UMMA TOKEN INVESTOR

About me

Alhemdulillah for every things

Translation is not possible.

የኪሳኢይ ገጠመኝ እና ወሳኝ ማስታወሻ

ኪሳኢይ ረሒመሁላህ ትልቅ የዐረብኛ እና የቁርኣን ጥናት ሊቅ ናቸው። የሆነ ጊዜ የገጠማቸውን አስገራሚ ክስተት እንዲህ ይገልፁታል።

በአንድ ወቅት ኸሊፋው ሀሩን አረሺድ ዘንድ እያሰገድኩ ሳለሁ አቀራሬ መሰጠኝ። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለሁ ፈፅሞ ህፃን የማይስተውን ስህተት ፈፀምኩ። "لعلهم يرجعون" (ለ0ለሁም የርጂዑን) ለማለት ፈልጌ "لعلهم يرجعين" (ለ0ለሁም የርጂዒን) ብዬ ቀራሁ።

በአላህ ይሁንብኝ ኸሊፋው ሃሩን አረሺድ "ተሳሳተሃል!" ሊለኝ አልደፈረም። ይልቁንም ካሰላመትኩኝ በኋላ:

* "ኪሳኢይ ሆይ! ይሄ የምን አነጋገር ነው?" አለኝ።

= "የአማኞች አዛዥ ሆይ! የሰለጠነ ፈረስም'ኮ አንዳንዴ ይንሸራተታል" አልኩት።

* "ይሄስ ልክ ነው" አለ።

ኢማሙ ዘሀቢይ ረሒመሁላህ ይህን ታሪክ ከጠቀሱ በኋላ እንዲህ ይላሉ፦

"አእምሮው ይህንን ንግግር የተገነዘበ ሰው አንድ ዓሊም የፈለገ ያክል ደረጃው ከፍ ቢልና በዒልም ቢገን እንኳ ከስህተቶች የማይተርፍ መሆኑ ነው። እነዚህ ስህተቶች መገኘታቸው ግን አዋቂነቱን አያጎድፉም፡፡ ደረጃውንም ዝቅ አያደርጉም፣ አያጎድሉትምም። የእውቀትና የመልካም ገድል ባለቤቶችን ስህተቶች በዚህ መልኩ እየተረጎመ ያለፈ መንገዱ ምስጉን፣ አካሄዱም ድንቅ ነው። ለትክክለኝነትም የታደለ ይሆናል።"

ምንጭ:- [ሲየሩ አዕላሚ ኑበላእ፡ 1/376]

ሰዎች ላይ የሚታዩ ስህተቶች የተለያየ መልክ ይኖራቸዋል።

* አንዳንዱ ከሚያራምዱት አካሄድ የመነጨ አቋም ተደርጎ የተያዘ ስህተት ነው።

* አንዳንዱ የተሳሳተ መረጃ በመያዛችን ወይም በተሳሳተ መልኩ በመረዳታችን የሚገጥም ስህተት ነው።

* አንዳንዱ ደግሞ በሚገጥመን ጊዜያዊ ግርታ ሰበብ የሚከሰት ነው።

* ሌላው ደግሞ ትኩረት ባለመስጠታችን የሚከሰት ምናልባትም መሳሳታችንን እንኳ ሳናውቀው የሚከሰት ነው።

ሁሉንም ባንድ ጨፍልቆ መረዳት እንደማይገባ ጤነኛ ጭንቅላት አያጣውም። ይልቁንም እንደየ ሁኔታቸው መያዝ ይገባል። አንዳንዴ ደርስ እየሰጠን፣ ደዕዋ እያደረግን ሳለን ደግሞ ለመናገር እንኳ የሚሰቀጥጥ ቃል ያመልጠናል። ሰዎች ነንና እነዚህን የመሰሉ ስህተቶች ብዙዎቻችንን ይገጥሙናል። ከመሰል ስህተቶች የሚተርፉ ካሉ ምናልባት ይሄ ነው የሚባል ተሳትፎ የሌላቸው ይሆናሉ።

ትኩረቴ በተለይ የዑለማዎችን ወይም የዱዓቶችን ትምህርቶች ስንከታተል የሆነ ስህተት ሲገጥመን ሊደንቀን ወይም ልናራግብ አይገባም ለማለት ነው። በተለይ በመልካም የምናውቃቸው ከሆኑ። በጥፋት የምናውቃቸው እንኳ ቢሆኑ ድንገተኛ ስህተቶችን እንደ ቋሚ መንሃጅ አድርጎ ማራገብ አይገባም። ልብ በሉልኝ! ጥቆማ ወይም እርምት አይሰጥ እያልኩ አይደለም። ይልቁንም እራሳችን እንድንያዝበት በማንፈልገው መልኩ ሌሎችን ልንይዝ፣ ስህተቶችን በመጎርጎር ላይ ልንጠመድና አድብተን ልንጠባበቅ አይገባም ለማለት ነው። የድምፅ ትምህርቶች ወይም ከድምፅ ትምህርቶች ተገልብጠው የተዘጋጁ ኪታቦች ላይ እንዲህ አይነት ስህተቶች በብዛት ያጋጥማሉ። የነሕው ትምህርት ላይ የነሕው ስህተት ያጋጥማል። ሰው በቃል ሲናገርና ሲፅፍ አንድ አይደለም። በየእለቱ የምንናገረው አማርኛ ውስጥ ብዙ የሰዋሰው ግድፈት አለበት። ከድምፅ ትምህርቶች ተገልብጠው የተዘጋጁ ኪታቦች ላይ የሰዋሰው ስህተት አገኘን ብለዉ ዓሊሞችን የሚጎነታትሉ አካላት በተጨባጭ አሉ። በዚህ መልኩ ቢያዝ በርግጠኝነት ማንም አይተርፍም።

አንዳንዴ ደግሞ ስህተቱ ከኛ አረዳድ ይሆናል። የሆነ ጊዜ የሆኑ ሸይኽ በሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን የአጅሩሚያህ ሸርሕ ላይ ስህተት አገኘሁ በሚል መነሻ አጠቃላይ የሳዑዲ ዓሊሞችን ጎንተል ያደርጋሉ። ቦታው ላይ የነበሩ ወንድሞች ጉዳዩን አጥብቀው ይይዙትና ጭቅጭቅ ይከሰታል። ደግነቱ ሸይኹ ነፍሲያ አልያዛቸውም። በማግስቱ ስህተቱ የራሳቸው እንደሆነ አመኑ።

አንዳንዴ ደግሞ ዓሊሞቹ ፊትና ጋር የተያያዘ ጥያቄ ሲጠየቁ መልሱን ጥለው ምክር ወይም ቁጣ ያዘለ ተግሳፅ ይሰጣሉ። በዚህን ጊዜ አንዳንዶች የተጠየቀው ጥያቄ ላይ ብቻ በማነጣጠር "ሸይኽ እከሌ በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲህ አሉ"፣ "በእከሌ ላይ ተናገሩ"፣ "ለእከሌ ተከላከሉ" የሚል ደማቅ ርእስ ሰጥተው ያራግቡታል። በእንዲህ አይነት ጉዳይ ላይ ከስሜት ነፃ ሆኖ አላህን በመፍራት የዑለማኦችን ንግግር ያላግባብ ከመመንዘር መጠንቀቅ ይገባል።

ሳጠቃልል እራሴን ጨምሮ ለሁሉም የማሳስበው ከሆነ አካል ስህተት የመሰለን ወይም በርግጥም ስህተት የሆነን ንግግር ስናገኝ ከማራገባችን ወይም "ረድ" ብለን ለምላሽ ከመቸኮላችን በፊት አላህን በመፍራት ግራ ቀኝ ማየት እንደሚገባ ለማስታወስ ነው።

👇👇👇👇👇👇

ጥያቄአችሁን በዚህ ፃፉልን

👆👆👆👆❗️👆

https://t.me/OfficialDemas

Telegram: Contact @OfficialDemas

Telegram: Contact @OfficialDemas

ይህ ቻናል በአህለል ሱና ወልጀማዓ የተደረጉ ዳእዋዎችና በዲናዊ አዝናኝ ግጥሞች ፤ሀዲሶች ታሪኮች እናንተን ማዝናናት ነው። በተጨማሪም የተደበቁ የጴንጤዎች ተንኮልና አደጋዎች ወደ ህዝበ ሙስሊሙ ያደርሳል። በህዝበ ሙስሊሙ ላይ የተጋረጠ ወቅታዊ አደጋም ካለ እየመረመረ ያደርሳል። ይህ ሁሉ የሚሆነው በአሏህ ፈቃድ ነው። ይግቡ ይቀመጡ ይዝናኑ ይማሩ የናንተ ሚድያ ነው።
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

🙏💯በህይወታችን ትዕግስተኛ መሆን ከቻልን የምንፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ ጊዜያቸውን ጠብቀው ወደእኛ ይመጣሉ😘

❤️በፍቅር አለም ውስጥም ትልቁን ዋጋ ሚያስከፍለው ትዕግስት ነው⭐️

🔔መታገስ ይከብዳል ያ ጊዜ ሲያልፍ ግን ምንፈልገውን እናገኛለን መራራውን ግዜ አልፈህ ጣፋጩን ፍሬ ትበላ ዘንድ ታጋሽ ሁን🥰

❤️ትዕግስተኞች ከ ጉልበተኞች💪 ይበልጣሉ❤️💯☑️

🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨🪴

     

🥰🥰🇪🇹 ሰላም 🇪🇹ፍቅር🇪🇹 🇪 🇹 😘😘

👉የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇

https://t.me/islam_my_life1

Telegram: Contact @islam_my_life1

Telegram: Contact @islam_my_life1

ወደ አላህ ከጠራና መልካምን ከሠራ፡እኔ ከሙስሊሞች ነኝካለ ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው? ቁርአን41:33 ?ኢንሻአላህ እምነትን በእውቀትchanali አላማው? #ቁርአን እና ሀዲስ #አስተማሪ ታሪኮች በአማርኛ #ጥበባዊ ንግግሮች_አባባሎችና ምክሮች ➡️በቡኻሪና ሙስሊም ሳይገደብ በሌሎች የሐዲስ ሊቃውንቶች የተዘገቡ ነቢያዊ ሀዲሶችም ይቀርቡበታል። ➾አላህ ያወቅነውን የምናሳውቅ
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

💞የወዳጅህን ቦታ እወቅ....❗️

❤️አንዳንድ ልብ  የወዳጇን ቦታ የምትረዳው ስታጣው ብቻ ነው🙏💯

💖ብልጧ ልብ ደግሞ ወዳጇን ከማጣቷ በፊት እንዳታጣው ትጠብቀዋለች......❗️

🇵🇸🇵🇸 #ድል_ለሙስሊሞች????

🇵🇸 #ዲል_ለፈለስጢን??

Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group
Translation is not possible.

‍ 👨የሕፃኑ አስደናቂ ታሪክ

•┈┈•❈••✦✾✦••❈•┈┈•

☞በአረብ አለም የሚኖር አንድ የአሥር አመት ታዳጊ ነው

ይህ ታዳጊ የሰራው ነገር ግን ሠውን አጃኢብ አስኝቷል።

ነገሩ እንዲህ ነው:

ይህ የአስር አመት ህፃን ዘውትር በሠላት ወቅቶች ከመሥጂድ ይታደማል

ሠላቱም በጀመዓ ይሠግዳል ድምፅ ከፍ ተደርጎ በሚሰገድባቸው ሦስት ሠላቶች ላይ ታዲያ ኢማሙ ፋቲሀን ቀርቶ ሲጨርስ ማለትም ወለዷ ሊን ሲል ሠጋጁ በአንድነት አሚን ሢል ይህ ልጅ ድምፁን ከፍ አድርጎ ከጀመዓው ተነጥሎ ብቻውን አሚን ይላል....

🔴ይህ ነገር በመደጋገሙ ኢማሙን እጅግ ያበሳጨው ነበር ቢያየው ቢያየው ልጁ ሊያቆም ስላልቻለ አንድ ቀን ከመግሪብ ሠላት በኃላ ንዴቱን መቆጣጠር ያቃተው ኢማም ይህን ልጅ እንቅ አድርጎ አንጠልጥሎ ያምባርቅበታል!

🤔ለምንድነው ምትረብሸው ከጀመዓው ጋር አብረህ ለምን አሚን አትልም እና መሰል ነገሮችን ይህን ህፃን ልጅ ተናገረው ይህ ታዳጊ በፍርሃት በተሸበሸቡት ልብሶቹና ቲማቲም በሚመሥሉ ጉንጮቹ እምባ ያቀረሩ አይኖቹ ያንን ኢማም በሥሥት እየተመለከቱ...

🗣«እኔ ምጮህው አለ......

እኔ ምጮህው እቤታችን መስጂዱ አጠገብ ነው አባቴ ደሞ ሠላት አይሰግድም ምናልባት የኔን ድምፅ ሢሠማ ደስ ብሎት አልያም ተደንቆ ከመጣና ከሠገደ ብዬ ነው ያ ኢማም» ብሎ መለሰለት ይህን ጊዜ ኢማሙ ሚናገረው ጠፋው ሠውነቱ ተርገፈገፈ የአከባቢውን ሠው አፈላልጎ ይህን ለአባቱ አደረሠው አባቱም በልጁ ተግባር እጅግ ተደንቆ ወደ ጌታው አልቅሦ ተውበት በማድረግ ሠላቱን ጀመረ።

🚫ሰዎችን አይተን ብቻ በችኮላ አንፍረድ። ይህን ለመስራት ያበቃቸው ምን ምክንያት ሊኖር ይችላል ብለን ኡዝር እንፈልግላቸው ምናልባት መጥፎ ሥራ የሚሰሩ መስሎን ሲፈተሽ ግን በጣም የሚደንቅ ሊሆን ይችላል!!

♥️ሱብሃን አላህ

በጣም ልብ የሚነካ ታሪክ ነው

"ወደ መልካም ነገር  ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

ኮፒ,

Send as a message
Share on my page
Share in the group