umma1700252771 Profile Picture
UMMA TOKEN INVESTOR

Translation is not possible.

‍ 🔰 ንስር እንደ ጥንካሬ

ሰማዩ ሲጠቁር ደመናው ወጀቡንም ሲያይል ሌሎች አዕዋፍት በየ አለቱና በየ ጢሻው ውስጥ ይደበቃሉ።

በቤት ታዛ ስርም ይደበቃሉ። ንስር ግን ደስ ይለዋል ወጀቡም ሲጀምር ንፋሱን በመሟገት የራሱን ጥንካሬ ይለካበታል።

የነፋሱን አቅጣጫ በመከተልም ይበራል። ራሱን ወደ ላይ ለማምጠቅ እና የከፍታውን ጫፍ ለመጨበጥ ይጠቀምበታል።

በዚህም ጥንካሬውን ይለካበታል። ንስር አሞራ ከአዕዋፍት ዘር ለ70 አመት የህይወት ዘመን የመቆየት እድል አለው።

ንስር አሞራ 70 አመት እድሜውን ለመኖር በ40ኛ አመቱ ላይ ከፍተኛ መሰዕዋትነት በሚጠይቅ ውሳኔ ላይ ይወድቃል። የንስር አሞራ የእግር ጥፍር በአግባቡ መስራች የሚችለው ለ40 አመት ብቻ ነው።

ንስር አሞራ ከተፈለፈለ ጀምሮ 40 አመት ከኖረ በኋላ በሰውነት ክፍሉ ላይ በሚታየው ለውጥ የተነሳ የአፍ መንቁሩ፣ የእግር ጥፍሩና ላባው እንደ በፊቱ ሊያገለግሉለት አይችሉም።

የእግር ጥፍሩ ደካማ በመሆኑ አደኑን በደንብ አይዝለትም። ረጅምና ስል መንቁሩ ይታጠፋል። ላባው በሰውነቱ ይለጣጠፍና ክብደት ስለ ሚጨምር እንደ ልቡ አይበርም።

በዚህ ወቅት ንስር አሞራ በሁለት ውሳኔዎች ላይ ይወድቃል።

ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠባበቅ! ወይም ደግሞ 5 ወር የሚፈጅበት ስቃይና መከራ ያለበት መሰዕዋትነት በመክፈል ቀሪ ዘመኑን እንደ ወጣት ንስር በደስታ መኖር!

30 ተጨማሪ እድሜ ለመኖር የ5 ወር መሰእዋትነት ይከፍላል።

ንስር አሞራ ቀሪ 30 አመት ለመኖር ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት ጎጆ ይቀልሳል። ንስር አሞራ በተራራው ላይ ጎጆውን ከቀለሰ በኋላ የመጀመሪያ ስራው የአፍ መንቁት ከአለት ጋር በመፋቅ ነቅሎ መጣል ነው።  ይህ ከፍተኛ ህመም እና ስቃይ አለው። ይሁን እንጂ አዲስ መንቁር ለማውጣት ይህን ማድረግ የግድ ነው። ከዚያ አዲስ መንቁር ከወጣለት ወይም ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁር አሮጌው የእግር ጥፍሩን ነቅሎ ይጥለዋል።

አዲሱ የእግር ጥፍሩን ከበቀለለት በኋላ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳሪያ በመጠቀም በሰውነቱ የተጣበቀውን ጥቅጥቅ ያለ ላባው ነቃቅሎ ጥሎ አዲስ እንዲበቅል ያደርጋል። ይህ ህመምና መከራ ያለው ድርጊት ነው።

ከዚያም የ5 ወር ማገገሚያ ጊዜ ካጠናቀቀ በኋላ እንደገና ራስን የመውለድ የትግል ሂደት ይጠናቀቅና ተጨማሪ 30 አመቱን በሰማይ እየበረረ እና እያደነ በደስታ ይኖራል።

➤ አንተም መከራና ፈተናን አትፍራ።

➤ በወጀብ እና በአውሎ ነፋስ ቢሆንም መንገድ አለና መከራውን ግብግቡን  የአዳዲስ ሀሳቦች መነሻ የጥንካሬህ መለኪያ አቅምህን የምትጠቀምበት አጋጣሚ ወደ ላይ የምትመጥቅበት  ከችግር ደመናዎች በላይ የምትንሳፈፍበት እድል አድርገው።

በህይወታችን ውስጥ የምንፈልጋቸው ለውጦች  አንዳንድ ጊዜ ባስቸጋሪ እና መራራ ሁኔታዎች ውስጥ እንድናልፍ የግድ ይሉናል።

የሰው ልጅ በህይወቱ መከራ ሲገጥመው ከዚህ አስቸጋሪ ህይወት ለመውጣት ወይም ለማምለጥ ብሎም ደስተኛ ለመሆን  የህይወት ልምዱን መለወጥ አሮጌ ልምዱን፣ ትዝታዎቹን የእለት እለት ኑሮውን አሸቀንጥሮ መጣል የግድ ይለዋል። እነዚህ አሽቀንጥረን የምንጥላቸው ነገሮች ግን ለማስወገድ ከፍተኛ መሰዕዋትነት ከከፈልን እንደ ንስር ቀሪ ዘመናችን በደስታ እንኖራለን።

እንደ ሌሎች ወፎች ከመከራውንም አንሸሽ ከችግሩንም አንደበቅ መከራን ለጥንካሬ እና ለበረከት እንጠቀምበት። እንደ ንስር ከፍ ብለን እንውጣ ዝቅ አንበል።  ከፍ ባልን ቁጥር ጥሩ እይታ ይኖረናል። ታጋሽ፣ አስተዋይ፣ ቻይ ያደርገናል። ከዛ በኋላ አሮጌ አስተሳሰባችን በማያስማሙን እኔ ብቻ የሚለው ስሜታችንን የሚያለያዩን ነገሮች ወደዚያ አሽቀንጥረን ነቅለን ጥለን በሚያስማሙን እና በሚያቻችሉን እንተካቸው......!!!!!!!

✍ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል

ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇

Telegram: t.me/SharpSwords1

Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1

YouTube: youtube.com/@SharpSwords1

Instagram: Instagram.com/sharp_swords1

Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

ጥቂት ስለዚህ ዲዛይን‼

=================

✍ ይህ ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ዲዛይን አፍሪካ ህብረት አካባቢ የተሰጠው የነጃሺ መስጅድና ኢስላማዊ ማዕከል ዲዛይን ነው። ከትናንት በፊት በወጣው የተወዳዳሪዎች ውጤት አሸናፊ የሆነው ዲዛይን ነው።

ብዙዎች «ኢስላማዊ ምልክት» የሌለው ነው፤ ከላይ ሲታይ ምንም ኢስላማዊ የሚመስል ምልክት የለውም ስትሉ ነበር፤ በውስጥም ያናገራችሁኝ ነበራችሁ።

የእኔ ሃሳብ፤ ለመሆኑ «ኢስላማዊ ምልክት» ማለት ምን ማለት ነው?

ሳንወሻሽ «ጨረቃና ኮከብ ምልክት» የለውመረ ለማለት ነው ኣ? በተጨማሪም የህንፃው ዲዛይን በወትሮው የምናውቀውን የመስጅድ ቅርፅ አይመስልም ለማለት ነው ኣ?

እንደዛ ከሆነ፤ በመስጅዶች ላይ ጨረቃና ኮከብን እንደ ምልክት መጠቀም በሸሪዓችን መሠረት የለውም። እንዳውም አንዳንዶች አላማውን አይተው ቢድዓህ ነው እስከማለት ደርሰዋል። ነገር ግን ከታለመለት በጎ አላማ አንፃር በዛ ደረጃ ላይደርስ ይችላል።

የተጀመረውና ኦፊሲያሊ ኢስላማዊ ምልክት የተደረገው ያኔ ኦቶማን ቱርኮች መለያቸውን መስቀል ካደረጉት የመስቀል ጦረኞች ለመለየት ብለው ነው። ሰንሰለቱም የAlexander the Great አባት Byzantiumን (ቆስጠንጣኒያን) ሲያጠቃ የተሸነፈበትን ምሽት ታሳቢ አድርገው ነው።

  (ዝርዝር ነገሮችን ከዚህ ኪታብ አንብቡ፦

"التراتيب الإدارية" للشيخ عبد الحي الكتاني رحمه الله (1 / 320) .

ኢብኑ ዑሠይሚንም አላህ ይዘንላቸውና፤ ይህን ጉዳይ ሙስሊሞች የሚያደርጉት እነርሱ "ቀይ መስቀል" ሲሉ እኛ "ቀይ ጨረቃ" ብለን ለመመሳሰል እና በተለያዩ ነገሮች ላይ ምልክቱን ስለሚጠቀሙት እኛም በራሳችን ለመጠቀም ከሆነ አይፈቀድም ብለዋል።

وقال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله :

" وضع الأهلة على المنائر قيل : إن بعض المسلمين الذين قلدوا غيرهم فيما يصنعونه على معابدهم ، وضعوا الهلال بإزاء وضع النصارى الصليب على معابدهم ، كما سموا دور الإسعافات للمرضى ( الهلال الأحمر ) بإزاء تسمية النصارى لها بـ ( الصليب الأحمر ) وعلى هذا فلا ينبغي وضع الأهلة على رؤوس المنارات من أجل هذه الشبهة ، ومن أجل ما فيها من إضاعة المال والوقت " انتهى .

"مجموع فتاوى ورسائل ابن عثيمين" (13 / 941)

√ በአጭሩ፦ ጨረቃና ኮከብን የምንጠቀመው የአላህን ታዕምር ገላጭ ከሆኑ ፍጡሮቹ መካከል ስለሆኑ ከምልክት አንፃር እንጂ የሚመለኩ ስለሆኑ ወይንም የተለዬ ነገር ስላላቸው አይደለም።

ከዚያ ወዲህ በብዙው ሙስሊም ዘንድ ስለተለመዱ ብቻ ጨረቃና ኮከብ ምልክት ሲቀር፤ ኢስላማዊ ምልክት የለውም ወደማለት ደረጃ መሄድ የለብንም።

ነገር ግን ይህ ዲዛይን የተመረጠው የእውነት እነዚህ ምልክቶች በሸሪዓው መሠረት የላቸው ተብሎ ነው ወይንስ አፍሪካ ህብረት አካባቢ ስለሆነ በኢስላማዊ ምልክትነት የተለመደ ነገር እንዳይቀመጥ ጫና ተደርጎ የሚለውን አላህ ይወቅ።

ያ ካልሆነ ግን አሁን ያለው ዲዛይን የሌላ እምነት ወይም ፈሳድ ነገር መታወቂያ የሆነ ነገር እስካልታየበት ድረስ፤ በአጠቃላይ ከሸሪዓው ጋር የሚጋጭ ምልክት እስከሌለው ድረስ፤ የተለመደው ጨረቃና ኮከብ ስለሌለው ብቻ ዲዛይኑን ኢስላማዊ ፋና የለውም ብሎ ማጣጣልና መተቸት ተገቢ አይደለም።

አላህ የበለጠውን ያውቃል።

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

አስቸኳይ መረጃ‼

=============

(ለሁሉም ይሰራጭ!)

||

✍ «ፕሮፌሰር ኢያሱ ኢሊያስ በተባለ የፓርላማ አባል አስተባባሪነት ህጋዊ የመስጂድ ካርታ እና የግንባታ ፍቃድ ያለው የመስጂድ ቦታ ግንባታ እንዳይደረግ ያለምንም ህጋዊ ምክንያት ታገደ ።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አግራዉ  በሚል ስያሜ የሚታወቀው መስጂድ በትላንትናው እለት ግዚያዊ የመስጂድ  አጥር ግንባታ ለማድረግ እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት የወረዳው አመራሮች ከከንቲብ ጽ/ቤት ተደውሎልናል በሚል  ግንባታው እንዲቆም አድርገዋል ።

ያለ ህግ አግባብ እንዲታገድ ስለተደረገበት ሁኔታ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ሲጠይቁ የአከባቢው ማህበረሰብ ቦታው ላይ መስጂድ እንዳይገነባ ፒትሽን ፈርሞ ስላስገባ ነው ካርታውን አምክነን ሌላ ተለዋጭ ቦታ እንሰጣቹሃለን የሚል ምላሽ ተሰጥቷል ።

ፕሮፌሰር እያሱ የተባለው የፓርላማ አባል መኖሪያ ቤቱ  ከመስጂዱ አጠገብ ሲሆን « እኔ እዚህ እያለው  በፍፁም አጠገቤ መስጂድ አይሰራም ‼ » በሚል በተለያየ ግዜ በአከባቢው ሙስሊሞች ላይ እንደሚዝትና በአከባቢው ላይ የሚገኙ ከ 90 የማይበልጡ የሌላ እምነት ተከታዮችን አስተባብረው ፒትሽን ማስገባቱን ለማወቅ ተችሏል  ።

ያለምንም የህግ አግባብ የመስጂዱ ግንባታ በመታገዱ ማህበረሰቡ በጊዚያዊነት የመስጂዱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ድንኻን በመወጠር ሰላቱን በማከናወን ላይ ይገኛል።»

መላው ህዝበ ሙስሊም በነገው ዕለት ዘነበ ወርቅ አካባቢ 72 ባጃጅ ተራ አግራው ሰፈር በመገኘት የጁሙዓህ ሶላትን በህብረት በመስገድ መስጂዱን እንዲያስከብር ጥሪ ተላልፏል።

ሁሉም ሼር በማድረግ ላልሰማ ያሰማ።

መልዕክቱን ለሁሉም በማድረስ መስጅዳችንን እናስጠብቅ።

||

t.me/MuradTadesse

fb.com/MuradTadesseOfficial

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🔴 የእስላማዊ ጂሃድ ንቅናቄ ምክትል ዋና ፀሀፊ ዶር. መሐመድ አል ሂንዲ፡- በካይሮ እየሆነ ያለው በ"እስራኤል" እና በጋዛ ዩናይትድ ስቴትስ ስላለው ችግር ላይ አስተያየት ለመስጠት ከተዘጋጁት ክፍሎች አንዱ ነው።

አል-ሂንዲ፡- ማንኛውም የእስረኞች ልውውጥ ጥቃቱ ካቆመ እና የጽዮናውያን ጦር ከጋዛ እስካልወጣ ድረስ እንደማይካሄድ አቋማችን ግልጽ ነው።

▫️ አል ሂንዲ፡ ተቃውሞው በዌስት ባንክ፣ እየሩሳሌም እና አል-አቅሳ መስጊድ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማስቆምም ያወራል።

👇👇👇

ለፈጣን መረጃ Zakariya nasir በሚለው ፔጃችን ገብታችሁ ፎሎ አድርጋችሁ ተከተሉን

Send as a message
Share on my page
Share in the group