Translation is not possible.

አያያዙ ብርቱ ነው !

የተራቀቀ ስልጣኔና ውስብሰብ መሳሪያ ያላቸውን ጉልበተኞች ስታይ " አሁን እነኚህ በምን ይነቀነቃሉ ?! " አትበል

የባርነት ቀንበር ድካምን ፣ የቅኝ ግዛት ግፍን ፣ የአፍሪካውያንን

ደም ፣ የካሪቢያያን እምባ በከንቱ ይቀራል ብለህ አታስብ

ኃያላኑ " ሥልጡኖች " በአፍሪካ ጅረቶች ደም ባፈሰሱ 20 እና 30

ዓመታት ውስጥ ፣ የግፋቸውን ግፍ ለመቅመስ በመካከላቸው

የ 1ኛው ዓለም ጦርነት ተከሰተ ፣ ተጫረሱ ፣ ተፋጁ ።

ኡኡታቸው ቀለጠ ።

ዳግመኛም !

ያለፉት የጥቁር ሙታኖች ጩሃት ሊያስተጋባ ፣ የጥቁር ህፃናት

ሰቆቃ ሊሰማ ፣ የጥቁር ሴቶች እምባ ጠብ ሊል ፣ የእርስ

በእርሳቸው መተራረድ በ 2ኛው ዓለም ጦርነት ቀጠለ ።

ጀሊሉ እንዴት ይቀጣል ብለህ አትጠይቅ ! #አያያዙ_ብርቱ_ነው ። የቆሰቆሱት እሳት እርስ በእርሳቸው ሊያያይዛቸው ቢረፍድ እንጂ አይዘገይም ።

አላህ ሆይ 🤲

በፍልስጤም ጋዛ ረዳት ላጡት ባሮችህ ከለላ ሁናቸው በወራሪዎች ጥቃት ህይወታቸው እየተቀጠፉ ያሉትን ወንድም እና እህቶች ከሸሂዶች መድባቸው

የታላቁ አርሽ ጌታ ሆይ 🤲

ሀይልም ፣ አቅምም ፣ ብልሀትም ካንተ ውጪ ለማንም የለውም :: በጉልበታቸው ተምክተው ንፁሃንን እየጨፈጨፉ ለሚገኙት በዳዮች ኃይልህን አሳያቸው ባንተ መንገድ ላይ እየታገሉ የሚገኙትን ባሮችህን እርዳታህ አይለያቸው

ኢላሂ 🤲

በዚህ ሰዓት ፣ በዚህ ደቂቃ በጋዛ በጭንቅ ላይ ላሉት ባሮችህ ድረስላቸው የጅብሪል ፣ የሚካኤል እና የኢስራፌል ጌታ ሆይ

ወራሪዎች የሙስሊሞችን መሬት ወረው ቤትህ አል አቅሷን እያረከሱት ይገኛሉና ይህን መስጂድህን የምንጠብቅበትን አቅም ስጠን

አሚን 😥🤲

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group