Translation is not possible.

ፍልስጤማዊያን ህፃናት ከተናገሩት በጥቂቱ…

* ሁሉንም ነገር ለ አላህ ነግረዋለው። (የ ሶስት አመት ህፃን)

* የታሉ አረቦች፣ የታሉ ሙስሊም ሀገራት

* እህቴ ለደቂቃዎችም እንኳን ቢሆን አልተለየሁሽም

* አሽሃዱ አላ ኢላሀ አላ አላህ በል ወንድሜ

* በጋዛ በየቀኑ ስድስት ሰላት እንሰግዳለን… ፈጅር፣ ዝሁር፣ ዐስር፣ መግሪብ፣ ኢሻ እና ሰላተል ጀናዛ።

*

__________________________

* ፈለስጢናዊት እናት ልጇን ሁለቴ ትሸከማለች። የመጀመሪያው በሆዷ ሲሆን ሁለተኛው በጀናዛ መሸከሚያ ቃሬዛ ነው።

* ማታ ማታ ስንተኛ ሂጃባችንን ለብሰን ነው የምንተኛው። ምክንያቱም ቦምብ ተጥሎብን ከሞትን ጀናዛችን ሲያገኝ ተሸፋፍኖ እንዲገኝ እንፈልጋለንና።

* "ልጅህ ጠባብ የሆነ የመትረፍ እድል አለው።"

ይህ ዶክተሩ ስለ ልጄ የነገረኝ ነበር።ትንሽ ቆይቼ ስመለስ ልጄም የለም።ዶክተሩም የለም። ሆስፒታሉም የለም።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group