UMMA TOKEN INVESTOR

Diana Kheyru shared a
Translation is not possible.

የዓለም ህዝብ ግን አይገርምም⁉️

=======================

(ዓለም በዚህ ዘመን አይታው የማታውቀው የጦር ወንጀልና የዘር ጭፍጨፋ በጘዝ'ዛ)

||

✍ 365 km² ስፋት ባላት አነስተኛ ከተማ ውስጥ 2.3+ ሚሊዮን ዜጎች ተጠጋግተው ይኖሩባታል። በዚህች densely populated በሆነች ከተማ ላይ ለተከታታይ 3 ሳምንታት ያላባራ ከ12 ሺህ ቶን በላይ ቦምብ ሲዘንብ፤ በዚህም ሳቢያ፦

1) በትንሹ 7,028 የሚሆኑ ፈለስጢናዊ ሙስሊሞች ሲገደሉ፣

2) ከ70% በላይ የሚሆኑት ህፃናትና ሴቶች ሲሆኑ (2,913 ህፃናትና 1,709 ሴቶች)፣

3) 18,482 የሚሆኑት ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ሲዳረጉ፣

4) ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 481 የሚሆኑት ሲገደሉ (ከመካከላቸው 209 የሚሆኑት ህፃናት ናቸው።)፣

5) ከ1,650 በላይ የሚሆኑት ጀናዛቸው እንኳ ሳይገኝ እስካሁን ድረስ በቦምብ በፈራረሱት ህንፃዎች ስር ሲሆኑ (ከመካከላቸው 940 ህፃናት አሉበት።)፣

6) 731 የሚሆኑ ፈለስጢናዊ ሙሉ ቤተሰቦች ሲገደሉ፣

⑦) 101 የጤና ባለሙያዎች ሲገደሉና 100 የሚሆኑት ሲቆስሉ፣

⑧) 12 ሆስፒታሎችና 32 የጤና ማዕከላት በነዳጅ እጥረትና በቦምብ ጥቃት ከአገልግሎት ውጭ ሲሆኑ፣

9) በኢንኩቤተር ውስጥ የሚገኙ ከ130 በላይ የሚሆኑ ህፃናት ያሉበት ሆስፒታል ባጋጠመው በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ነፍሳቸው በእንጥልጥል ላይ ሲገኝ፣

⑩) ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ንጹሐን ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፖች፣ በት/ቤቶች፣ በሆስፒታል ግቢዎች፣ በመስጂዶችና ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው ሳለ በዛው ባሉበት ጥቃቱ ሲያገኛቸው…

(ከሰው ነፍስ አይበልጥምና ወደ አመድነት ስለተቀየሩት ውብ ህንፃዎችና መሠረተ ልማቶችማ አውርተን አንዘልቀውም።)

የሰለጠነ ተብዬው ዓለም አሁንም «ጦርነቱ ይቁም!» ከማለት ይልቅ «እስራኤል ራሷን የመከላከል መብት አላት፣ ሐማስ መጥፋቱን ማረጋገጥ አለባት፣ ከጎንሽ ነን፣ ሐማስ ሽብርተኛ ነው፣ በሐማስ ጥቃት ለሞቱተረ እስራኤላዊያን አዝነናል!…» እያሉ ነው።

ትንሽ አሻሻልን የሚሉት ደግሞ ጦርነቱ መቆም የለበትም፤ ግን የተወሰነች እርዳታ ይግባላቸው ይላሉ።

እስካሁን በጋዛ መብራት የለ፣ ውሃ የለ፣ ምግብ የለ፣ ነዳጅ የለ…። በዚህ የተነሳ የቆሰሉትና መደበኛ ህመም የሚታመሙትም መታከም አልቻሉም።

ዙሪያውን በከበባ ስለሆነ ለጠናበት ታማሚ የውጭ ሕክምና እንዲያገኝ ማድረግ አልተቻለም።

እስራኤል ከላይ በአየር ከምታዘንበው የቦምብ ዝናብ ባሻገር ከምግብና ውሃ እንዲሁም ከሕክምና ከልክላ በጅምላ ጭፍጨፋ የጦር ወንጀልና የዘር ማፅዳት ወንጀል በመፈጸም ላይ ትገኛለች። ይህ ሁሉ የሚሆነው ዓለም እያዬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ተመድ ተብዬውም ሆነ የትኛውም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነኝ የሚል ተቋም ሁሉ የውሃ ሽታ ሆኗል። የነርሱ ህግ እነርሱን ለማዳን እንጂ ለሌላው አይሠራም። እነርሱ ዘንድ የሙስሊም፣ የዓረብና የአፍሪካዊ ሞት ከውሻቸው ሞት በታች ነው።

ግን ነፍስ ሁሉ እኩል ናትና የእጃቸውን አንድ ቀን ማግኘት አይችሉም። ነገ ላይ በሌላ የነርሱ አካል ላይ ጥቃት ሲፈጸም በሚዲያቸውም ሆነ ባልተጻፈው ህጋቸው ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ሲለፍፉ እናገኛቸዋለን።

አላህ ውርደታቸውን ያቅርበው፤ ለተበዳዮች ነስሩን ያፍጥነው።

አላህ የአሸናፊዎች ሁሉ አሸናፊ የሆነ ጥበበኛና ታጋሽ ጌታ ነው። አንድ ቀን አይርላቸውም።

Send as a message
Share on my page
Share in the group
1 year Translate
Translation is not possible.

💔

ፍልስጤማዊያን ህፃናት ከተናገሩት በጥቂቱ…

* ሁሉንም ነገር ለ አላህ ነግረዋለው። (የ ሶስት አመት ህፃን)

* የታሉ አረቦች፣ የታሉ ሙስሊም ሀገራት

* እህቴ ለደቂቃዎችም እንኳን ቢሆን አልተለየሁሽም

* አሽሃዱ አላ ኢላሀ አላ አላህ በል ወንድሜ

* በጋዛ በየቀኑ ስድስት ሰላት እንሰግዳለን… ፈጅር፣ ዝሁር፣ ዐስር፣ መግሪብ፣ ኢሻ እና ሰላተል ጀናዛ።

*

__________________________

* ፈለስጢናዊት እናት ልጇን ሁለቴ ትሸከማለች። የመጀመሪያው በሆዷ ሲሆን ሁለተኛው በጀናዛ መሸከሚያ ቃሬዛ ነው።

* ማታ ማታ ስንተኛ ሂጃባችንን ለብሰን ነው የምንተኛው። ምክንያቱም ቦምብ ተጥሎብን ከሞትን ጀናዛችን ሲያገኝ ተሸፋፍኖ እንዲገኝ እንፈልጋለንና።

* "ልጅህ ጠባብ የሆነ የመትረፍ እድል አለው።"

ይህ ዶክተሩ ስለ ልጄ የነገረኝ ነበር።ትንሽ ቆይቼ ስመለስ ልጄም የለም።ዶክተሩም የለም። ሆስፒታሉም የለም።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Diana Kheyru shared a
Translation is not possible.

ሥራ አጥቶ እየተንከራተተ ያለን "መቼ ነው ሥራ የምትጀምረው?" ብለህ ሌላ ጭንቀት አትጨምርበት።

አማራጭ ሲጠፋው ሀገሩን ለቆ በስደት ያለን "መቼ ነው የምትመለሰው?" እያልክ ብሶቱን አትቀስቅስበት።

ትዳር የዘገየባትን ሴት "መቼ ነው የምታገቢው?" እያልክ አትነዝንዛት። ራስ ምታት አትሁንባት!

ሀሳብና ጭንቀታቸውን ታግለው አፍነው የአላህን ፈረጅ በትዕግስት የሚጠባበቁን ጥያቄ በማብዛት ሌላ ችግር አትሁንባቸው።

ምን እንደሚጠብቁ አትጠይቃቸው!

ከመጠበቅ ውጪ ሌላ አማራጭ ቢኖራቸው ያደርጉት ነበር!!

ሪዝቅ ያለው በአንተ ሳይሆን በአላህ እጅ ነውና ተዋቸው። ከቻልክ አግዛቸው፤ አልያም ዱዓ አድርግላቸው! ካልቻልክ አትረብሻቸው ዝም በላቸው!

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Diana Kheyru shared a
1 year Translate
Translation is not possible.

አሁን ላይ አብዛህኞቻችን በፍልስጢን ወንድምና እህቶቻችን ላይ የሚደርሰውን ዘግናኝ ግፍ እያየን ምንም ማድረግ ባለመቻላችን ከንፈራችንን እየመጠጥን ይሆናል፤

አንዳንዶቻችን ደግሞ ምናልባት ፍልስጢን ኒውክሌር ብትታጠቅ እንደዚህ አይደፍሯት ይሆናል፤ ሌላም ሌላም ነገሮችን እያሰብን እምሯችን ግራ ተጋብቶ ይሆናል።

ዳሩ ግን 'የሙእሙን ትልቁ መሳሪያው ዱኣ ነው'

ለዛውም አንድ ሰው ሩቅ ላለ ወንድሙ የሚያደርገው ዱኣ🤲🤲🤲

አላህ ለፍልስጢን ወንድሞቻችን ድልን ያጎናፅፋቸው። ከመጥፎ ነገር ሁሉ ይጠብቃቸው።🤲🤲🤲

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Diana Kheyru shared a
Translation is not possible.

የመጨረሻው የመስጂደል አቅሳ ጠባቂ

Mahi mahisho

ይህንን ታሪክ ስተረጉም ዕንባ እየተናነቀ የራሴ ልብ ሰላም ነስቶ በብረት ክንድ ይደልቀኛል። የዕንባ ከረጢቴ ዘለላ ዘለላ ዕንባን እያረገፈ ሆድ ያስብሰኛል። እንዲህ ዓይነት የኢስላም ዘቦች ማለፋቸው እያስገረመ ያስለቅሰኛል። ቁጭት፣ ብሶት፣ ንዴትና ሀዘን ተፈራርቀው እኔስ ለኢስላም ምን አበረከትኩ ያስብለኛል።

እርሱ ኢየሩሳሌምን ለቆ ወደ ሀገሩ ቱርክ እንዲመለስ በታዘዘ ጊዜ “በይተል መቅዲስ ከሁሉ ነገሬ በላይ ነች ሦስተኛውን ቅዱስ ስፍራ ትቼ ብሄድ ረሱል ያዝኑብኛልና ፈፅሞ ይህን ቦታ ለቅቄ አልሄድም" ነበር ያለው።

“ኢልሃን በርዳክጂ” የተሰኘ የቱርክ ጋዜጠኛ “አቅሳ መስጂድ ግቢ ውስጥ አውቀዋለሁ” በሚል ርዕስ ታሪኩን እንዲህ ሲል ያካፍለናል:-

“አየሩ ሞቃታማ ነበር ሰውነቴ በላብ ተዘፍቋል። ፎቶግራፍ እያነሳሁ ወደ ላይኛው አደባባይ ወደ አስራ ሁለት ሺህ ሻማዎች ግቢ ወጣሁ፡፡ ከመግቢያው በራፍ አካባቢ በዘጠናዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኝ አንድን ሰው ተመለከትኩ። ልብሶቹ ቆሽሸዋል። ስጋ የለውም በአጥንቱ ቀርቷል። ማደሪያ የለው እዚያው ግርግዳውን ተደግፎ አረፍ ይላል። ከርሃብ መፈራረቅ ብዛት ሆዱ ከጀርባው ጋር ሊጣበቅ ተቃርቧል። ያደፉ ልብሶችን ያጠለቀ ፀጉሩና ፂሙ የተንጨባረሩ ጥቁርቁር ያለ ፊት ድህነት አጎሳቅሎ ያጠወለገው ሰው ይታያል።

አጠገቤ ከነበሩት ሰዎች አንዱን ጠርቼ ይህ ሰው ማነው? በማለት ጠየቅኩት "እብድ ነው እዚህ እንደ ሃውልት ቆሞ ለዓመታት ኖሯል። ማንንም አያናግርም። እሱ የሚመለከተው መስጂዱን ብቻ ነው" የሚል መልስ ቸረኝ።

ተጠጋሁትና ሰላምታ አቀረብኩለት። ዞረና ተመለከተኝ ዓይኖቹን ወደ መስጂዱ አቅጣጫ እየመለሰ "ሰላም ላንተ ይሁን" አለኝ። ይበልጥ ተጠጋሁትና ስለ ማንነቱ ጠየቅኩት፡፡ ሐዘን ባጠወለገው ፊቱ ጥርሱን ፈልቅቆ እንዲህ ሲል ታሪኩን አጫወተኝ

"እኔ የአስራ አንደኛው የመሣሪያ ጥበቃ ቡድን መሪ ስምንተኛው ሻለቃ የኦቶማን ጦር ስድስተኛው አምድ ኮረኔል ሐሰን አልግህዳርሊ ነኝ"

"ኦቶማን ኢምፓየር እየተጠቃ በነበረበት በዛን ወቅት በይተል መቅዲስ እንዳይዘረፍ ሰራዊታችን ተመደበ፡፡ የእንግሊዝ ጦር መስጂደል አቅሳን እንደተቆጣጠረ እኔም ጓደኞቼም ተይዘን በአንድ ክፍል ታጎርን"

ወደ ሀገሬ እንድመለስ ትዕዛዝ ሲሰጠኝ የካፒቴን ሙስጠፋ ንግግር ትዝ አለኝ

"ኢስላማዊው መንግስት በመፈረካከስ ላይ ነው። የተከበረው ሰራዊታችንም እየሸሸ ነው። አመራሩ ወደ ኢስታንቡል እንድመጣ ጠርቶኛል። በይተል መቅዲስ የሱልጣን ሰሊም አደራ ነው። ኢየሩሳሌምን ሸሽቶ የሄደ የመጀመሪያው ጦር እንዳንሆን ተጠንቀቁ፡፡ አደራ የእስልምናን ክብር ከእግራችሁ በታች እንዳታስቀምጡት"

ይህ ቃል ታወሰኝ በፍልስጤም ያሉ ወንድሞቻችን ኢስላማዊው ጦር ኦቶማን ኢምፓየር ጥሎን ሄደ እንዳይሉና እርዳታን የነፈግናቸው እንዳይመስላቸው በማሰብ ብቻዬን እዚያው ቆየሁ፡፡ ከአራት መቶ ዓመታት በኋላ የአል-አቅሳ መስጂድ እንዳያነባ ሰጋሁ። በዚህ ሁኔታ ዓመታቶች እንደ ዐይን ብልጭታ አለፉ። ሃምሳ ሶስት ነበርን። ጠላቶቻችንን ተጋፍጦ ማሸነፍ ሳይቻለን ቀርቶ የሁሉም ጓደኞቹ እጣ ፈንታ ሸሂድነት ሆነ"

ዓይኖቹ በዕንባ ተሞልተው ዕንባው ግንባሩ ላይ ከሚወጣው ላብ ጋር ተቀላቀለ።

"ልጄ እባክህ ስትመለስ ወደ ሳንጃክ ቶካት መንደር አቅና። የካፒቴን ሙስጠፋ መኖርያ እዚያ ነው፡፡ አማናውን የተቀበልኩት ከርሱ ነው። ስታገኘው እጆቹን ሳምልኝና እንዲህም በለው። አንድ ወታደርህ ባስቀመጥከው እዚያ ቦታ መስጂደል አቅሳን እየጠበቀ ነው በትዕዛዝህ መሠረት ካስቀመጥከው ቦታ አልተነቃነቀም። መስጂደል አቅሳን ከመጠበቅ ስራው ለአፍታም ተዘናግቶ አያውቅም ዱዓህን ይከጅላል በለው"

ጋዜጠኛው ንግግሩን ይቀጥላል

"ቱርክ እንደተመለስኩ ወደ ሳንጃክ ቶካት መንደር አመራሁ ከብዙ ጥረት በኋላ የአለቃውን አድራሻ አገኘሁ፡፡ ከብዙ ዓመታት በፊት መሞቱ ተነገረኝ።

የተመቻቸውን የትውልድ ሀገሩን ኑሮ ትቶ አል-አቅሳ መስጂድን እየጠበቀ ዓይኑን ከመስጂዱ ላይ ሳይነቅል እዚያው በተቀመጠበት እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1982 ወደ አኼራ ነጎደ፡፡

ለአመታት ፀሐይና ብርዱ እየተፈራረቀብን ለኢስላም ዘበኛ ልንሆን ይቅርና በታዘዝነው የኢስላም ህግጋት ላይ ቀጥ ያልን ስንቶቻችን ነን የተመቻቸ ኑሮውን ትቶ ተቦሳቁሎና ተርቦ ለኢስላም ዘብ የቆመን ፈልጋችሁ አምጡልኝ።

በታሪክ መዝገብ ላይ በጥሩ ተዘከር

https://ummalife.com/mahimahisho

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group