እስራኤል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በፈፀመችው ጥቃት 350 ፍልስጥኤማውያን ተገደሉ
የእስራኤል ጦር ተዋጊ ጄቶች በጋዛ ከተማ አል ዳራጅ ሰፈር የአል-አሳሊ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ላይ በፈፀመው ጥቃት የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 30 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል። በቤቴ ላህያ የእስራኤል ወታደሮች በሰሜን ጋዛ በሚገኝ ትምህርት ቤት ተጠልለው የነበሩ በርካታ የአንድ ቤተሰብ አባላትን ገድለዋል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተሰራጨ ቪዲዮ መሰረት የአቡ ሳላህ ቤተሰብ የሆኑ በርካታ አስከሬኖች በኢንዶኔዥያ ሆስፒታል አቅራቢያ በሚገኘው አሌፖ ትምህርት ቤት የመጫወቻ ሜዳ ላይ ይታያል።
በሌላ በኩል በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ ዋዲ አል-ሳልቃ አካባቢ፣ የእስራኤል ጥቃት በመኖሪያ ቤት ላይ ካነጣጠረ በኋላ አንድ ሕፃን ጨምሮ አራት ሰዎች ተገድለዋል።በጋዛ የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ከጥቅምት 7 ጀምሮ በእስራኤል ጥቃት የተገደሉት ፍልስጤማውያን ቁጥር 17 ሺ 1 መቶ 77 የደረሰ ሲሆን ከ46,000 በላይ ሌሎች ፍልስጥኤማውያን ቆስለዋል። ባለፉት 24 ሰዓታት ደግሞ 350 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን ሚኒስቴሩ አክሎ ገልጿል።
በሰሜን ጋዛ የሚገኘው የጃባሊያ የስደተኞች ካምፕ የእስራኤል ታንኮች አካባቢውን ከበው ከባድ ውጊያ በዚህ ሰዓት እየተካሄደ ይገኛል። በሃማስ የሚተዳደረው የአካባቢው ባለስልጣን 100,000 የሚጠጉ ሰዎች በካምፑ ውስጥ እንደሚገኙ እና ለረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል ብሏል።ባለፈው ሳምንት የሰብአዊ እርቅ ካበቃ በኋላ ምንም አይነት እርዳታ ወደ ሰሜን ጋዛ አልደረሰም።
በትናንትናው እለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሃላፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በጋዛ ያለው የሰብአዊነት ስርዓት ሊፈርስ እና ህዝባዊ ስርዓቱ ሙሉ በሙሉ ሊናጋ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ገተሬዝ ይህንን አስተያየት ቢሰነዝሩም የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤሊ ኮኸን ግን ተችተውታል። የጉቴሬዝ የስልጣን ቆይታ "ለአለም ሰላም አደጋ" ነው ሲሉ ጠርተውታል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል