Translation is not possible.

ጥቂት ስለዚህ ዲዛይን‼

=================

✍ ይህ ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ዲዛይን አፍሪካ ህብረት አካባቢ የተሰጠው የነጃሺ መስጅድና ኢስላማዊ ማዕከል ዲዛይን ነው። ከትናንት በፊት በወጣው የተወዳዳሪዎች ውጤት አሸናፊ የሆነው ዲዛይን ነው።

ብዙዎች «ኢስላማዊ ምልክት» የሌለው ነው፤ ከላይ ሲታይ ምንም ኢስላማዊ የሚመስል ምልክት የለውም ስትሉ ነበር፤ በውስጥም ያናገራችሁኝ ነበራችሁ።

የእኔ ሃሳብ፤ ለመሆኑ «ኢስላማዊ ምልክት» ማለት ምን ማለት ነው?

ሳንወሻሽ «ጨረቃና ኮከብ ምልክት» የለውመረ ለማለት ነው ኣ? በተጨማሪም የህንፃው ዲዛይን በወትሮው የምናውቀውን የመስጅድ ቅርፅ አይመስልም ለማለት ነው ኣ?

እንደዛ ከሆነ፤ በመስጅዶች ላይ ጨረቃና ኮከብን እንደ ምልክት መጠቀም በሸሪዓችን መሠረት የለውም። እንዳውም አንዳንዶች አላማውን አይተው ቢድዓህ ነው እስከማለት ደርሰዋል። ነገር ግን ከታለመለት በጎ አላማ አንፃር በዛ ደረጃ ላይደርስ ይችላል።

የተጀመረውና ኦፊሲያሊ ኢስላማዊ ምልክት የተደረገው ያኔ ኦቶማን ቱርኮች መለያቸውን መስቀል ካደረጉት የመስቀል ጦረኞች ለመለየት ብለው ነው። ሰንሰለቱም የAlexander the Great አባት Byzantiumን (ቆስጠንጣኒያን) ሲያጠቃ የተሸነፈበትን ምሽት ታሳቢ አድርገው ነው።

  (ዝርዝር ነገሮችን ከዚህ ኪታብ አንብቡ፦

"التراتيب الإدارية" للشيخ عبد الحي الكتاني رحمه الله (1 / 320) .

ኢብኑ ዑሠይሚንም አላህ ይዘንላቸውና፤ ይህን ጉዳይ ሙስሊሞች የሚያደርጉት እነርሱ "ቀይ መስቀል" ሲሉ እኛ "ቀይ ጨረቃ" ብለን ለመመሳሰል እና በተለያዩ ነገሮች ላይ ምልክቱን ስለሚጠቀሙት እኛም በራሳችን ለመጠቀም ከሆነ አይፈቀድም ብለዋል።

وقال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله :

" وضع الأهلة على المنائر قيل : إن بعض المسلمين الذين قلدوا غيرهم فيما يصنعونه على معابدهم ، وضعوا الهلال بإزاء وضع النصارى الصليب على معابدهم ، كما سموا دور الإسعافات للمرضى ( الهلال الأحمر ) بإزاء تسمية النصارى لها بـ ( الصليب الأحمر ) وعلى هذا فلا ينبغي وضع الأهلة على رؤوس المنارات من أجل هذه الشبهة ، ومن أجل ما فيها من إضاعة المال والوقت " انتهى .

"مجموع فتاوى ورسائل ابن عثيمين" (13 / 941)

√ በአጭሩ፦ ጨረቃና ኮከብን የምንጠቀመው የአላህን ታዕምር ገላጭ ከሆኑ ፍጡሮቹ መካከል ስለሆኑ ከምልክት አንፃር እንጂ የሚመለኩ ስለሆኑ ወይንም የተለዬ ነገር ስላላቸው አይደለም።

ከዚያ ወዲህ በብዙው ሙስሊም ዘንድ ስለተለመዱ ብቻ ጨረቃና ኮከብ ምልክት ሲቀር፤ ኢስላማዊ ምልክት የለውም ወደማለት ደረጃ መሄድ የለብንም።

ነገር ግን ይህ ዲዛይን የተመረጠው የእውነት እነዚህ ምልክቶች በሸሪዓው መሠረት የላቸው ተብሎ ነው ወይንስ አፍሪካ ህብረት አካባቢ ስለሆነ በኢስላማዊ ምልክትነት የተለመደ ነገር እንዳይቀመጥ ጫና ተደርጎ የሚለውን አላህ ይወቅ።

ያ ካልሆነ ግን አሁን ያለው ዲዛይን የሌላ እምነት ወይም ፈሳድ ነገር መታወቂያ የሆነ ነገር እስካልታየበት ድረስ፤ በአጠቃላይ ከሸሪዓው ጋር የሚጋጭ ምልክት እስከሌለው ድረስ፤ የተለመደው ጨረቃና ኮከብ ስለሌለው ብቻ ዲዛይኑን ኢስላማዊ ፋና የለውም ብሎ ማጣጣልና መተቸት ተገቢ አይደለም።

አላህ የበለጠውን ያውቃል።

||

t.me/MuradTadesse

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group