳል።

«اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد»

ይልና ሶስተኛው ተክቢራ ይላል

✍️ከሶስተኛው ተክቢራ በኋላ……

ለሟቹ ዱዓ ያደርግለታል። ለምሳሌ ከመጡ ዱዓዎች መሃል……

«اللهم اغفر له وارحمه، وعافه واعف عنه،

وأكرم نزله، ووسع مدخله، واغسله بالماء والثلج والبرد، ونقه من الخطايا كما ينقى الثوب الأبيض من الدنس،

اللهم أبدله دارًا خيرًا من داره، وأهلًا خيرًا من أهله،

اللهم أدخله الجنة، وأعذه من عذاب القبر، ومن عذاب النار، ووسع له في قبره، ونور له فيه»

ከዚህም ውጪ ያሉ ዱዓዎች የቻለውን ያደርግለታል። ይህንን ሲጨርስ አራተኛው ተክቢራ ይላል።

✍️ከአራተኛው ተክቢራ በኋላ…

ቲንሽ ዝም ይልና እዛው በቆመበት ወደ ቀኝና ወደ ግራው ያሰላምታል።

«السلام عليكم ورحمة الله,

السلام عليكم ورحمة الله»

ይላል።

🔘አንዳንድ ነጥቦች

💫ጀናዛው ከኢማሙ ፊት ይቀመጣል።

ጀናዛው የወንድ ከሆነ;

ኢማሙ ጭንቅላቱጋ ይቆማል።

ጀናዛው የሴት ከሆነ;

ኢማሙ ወገቧ አካባቢ ይቆማል።

💫ባለው የሰጋጆች ብዛት ረዥም ሰፍ ከመስራት ይልቅ ሰፎቹ መብዛታቸው ይመረጣል።

💫አራቱንም ተክቢራዎች ሲባሉ እጅ ማንሳቱ የተሻለ የተወደደ ነው።

💫አንድ ሰው ኢማሙ የተወሰነ ከሰገደ በኋላ ደርሶ ወደ ሰላቱ ቢገባ የሚጀምረው ኢማሙ ከደረሰበት ቦታ ሳይሆን ከመጀመሪያው ቦታ ነው።

ለምሳሌ፦

ኢማሙ የሁለተኛው ተክቢራ ሲያደርግ ቢደርስ እሱ የሚያደርገው ሰለዋት ማውረድ ሳይሆን ፋቲሃን መቅራት ነው; በመጨረሻ ኢማሙ ሲያሰላምት ቶሎ ቶሎ ብሎ ይጨርስና ያሰላምታል።

💫ጀናዛው የሆነ ቦታ ተሰግዶበት የተቀበረ ከሆነ ሌላ ቦታ "ሰላተል غይብ" ተብሎ አይሰገድበትም።

💫አንድ ሰው ሰላተል ጀናዛ ቢያመልጠውና መስገድ ቢፈልግ ጀናዛው ቢቀበር እንኳ ቀብሩ አጠገብ ሄዶ ይሰግድበታል።

🔘ማሳሰቢያ

✏️ቀላል ከመሆኑም ጋ ብዙሃኖች የሚከብድ መስሏቸው ብዙ ጊዜ ከመስገድ ሲቆጠቡ ይታያሉና ሼር አድርጉላቸው።

🤲አላህ መጨረሻችን አሳምሮ ይውሰደን🤲

✍ሐምዱ ቋንጤ

🕌ከፉርቃን ሰማይ ስር

👍 በ Umma Life ሚድያ የአል-ፉርቃን ገፅ ለመቀላቀል⤵️⤵️

📎 https://ummalife.com/AlFurqan_IslamicStudio

👍 በ Telegram ሚድያ የአል-ፉርቃን ገፅ ለመቀላቀል⤵️⤵️

🔗 https://t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
kumel bonge Сhanged his profile picture
7 month
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group