jemal ebrahim Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

jemal ebrahim shared a
Translation is not possible.

ሙስሊም አማራ አለ ግን?

~

በተያያዘው ቪዲዮ ላይ የሚታዩት ማኅበረ ደና ቁራ ን እንደሚያስተጋቡት የአማራ ህዝብ የአይሁድ ነገድ አይደለም። ይሄ ፍጥጥ ያለ ውሸት ነው። እንዲያውም "የአይሁድ ነገድ ነን" የሚል አካል በራሱ ላይ "መጤ ነኝ" ብሎ እየመሰከረ ነው። በርግጥ መጤነት የሰለጠኑ ሰዎች ዘንድ ነውር አይደለም። ነውር የሚሆነው በመጤነታቸው የሚኮፈሱ አካላት ሌሎችን "መጤዎች" እያሉ ሊያነውሩ ሲሞክሩ ነው። እንዲህ አይነቶቹን ነውር ጌጡዎች በ"ነውራችሁ" አታጊጡ ብለን እናስታውሳለን።

መታወቅ ያለበት ሐቅ ብሄርና ቋንቋ በዘመናት ውስጥ ውልደት፣ እድገትና ሞት ያስተናግዳሉ። አንድ የነበረ ቋንቋ በአካባቢ መለያየትና መራራቅ የተነሳ በሂደት የተለያየ ቋንቋ ወደመሆን ሊቀየር ይችላል። ይሄ ውልደት ነው። ከሌሎች ቋንቋዎች እየወሰደ የሚዳብርና የሚሰፋም አለ። የቋንቋ እድገት አንዱ መገለጫ ይሄ ነው። የተለያዩ ቋንቋዎች በሌሎች ተውጠው ሊጠፉም ይችላሉ። ይሄ የቋንቋ ሞት ነው። በውጭው በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ፣ በዐረብኛ፣... ተውጠው ብዙ ቋንቋዎች ሞተዋል። በሃገራችንም የከሰሙና በመክሰም ላይ ያሉ ቋንቋዎች አሉ።

የአማራ ብሄርና ቋንቋም በዘመናት ውስጥ ሌሎች ህዝቦች የቋንቋው ተናጋሪ በሆኑ ቁጥር እየሰፋ የመጣ ቅይጥ ማንነት ነው። የጋፋት ቋንቋ በዚህ ዓይነት ሂደት ጠፍቷል። የአርጎባ ህዝብ የራሱን ቋንቋ ጥሎ የአማርኛና የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሆኗል። ይሄ የአማርኛ ብቻ ሳይሆን የብዙ ቋንቋዎች የጋራ ባህሪ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በታሪክ አማራ የሚለው ቃል ክርስቲያን ማለት እንደነበር እስከ ቅርብ ጊዜ የሚታወቅ ነው። ይህ የሆነው የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪው በአመዛኙ ክርስቲያን በመሆኑ እንጂ አማራነት በራሱ ክርስትና ስለሆነ አይደለም። ብሄር ማለት የጋራ ቋንቋና ማንነት ያላቸውን ህዝቦች ለመግለፅ እስከዋለ ድረስ በእምነት ቢለያዩም አማርኛ ቋንቋ የሚያገናኛቸው ህዝቦች አሉ፣ ዛሬ። ትኩረቴ አማራ ከሚለው ጥሬ ቃል ላይ አይደለም። ወደ ኋላ ረዘም ያለ ዘመን ብንመለስ ብዙ ብሄሮችን የዛሬ ስማቸውን ከነ ጭራሹ አናገኝም። ይሄ ማለት የጋራ ማንነት አልነበረም ማለት አይደለም።

ስለዚህ ዛሬ የትናንቱ የአማራነት ፅንሰ ሃሳብ የለም። አማራ ማለት ዛሬ ብሄር እንጂ ሃይማኖት ገላጭ አይደለም። በብሄር መለኪያ ከአማርኛ ተናጋሪው ክርስቲያን ጋር አንድ የሆኑ ሙስሊሞችን "አማራ አይደላችሁም" አይባልም። ብሄሩ ውስጥ የመሸጉ ገፊ አካላት መኖራቸውም የሚቀይረው ነገር የለም። "ትግሬ ብሎ ሙስሊም የለም" ብለው የሚያምኑ አግኣዚያን ስለኖሩ ሙስሊም ትግሬዎችን ትግሬነታቸውን መግፈፍ አይቻልም። "የኦሮሞ ነባር እምነት ዋቄፈና ነው" የሚሉ አካላት ስላሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊምና ክርስቲያን ኦሮሞዎችን ኦሮሞነታቸውን መግፈፍ ይቻላል? አይሆንም። በብሄርና በቋንቋ የለየንኮ ፈጣሪ እንጂ ፖለቲከኞች አይደሉም። ከአፋር ቤተሰቦች የተወለደን አካል አፋርነቱን መፋቅ ይቻላልን? እንኳን ሌሎች ራሱም መቀየር አይችልም። የአማራ ሙስሊሞችም ጉዳይ እንደዚያ ነው።

ጉዳዩ በቁጥር ማነስና መብዛት የሚወሰንም አይደለም። በዐረቡ ዓለም ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖች 5% አይሞሉም። ቁጥራቸው ስላነሰ ዐረብነታቸውን መንጠቅ እንችላለን? አይሆንምኮ! በአማራ ፖለቲከኞች አግላይ አካሄድ ሰበብ በክልሉ ውስጥ ያሉ ከ17% (በመንግስት ህዝብና ቤት ቆጠራ ከተቀመጠው) በላይ ሙስሊሞችን ብሄር የለሽ ናቸው ልንል ነውን? አንችልምኮ! ደግሞም ራሱን በሆነ ብሄር የሚገልፅ አካል "እናንተ ግን ብሄር የላችሁም" ማለት አለበት ወይ? አይባልም። ስለሆነም ሙስሊም ወገኖቻችንን ራሳቸውን በአማራነት ስለገለፁ የምንተችበት አካሄድ ፈፅሞ የተሳሳተ ነው። ማድረግ ያለብን ዘረኝነት ሲጎትታቸው ካየን ከየትም ብሄር ቢሆኑ አላህን እንዲፈሩ ማስታወስ ብቻ ነው። እንጂ አማራ ተብለው እየተገደሉበት፣ እየተገፉበት ያለን ማንነት የለም አይደላችሁም አይባልም።

ስለዚህ  ዛሬ አማራነትን ክርስቲያን ማለት አድርጎ የሚገልፅ ካለ ምሁርም ይሁን መሀይም፣ ደጋፊም ሆነ ነቃፊ ያለ ጥርጥር ተሳስቷል። ይሄ አተረጓጎም የህዝቦችን ማንነትና ማህበራዊ ውቅር ተለዋዋጭነት (dynamism) ከግንዛቤ ያላስገባ ግልብ ድምዳሜ ነው። ስያሜዎች በዘመናት ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች እንደ አካባቢው ሁኔታ ይለዋወጣሉ።

* ትናንት ቱርክ፣ ደይለም፣ ፋርስ የሚሉት መጠሪያዎች ሙስሊም ያልሆኑ ህዝቦችን ለመግለፅ የዋሉበት ዘመን ነበር፣ ለሚታወቅ ምክንያት። ያ ዘመን ካለፈ በኋላ እነዚህ ስያሜዎች ሃይማኖትን ገላጭ የነበረው ይዘታቸው ቀርቷል። አማራም ላይ ያለው እውነታ ተመሳሳይ ነው።

* በፊት አጎራባቾቹ አማራና አርጎባ መሀል የነበረው እውነታም ይህንን አጉልቶ ያሳያል። ሰሜን ሸዋ ላይ አንድ ክርስቲያን አማራ ወደ ኢስላም ሲገባ "እከሌ አርጎባ ሆነ" ነበር የሚባለው። አንድ አርጎባ ወደ ክርስትና ሲገባ ደግሞ "አማራ ሆነ" ነበር የሚባለው። ዛሬ ግን አርጎባነት ዘር እንጂ ሃይማኖት እንዳልሆነ ግልፅ ነው። አንድ ሰው ሃይማኖቱ ስለተቀየረ ዘሩ እንደማይቀየር ማወቅኮ ያን ያህል ውስብስብ ሂሳብ አይደለም።

* ሲዳማ የሚለው ቃል ሃይማኖትን ሲገልፅ የነበረበት ዘመንም ነበር። ዛሬ የሲዳማ መስሊሞችን "ሲዳማ አይደላችሁም፣ ሙስሊሞች ናችሁ" ልንላቸው አንችልም። ምክንያቱም ሲዳማነት እንደ ትላንቱ ሃይማኖትን ሳይሆን የሲዳማ ቋንቋ በወል የሚያገናኛቸው ህዝቦችን የሚገልፅ የብሄር ስያሜ እንደሆነ ግልፅ ነውና። ይሄ ቀላል ግንዛቤ አማራ ዘንድ ሲደርስ መልኩን የሚቀይርበት ስሌት የለም።

ስለዚህ የአማራ ሙስሊሞች ከብሄር አንፃር እንዴት ራሳቸውን አማራ ብለው ይጠራሉ የሚል አተካራ ውስጥ መግባት አያስፈልግም። ይሄ ብሄር ተኮር ጥላቻና መነቋቆርን ከማምጣት ባለፈ የሚያመጣው ኸይር የለም። ማድረግ ያለብን በየትኛውም ብሄር ውስጥ ያደፈጡ ዘረኛ ቡድኖች መጠቀሚያ እንዳንሆን ተቆርቋሪነት በሚታይበት መልኩ እርስ በርሳችን መመካከር ነው። ዋናው ነገር ኢስላማዊ ወንድማማችነታችን የዘር አጥር የሚገድበው አለመሆኑ ነው። የላ ኢላሀ ኢለላህ ገመድ ከዘርና ከቋንቋ በላይ ነው። ዛሬ ስለታመምን እንጂ ለሙስሊሙ አማራ ከነሷራው አማራ በላይ ሙስሊሙ ኦሮሞ ነው የሚቀርበው። ለሙስሊሙ ኦሮሞ ከነሷራው ኦሮሞ በላይ ሙስሊሙ አማራ ነው የሚቀርበው። በጠጣነው ፖለቲካዊ መርዝ ሳቢያ ቢተናንቀንም እውነታው ያ ነው። በዘር ቢሆን ለውዱ ነብያችን ﷺ ከሐበሻው ቢላል በላይ አጎታቸው አቡ ለሃብ በስጋ ይቀርባቸው ነበር። ኢስላማዊው መለኪያ ግን ሌላ ነው። ኢማንና ዘር እኩል ሚዛን ላይ አይቀመጡምና።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጁማደል ኡላ 27/1445፣ (ታህሳስ ዐ1/2016))

=

Send as a message
Share on my page
Share in the group
jemal ebrahim shared a
Translation is not possible.

ከዕለታት አንድ ቀን ተኩላ እና አህያ የሳር ቀለም እንዲህ ነው እንዲያ ነው በሚል ክርክር

ውስጥ ገቡ ።

አህያ ፡- “ የሳር ቀለም ቢጫማ ነው ” አለ።

ተኩላ ፡- “ በፍፁም! አረንጓዴ ነው ” አለ።

ክርክራቸው እየጦፈ መጣ ። ሊያስማማ የሚችል ነጥብ ላይ መድረስ አልቻሉም ።

በመጫረሻም የጫካ ንጉስ ከሆነው አንበሳ ዘንድ ቀርበው መሸማገል እንዳለባቸው ወሰኑ።

ሽምግልናው ተጀመረ።

ሁለቱም የመከራከሪያ ሃሳባቸውን አቀረቡ። አንበሳም የሁለቱን የመከራከያ ነጥብ በጥሞና አዳመጠ። የፍርድ ሂደቱን ለመከታተል የታደሙት እንስሳት በሙሉ ውሳኔውን ለመስማት ጆሯቸውን ጣል አደረጉ።

አንበሳው ታዳሚውንም ሆነ ተኩላውን ቅር የሚያሰኝ የፍርድ ውሳኔ አስተላለፈ።

ተኩላው በአንድ ወር እስራት እንዲቀጣ ሲወሰንበት አህያው ደግሞ በነፃ ተሰናበተ።

በፍርዱ ውሳኔ ቅር የተሰኘው ተኩላ እንዲህ በሚል ስሞታ አቀረበ ፡-

“ክቡር አንበሳ ሆይ! የሳር ቀለም አረንጓዴ አይደለምን?”

አንበሳም “አዎ በርግጥ አረንጓዴ ነው” በማለት መለሰ።

ተኩላውም “ታዲያ በየትኛው ጥፋቴ ነው ለአንድ ወር ያህል ዘብጥያ እንድወርድ

የወሰንክብኝ” በማለት ጠየቀ።

አንበሳውም “ትክክል ነህ, በአመለካከትህ ቅንጣት ስህተት አላስተዋልኩም። ጥፋትህ

በዚህ ጉዳይ ከአህያ ጋር ክርክር ውስጥ መግባትህ ነው። ነገሮችን በጥልቀት መረዳትና መገንዘብ ከማይችል አካል ጋር መከራከር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዘን አንደሚችል ትምህርት ትቀስም ዘንድ ብየ ነው የአንድ ወር እስራት የወሰንኩብህ” አለው ።

ነገ ደግሞ "አህያ" ብሎናል ብለው ይመጣሉ

Send as a message
Share on my page
Share in the group
jemal ebrahim shared a
Translation is not possible.

ያህያ ሲንዋርን በእስር ቤት ሲያሰቃየው የከረመው መርማሪ ሚካኤል ኮቢ ስለርሱ እንዲህ በማለት የምስክርነት ቃሉን ይሰጣል።

"ከእናቱ የበለጠ ያህያ ሲንዋርን አውቀዋለሁ። እርሱ ጠንካራ እምነት ያለው ግትር ሰው ነው። እስራኤል ከምድረ ገፅ መወገድ አለባት ብሎ በእጅጉ ያምናል። እጅ መስጠት በህይወት መዝገበ ቃላቱ ውስጥ የለም። እስከ መጨረሻው የጥይት ቀለሐ ድረስ ይፋለማል። እርሱ ያህያ ሲንዋር ነው"

በወራሪዋ እስራኤል እስር ቤት ውስጥ 24 ዓመታትን ያሳለፈ የወጣትነት ዕድሜውን ከፍርግርጉ ኋላ የኖረ! በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ተወልዶ አሁን የሐማስ ቁልፍ ሰው! ያለበትን ለጠቆመ ዳጎስ ያለ ወረታ አለው የተባለለት የትም ቢገባ ተከታትዬ እይዘዋለሁ አሊያም እገለዋለሁ በማለት እስራኤል የዛተችበት የህያ ሲንዋር ማን ነው?! ሙሉ ታሪኩን አስነብባችኋለው ኢንሻ አላህ።

#gaza

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
jemal ebrahim shared a
Translation is not possible.

ያህያ ሲንዋርን በእስር ቤት ሲያሰቃየው የከረመው መርማሪ ሚካኤል ኮቢ ስለርሱ እንዲህ በማለት የምስክርነት ቃሉን ይሰጣል።

"ከእናቱ የበለጠ ያህያ ሲንዋርን አውቀዋለሁ። እርሱ ጠንካራ እምነት ያለው ግትር ሰው ነው። እስራኤል ከምድረ ገፅ መወገድ አለባት ብሎ በእጅጉ ያምናል። እጅ መስጠት በህይወት መዝገበ ቃላቱ ውስጥ የለም። እስከ መጨረሻው የጥይት ቀለሐ ድረስ ይፋለማል። እርሱ ያህያ ሲንዋር ነው"

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
jemal ebrahim shared a
Translation is not possible.

የጀመርናቸው ጓደኝነቶች ሁሉ አይዘልቁም፤

መንገድ ያጃመሩን ሁሉ አብረዉን አይጨርሱም፤

እያንዳንዱ ሰው በሕይወታችን ዉስጥ የሆነ የሆነዉን ክፍል ወስዶ ይሄዳል፤

ከፊሉ ተራምዶ ይቆማል፤

ሌላው ሸኝቶ ይመለሳል ፤

ሌላው ረጅም ሄዶ ይጠፋል፤

ሁላችንም ምክንያቶች ምን ይሁን ምን የከሰሙና ያልተሳኩ ግንኙነቶች ይኖሩናል፣

ዐይብ ካለባቸው ተመልሰህ አትግለጥ፤

የሄዱ ሰዎችን ሚስጢር አታውራ፣

መልካም የነበሩ ጊዜያትን አስታውስና የግንኙነቶችን ክብር ጠብቅ፤

መመለስ የማትችለዉን ዘመን ወደኋላ አትጎትት፤

የተዘጋን መቃብር አትክፈት፤

ወረቀቱን ገልብጥና በአዲስ ገፅ ጀምር፤

ወደፊት ሂድ፤

ሕይወትህን ኑር፤

ባለህ ተደሰት፤

በተሰጠህ እርካ፤

በበለጡህ አትቅና፤

ለሰዎች ተደሰት፤

ለመደሰታቸዉም ምክንያት ሁን፣

እስከመጨረሻው አብሮህ የሚዘልቅ እሱ ነዉና

ቀልብህን በጥላቻና ቅናት አታጠልሸው፣

ሐቢቢ

ይህች ዱንያ እኮ በጣም አጭር ናት።

ለጥላቻ የሚበቃ ቦታ የላትም።

" ወሬ አታምጡልኝ፤ ሁላችሁንም እንደወደድኩ ልኑር ።" ይሉ ነበር ረሱላችን ሶ.ዐ.ወ።

እንደርሳቸው እንሁን።

ሶባሐል ኸይር

የምትወዱኝ ሼር አድርጉ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

Telegram: Contact @MuhammedSeidAbx

Telegram: Contact @MuhammedSeidAbx

ወደ ቤታችሁ እንኳን መጣችሁ
Send as a message
Share on my page
Share in the group