አምስት ነገሮችን ከረመዷን በፊት!!
በ አቡ ሀይደር
4ኛ) ይህ ወር የተውበት፣ የንሰሀና የምሕረት ወር ነው፡፡ ስለዚህ በተውበትና በኢስቲግፋር መበርታት ይጠበቅብሀል፡፡ በሐዲሥም እንደተገለጸው፡-
አቢ ሙሰል-አሽዐሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "አላህ የቀን ጥፋተኞችን ሊምራቸው በለሊት የራሕመት እጁን ይዘረጋል፡፡ የለሊትን ጥፋተኞችን ሊምራቸው በቀንም የራሕመት እጁን ይዘረጋል፡፡ ይህም የሚሆነው ጸሀይ ከመግቢያዋ በኩል ብቅ እስክትል ነው" (ሙስሊም 7165)፡፡
በሌላም ሐዲሡል ቁድሲይ ላይ ጌታችን፡- ‹‹የአደም ልጆች ሆይ! እናንተ በቀንም በለሊትም ኃጢአት ትፈጽማላችሁ፡፡ እኔ ደግሞ ኃጢአትን በመላ እምራለሁና እምራችሁ ዘንድ ማረን በሉኝ!›› ይለናል (ሙስሊም)፡፡
በተጨማሪም በሌላ ዘገባ ይኸው ጌታችን አላህ፡- ‹‹የአደም ልጅ ሆይ! ኃጢአትህ በዝቶ ሰማይ ጣሪያ ቢደርስና ከዛም ‹ጌታዬ ሆይ! ማረኝ› ብለህ ምሕረትን ብትጠይቀኝ፡ ምንም ሳይቸግረኝና ምንም ሳይመስለኝ እምርሐለሁ›› ይላል (ቲርሚዚይ 3540)፡፡
ታዲያ ዛሬ በረመዷን ወር ተውበት ያልገባህ መቼ ነው የምትቶብተው? በዚህ ወር ወደ አላህ ካልተመለስክ መቼ ነው የምትመለሰው?
ይቀጥላል...
ኢስላማዊ ዳእዋ በቴሌ ግራም ለመከታታል ሊንኩን ይጫኑት!
https://telegram.me/islamictrueth