UMMA TOKEN INVESTOR

About me

አላህ ሱብሃና ወተዓለ እንዲህ ይለናል በሱረቱል ጡር ... ለጌታህ ፍርድም ታገሥ፡፡ አንተ በጥበቃችን ውስጥ ነህና፡፡ ጌታህንም በምትነሳ ጊዜ ከማመስገን ጋር አወድሰው፡፡

Translation is not possible.

የእስራ*ል ሀይሎች በምድር ውግያ ሀማስን በአመታት እንኳ ማጥፋት አይችሉም ተባለ።

ጋ-ዛ የቆዳ ስፋቷ የአዲስ አበባን ግማሽ አያክልም። ተራራ የለ ሸለቆ አባጣ ጎርባጣ ድንጋይ ቋጥኝ የለ መሬቱ አሸዋማና ለም መሬት ነው። በዛ ላይ በዛች ትንሽ መሬት 2.3 ሚሊዮን ህዝብ ተጨናንቆ ይኖራል። ያ ደግሞ ሁሉም አይነት የጦር መሣርያ ቴክኖሎጂ በጁ ለያዘው የእስራ*ል አየር ሀያል ጋ-ዛን በአየር ለማረስ ውሀ በብርጭቆ እንደመጠጣት ቀላል ሆኖላታል። ስለዚህ የእስራ*ል አየር ሀይል የጋ-ዛ ሰማይ ላይ እንደፈለገ መዋኘት ችሎዋል።

የምድሩ ግን እንደዛ አደለም። የተለየ ጉዳይ ነው። የጋ-ዛ መሬት ለስላሳ ስለሆነ ሀማስ ለአመታት የውስጥ ለውስጥ ጉድጓድ እንደ ፍልፈል ሲቆፍር ነው የሰነበተው።

አሁን ሰሜን ጋ-ዛ የገባው የእስራ*ል እግረኛም የገጠመው ይህንኑ ነው።

ሰሜን ጋ-ዛ ሲገባ ያን ያህል በጣም ከባድ መከላከል ያልገጠመው የእስራ*ል ሰራዊት እንደ ሸረሪት ድር ወደ ተቆፈሩት ጉድጓዶቹ በገባ ቁጥር የገጠመው ፈተና ግን ከባድ ነው።

የእስራ*ል ሰራዊት ጉድጓዶቹን ለመቆፈር ወራት ይፈጅበታል ያንን ሲያደርግ ግን ሀማ-ስ እንደገና ሌላ ጉድጓድ እየቆፈረ መዋጋቱን ይቀጥላል ስለዚህ ነገሩ ፈተና ነው ይላሉ የእስራ*ል ተንታኞች።

የጉድጓዶቹ ጥልቀት ከ 20-80 ሜትር ጥልቅ ነው እንደ ጉድጓዱ ሁኔታና ቦታ ቢለያይም። ጋ-ዛ ውስጥ የተቆፈሩ ጠመዝማዛ ጉድጓዶች ጠቅላላ ርዝመት እስከ 400 ኪ.ሜ ይሆናል። የአዲስ አበባ ግማሽ በማያክል ቦታ ያ ሁሉ ርዝመት ያለው ጉድጓድ መቆፈር ምን ያህል ጉድጓዱ ጠመዝማዛ ውስብስብና ጥልፍልፍ መሆኑን ያሳያል።

አንዳንዶቹ ጉድጓዶች oxygen የውሀ ማጠራቀሚያ አላቸው መብራት ያላቸውም ብዙ ናቸው። የመሣርያ ምግብ መጋዘን እና የስልክ ኔትወርክ ጭምር ያላቸው ጉድጓዶች ብዛት ቀላል አደለም። የሀማ-ስ ተዋጊዎች ድንገት ከጉድጓድ ወጥተው ጥቃት ሰንዝረው ወደ ጉድጓድ ስለሚመለሱ ወዴት እንደገቡ መፈለግም ከባድ ነው በተለይ በማታ። ታጋቾቹ የሚገኙትም እዛ ነው ተብሎ ይታሰባል።

የእስራ*ል ሠራዊት ጋር በቴክኖሎጂ ስለማይመጣጠኑ ሀማ-ሶች ካሏቸው አማራጮች አንዱ እንደዚ አይነት ዘዴዎችን መቀየስ ነው።

ሀማ-ሶች እንደዚ አይነት ጉድጓድ የመቆፈር ልምድ ካዳበሩ ቆይተዋል። የጋ-ዛ ገበሬዎች ከጥንት ጀምሮ ውሀ ለማውጣት በእጅ ጥልቅ ቁፋሮ የመስራት ጥበብ አላቸው።

ከባህርም አየርም ምድርም ታፍና ባለችው ጋ-ዛ ለአመታት የሀማ-ስ ታጣቂዎች ብዙ የሠው ጉልበትና ጊዜ ሚጠይቀውን እና እጅግ አደገኛ የሆነውን "ከተማ ስር ሌላ ከተማ" የተባለውን የጉድጓድ ኔትወርክ ለመገንባት የተገደዱት ምግብ መድሀኒት ሸቀጣሸቀጥ ነዳጅና መሣርያን ጨምሮ የተለያዩ ነገሮችን ለማስገባትና ወደ ፊት ጦርነት ቢጀመር ጠላት ጋር ለረጅም ጊዜ የሽምቅ ውግያ ለመዋጋት ውስጥ ለውስጥ በሰው ሀይል ከተቆፈሩ ጉድጓዶች ውጭ ሌላ ምርጫ ስላልነበራቸው ነበር።

እነዚህ ጉድጓዶች ለጋ-ዛ ነዋሪዎች የደም ስር ነበሩ ማለት ይቻላል። ከታች እንደምታዩት የተለያዩ አስፈላጊ ሸቀጦች በጎች ፍየል ከብት ግመል ጭምር በነዚ ጉድጓዶች ነበር ሚገቡት። የሆነ ጊዜ አምበሳ ሁላ ለፓርኪንግ ተብሎ መግባቱ ይነገራል።

እስራ*ል ከአየር ላይ የምትጥለው ቦምብ ወደ መሬት ውስጥ በጣም ጠልቆ ሰርስሮ መግባት ስለማይችል ያላት ብቸኛ አማራጭ የእግረኛ ሰራዊት መጠቀም ኢንጅነሮችና የፈንጂ ባለሙያዎችን ይዛ የጉድጓዱ መጀመሪያና መጨረሻ ድረስ እዛው ቦታው ድረስ ሄዶ በሀይለኛ ፈንጂዎችና ማሽነሪዎች እየደረመሱ ማፈራረስ ነው ይላሉ ተንታኞች።

ያንን ስታደርግ ደግሞ የጉድጓዶቹን መውጫ መግቢያ የሚያውቁት የሀማ-ስ ተዋጊዎች አንዴ ከፊት ከኋሃ ከቀኝ ከላይ ከሰር እያሉ በተለያዩ ስልቶች የእስራ*ልን ሰራዊት ፈተና ያከብዱበታል ስለዚህ ነገሩ አደገኛና ከባድ ነው ይላሉ ተንታኞች።

አሜሪካ ኢራቅና አፍጋኒስታን ስትደበድብ ለሷ በጣም ቀላል ነበር። ሆኖም በምድር ገብታ የተዋጋች ጊዜ ነው እግረኛ ሰራዊቷ የተሸነፈው። እስራ*ልም ተመሣሣይ ነገር ይገጥማት ይሆን?

ምንጭ- ሙሉ ዘገባው የ Al jazeera ነው

(ውድ አንባቢያን ፔጃችን ተደራሽነት በከፍተኛ ደረጃ restricted ስለሆነ ላይክና ሼር በማድረግ ተደራሽ እንድታረጉ እናሳስባለን)

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ታዋቂ አሜሪካዊቷ ቲክቶከር ሰለመች።

Megan Rice የተባለችዋ አሜሪካዊቷ ታዋቂ ሚሊኒየር የሆነችው ቲክ ቶከር የሰለመችው ቁርአን ቀርታ መገንዘብ በመቻሏና ፍልስጤማውያን የጋ-ዛ ነዋሪዎች ያ ሁሉ ውርጅብኝ እየወረደባቸው በቁም እየነደ-ዱ ሁሉ ነገራቸው እየወደመ እነሱ ግን ጌታቸው ላይ ያላቸው ለሰከንድ የማይነቃነቅ የእምነት ፅናት አስገርሟት እንደሆነ ገልፃለች።

እኔም እንደዚ አይነት ማይነቃነቅ የእምነት ፅናት እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ ብላለች።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🥀ሁሉን ችለው ታጋሽ በሆኑ ሰዎች የአላህ እዝነት ስላም ይስፈን🤲🤲

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

Breaking news

የየመኑ ሁ-ቲ የእስራ*ሏን Eilat ከተማ መቶ ከባድ ጉዳት ማድረሱን ገለፀ።

የእስራ*ል ምንጮችም ዘገባውን አረጋግጠው። በዛሬው የሁቲ ባሊስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ከተማዋ ውስጥ ያለ 1 ሀይስኩል ሙሉ ለሙሉ መውደሙን ገልፆዋል።

በቅርቡ የየመኑ ሁ-ቲ ባስወነጨፈው ሚሳኤል ኤርትራ ዳህላክ ደሴት የነበረውን የእስራ*ል ትልቅ ወታደራዊ የጦር ሰፈር ላይ ከባድ ጥቃት በማድረስ የወታደራዊ ጦር ሰፈሩ አዛዥን ጨምሮ በጦር ሰፈሩ የነበሩ የእስራ*ል ወታደሮች መሞ*ታቸው ይታወሳል። በዛው እለት ኤርትራ አምባሶይራ ተራራ ጫፍ ላይ የነበረው የእስራ*ል አየር መቆጣጠርያ ጣቢያ በሁቲ ባሊስቲክ ሚሳኤል ተመቶ መውደ*ሙም ይታወቃል።

እንደዚሁ ትናንት የአሜሪካ እጅግ ዘመናዊ ድሮን ነው የሚባለው Reaper ድሮን በሁቲ ከምድር ወደ አየር በሚወነጨፍ ሚሳኤል ተመቶ መውደቁ ይታወቃል።

ከሳውዲና በሳውዲ ከሚመራው የ 30 ሀገራት ጥምር ኔቶ ጦር ከአስር አመታት በላይ ሲዋጋ የቆየው ሁቲ በምድር ውግያ ላይ ካለው ጥንካሬ በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ የየመን ኢንጅነሮች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚሰሯቸው ባሊስቲክ ና ክሩዝ ሚሳኤሎች ሮኬቶች ራዳሮች ፀረ ድሮኖች የአየር መቃወሚያዎችና እና ድሮኖች ሰፊ አለማቀፍ ገረሜታ እየፈጠረ ነው። ከ 5 አመታት በፊት ከ 200 ኪ.ሜ በላይ ብዙም መጓዝ አይችሉም ጥቃት የማድረስ አቅማቸውም ትንሽ ነው በቀላሉ በፀረ ሚሳኤል ተመተው ይከሽፋሉ ሲባሉ የነበሩ የየመን ድሮኖች እና ሚሳኢሎች ዛሬ ከ 2000 በላይ ይጓዛሉ። በዚህም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ጅዳን ጨምሮ የሳውዲ በርካታ ከተሞች የሁቲ ሚሳኤሎችና ድሮኖች ሳውዲ በቢሊዮኖች ዶላር ከስክሳ የሸመተቻቸውን የአሜሪካን የሚሳኤል መከላከያ እያለፉ ቁልፍ ተቋማቶቿን በከፍተኛ ደረጃ ማውደም ሲጀምሩ ሳውዲ ሳትወድ በግድ ሁቲ ጋር የሰላም ስምምነት ለመፈረም መገደዷ ይታወቃል።

አሜሪካ የጋ-ዛ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ 6 ቢሊዮን የወጣበትን የአለም ትልቁ የጦር መርከቧን ጨምሮ በርካታ የጦር መርከቦቿን እና በቢሊዮን የወጣባቸው ሚሳኤልና ድሮን መከላከያዎቿን ወደ ቀይ ባህርና ሜዲትራኒያን ባህር በማሰማራት ከየመኑ ሁቲ ወደ እስራ*ል የተተኮሱ ባሊስቲክና ክሩዝ ሚሳኤሎችን መመከታቸው ይታወቃል። ሆኖም ሁቲ ባሊስቲክ ክሩዝ ሚሳኤልና አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን በብዛት አቀናጅቶ በመተኮስ የሚሳኤል መከላከያዎችን ሾልኮ መምታት እየቻለ መሆኑን የዛሬ ጥቃት ማሳያ ነው ይላሉ ታዛቢዎች።

የየመን ሁቲ ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዲየር ጄኔራል የህያ ሰሬ በበኩሉ የየመን ሳይንቲስቶች እና ኢንጅነሮች ሚሳኤሎችና ድሮኖችን መስራት ከጀመሩ አጭር ጊዜ ቢሆንም አለምን ያስደነቀ የፈጠራ ስራ እያሳዩ ነው ይላል። ድሮኖቻችን እና ሚሳኤሎች ከየመን ከ 2000 ኪ.ሜ በላይ ተጉዘው ኢላማ መምታት ጀምረዋል ብሎዋል። በቀጣይ በአሜሪካ ፀረ ሚሳኤል ማይመከቱ ከፍተኛ የማውደም አቅም ያላቸው እና ከ 3500 ኪ.ሜ በላይ ሳይስቱ የሚመቱ የተለያዩ አይነት ድሮኖች ሚሳኤሎችን በስፋት እየሰሩ ነው ያንን በሳምንታት ጊዜ ውስጥ በተግባር ታዩታላቹ ብሎዋል።

የሁቲ ሚሳኤሎችና ድሮኖች የናቶን መከላከያ ሾልከው ማለፍ መቻላቸው ዘመኑ እየተቀየረ መሆኑን ያሳያል ይላሉ ታዛቢዎች። የዛሬው መካከለኛው ምስራቅ ከዛሬ 60 አመት በፊት የነበረችው አደለችም። ዛሬ ዘመኑ እየተቀየረ እንደ ሁቲ ሂዝ-ቦላ የመሣሠሉ የሚሊሺያ ቡድኖች የራሳቸውን ድሮን ሚሳኤል እያሻሻሉ እየሰሩ ሀያላን ሚባሉ ሀገራትን በተወንጫፊና ፈጣን መሣርያዎች ማጥቃት እየቻሉ ነው ይላሉ።

በሌላ ዜና እንግሊዝ ውስጥ ሰልፍ የወጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ዘቢሊዮን ዶላሮች ሚገመት ለእስራ*ል መሣርያ ያቀርባል ወደ ተባለ የመሣርያ ፋብሪካ ግቢ ሰብረው በመግባት ስራ ማስቆማቸው ታውቆዋል።

የጋ-ዛ ጦርነት አሜሪካ እንግሊዝና ምእራብ ሀገራት ለሚገኙ የመሣርያ ፋብሪካዎች በመቶ ቢሊዮኖች የመሣርያ ሽያጭ ገበያና የስራ እድል በመፍጠሩ የመሣርያ ፋብሪካዎች ፈንጠዚያ ላይ ናቸው እየተባለ ነው።

Daily mail, press tv and vice news

image
image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

★ መመካት ሚፈልግ ሁሉ በአላህ ይመካ !!!

* አዎ በምድር ላይ ማንም ቢያስቸግርህ አዛ ቢያደርግ መከታህና መመኪያህ አላህ ብቻ ይሁን ።

* አላህ ወደሱ መንገድ ሚያደርስ ወደሆነው ኢስላም ከመራህ ምን ቀረብህ ! ! ! አልሀምዱ ሊላህ

ውዱ አዛኙ ጥበበኛው አላህ እንዲህ ይላል ፣ (( «መንገዳችንንም በእርግጥ የመራን ሲኾን በአላህ ላይ የማንመካ ለእኛ ምን አለን በማሰቃየታችሁም ላይ በእርግጥ እንታገሳለን፡፡ በአላህም ላይ ተመኪዎች ሁሉ ይመኩ፡፡» ))

((وَمَا لَنَا أَلَّا نَتَوَكَّلَ عَلَى اللَّهِ وَقَدْ هَدَانَا سُبُلَنَا ۚ وَلَنَصْبِرَنَّ عَلَىٰ مَا آذَيْتُمُونَا ۚ وَعَلَى اللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ الْمُتَوَكِّلُونَ)) (ሱረቱ ኢብራሂም፣ - 12)

★ ዱንያ ላይ ሙስሊም ከመሆነ በላይ የሚያስደስት ምንም ነገር የለም ።

አልሀምዱ ሊላህ

አልሀምዱ ሊላህ

አልሀምዱ ሊላህ

Send as a message
Share on my page
Share in the group