Translation is not possible.

የሰዉ ልጅ ግን በምኑ ነዉ ሊኮራ የሚችለዉ?

ገንዘብ ፣ ዉበት፣ እዉቀት ፣ጤና፣ልጅ ሁሉም ከአሏህ ናቸዉ የሆነ ቀን ሁሉም ወደ አሏህ ይሄዳሉ ።

1,ለዘመናት ባካበተዉ ሀብታም ሁኖ ሲኩራራ በ1 ቀን ስህተት ስበብ ድሀ ይሆናል።

2,ከአሏህ በሆነ ዉበት ሲኩራራ እርጅና መጥቶ ወይም በድንገተኛ አደጋ ያጣዋል።

አረብ ሀገር ያሉ በጋዝ ፍንዳታ ምክኒያት ዉበታቸዉን ያጡ እህቶች የበፊት ፎቶአቸዉን ከአሁኑ ጋር ሲለቁት ሳይ 😓 ያ አሏህ ዉበትም በድንገት ይታጣል ።

3, እዉቀት አለኝ ብሎ መኩራራትም አደጋ አለዉ ። ብዙ በእዉቀታቸዉ ያስገረሙን ሰዎች የሰዉ ልጅ ለህመማቸዉ ስበብ ቢሆንም አዕምሯቸዉን አጥተዉ አይተናል።

4,ጤናም አያኮራ ። ድንገት በተቀመጥንበት ላንነሳ እንችላለን ። በብዙዎችም አይተናል።

5,ልጅ ልጅም ከአሏህ ነዉ ድንገት ሊታጣ ይችላል።

ሁሉም ከአሏህ ነዉ ። የአላህን ፀጋ ልናመሰግንበት እንጅ ልንኮራበት የተገባ አይደለም ።

ምን የሚያስተማምን ነገር አለና ይኮራል?

መልካም ዉሎ 💝

Send as a message
Share on my page
Share in the group